በመከላከያ ሰራዊ ውስጥ ባሉ ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የብሄረሰብ ተዋጽኦ

ግንቦት 18 2001 ዓ.ም

በዘረኝነት ላይ የተመሰረተው የወያኔ አገዛዝ በውስጡ ባሰባሰባቸው ጥቂት ፀረ አገርና ጸረ ህዝብ ሃይሎች ላለፉት 18 አመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች በአገሪቷ ታሪክ ታይተው የማይታወቁ መሆናቸው ተብሎ ያለቀለት ነገር ነው። በማንኛውም አገር ያልተለመደ ይልቁንም የአውሮጳ ቅኝ ገዥዎች ቅኝ በገዙዋቸው አገሮች ይፈጸሙት የነበረው አይነት ግፍና መከራ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ለመሆኑ ለኢትዮጵያዊያን መግለጽ ለቀባሪ ማርዳት ነው:

ወያኔ ወደ ስልጣን በመጣ ማግስት ጀምሮ የአገሪቱን ሃብት አይን ባወጣ መንገድ መዝብሯል፡; የንግድና የኢኮኖሚ ተቋማቱን ፍጹም ይሉኝታ በሌለውና በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለአፍራሽ አላማ ከአንድ ዘውግ በተሰባሰቡ የጥቅም ሸሪኮች እጅ እንዲገባ አድርጓል፡ለመብታቸው መከበር የተነሱትን ዜጎች ለመደፍጠጥ ከደርግ በከፋ ፋሽስታዊ ጭካኔ ጨፍጭፏል።

በ17 ዓመታቱ የደርግ ኮሚንስታዊ አስተዳደር የተማረረው አብዛኛው የአገራችን ህዝብ ጸረ ደርግ ትግል አካሂዳለው ይል የነበረን ወያኔን አቅፎና ደግፎ ለድል ያበቀበት ዋናው ምክንያት የወያኔን መሪዎች አገራዊ አጀንዳ አላቸው ብሎ በማመኑ እንደነበር የግንቦት 7 ንቅናቄ ያምናል:: ግንቦት 7 በኢትዮጵያ ላይ በተደጋጋሚ ተቃጥቶ የነበረን የውጭ ወረራ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ሲመክት ከኖረው ጀግናው የትግራይ ህዝብ አብራክ እንደ መለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረአበሮቹ ያሉ ከሃዲዎች ይፈጠራሉ ብሎ ለማመን ይቸገራል። ወያኔ በአገዛዝ ዘመኑ በተግባር እንዳስመሰከረው ጸረ አማራ; ኦሮሞ :ጉራጌ: ወላይታ: ከምባታ: አፋር: ሱማሌ : አኝዋክ ወዘተ ይሆናል ተብሎ ቢታሰብ ኖሮ ሌላው ቢቀር የወሎ : የጎንደር የጎጃምና የሰሜን ሸዋ ህዝብ በጉያው ውስጥ ደብቆ ከደደቢት አሰከ ሰሜን ሸዋ የሚዘልቀውን ጠመዝማዛ መንገድ እንዲጓዝና ምንሊክ ቤተመንግሥት ድረስ እንዲዘልቅ አይፈቅድለትም ነበር። የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይን ህዝብ እንደሌሎች ህዝቦች በወንድምነትና በእህትነት በመመልከትና ከአካባቢው የተነሳውን ትግል እንደራሱ ትግል አድረጎ በመውሰድ ወያኔ የጀመረው ትግል ዳር እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ወያኔ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ያደረገለትን ውለታ በመዘንጋት ዋና ዋና የሚባሉትን የመከላክያ፣ የደህንነትና የፖሊስ የአዛዥነት ስልጣን ቦታዎችን ከአንድ ጎጥ በመጡ ሰዎች አስይዟል። ይህን የሚያደርገውም ሌላውን የኢትዮጵአ ህዝብ በመናቁ፣ በመጥላቱና በመፍራቱ መሆኑን መግለጽ ያሻል።

ምንም እንኳ ወያኔ እነዚህን ቁልፍ የስልጣን ቦታዎች በጎጡ ልጆች እንዲያዙ ቢያደርግም፣ ከአፓርታይድ አገዛዝና ከሌሎችም ተሞክሮዎች እንደታየው፣ በዘር ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ረጅም እርቀት መጓዝ አለመቻሉን ነው። በዘር ላይ ተመስርተው የነበሩ አገዛዞች አወዳደቃቸው እንደላማረ ሁሉ የወያኔ የመጨረሻ ውድቀትም ከእነሱ የከፋ እንጅ የተሻለ እንደማይሆን ግንቦት 7 ያምናል።

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፣ በጠባብ የጥቅም ዓላማ ከእንድ ጎጥ በመጡ ሰዎች ፍጽም ጭካኔ በተሞላው አኳሀን እየተገዛህ መሆንክህን ለማሳየት ከመከላከያ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው አቅርበንልሀልና ፍርዱን አንተው እንደትሰጥ እንጠይቃለን። የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁትን ጨምሮ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለሄውም ወገናችን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተውን ይህንን ፍጹም አድል’ኦ በመቃወም ለፍትህ ለ’እኩልነትና ለዲሞክራሲ የምናደርገውን ትግል ትደግፍ ዘንድ ወቅቱ አደራ ይልሃልና ይህን መረጃ ተመልክተህ ውሳኔህን በአስቸኳይ እንድትሰጥም እንጠይቃለን።

በመከላከያ ሰራዊ ውስጥ ባሉ ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የብሄረሰብ ተዋጽኦ

የመከላከያ ዋና መምሪያዎች

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 ጠቅ/ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ትግሬ
2 ስልጠና ዋና መምሪያ ሌ/ጅኔራል ታደሰ ወረደ ትግሬ
3 ሎጂሰቲክ ዋና ሌ/ጅኔራል ገዛኢ አበራ ትግሬ
4 መረጃ ውና መምሪያ ብ/ጅኔራል ገብረ ዴላ ትግሬ
5 ዘመቻ ዋና መምሪያ ሜ/ጅኔራል ገ/እግዜብሄር ትግሬ
6 መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሌ/ጅኔራል ብርሃነ ነጋሽ ትግሬ
7 አየር ሃይል አዛዥ ብ/ጅኔራል ሞላ ሃይልማሪያም ትግሬ

እዝ አዛዦች

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 ማእከላዊ እዝ ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ አገው
2 ሰሜን እዝ ሌ/ጅኔራል ሳረ መኮንን ትግሬ
3 ደቡብ ምስራቅ እዝ ሜ/ጅኔራል ገአብርሃ ወ/ገብረኤለ ትግሬ
4 ምእራብ እዝ ብ/ጅኔራል ስዩም ሃጎስ ትግሬ

ክፍል ጦር አዛዦቸ – ማእከላዊ እዝ

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 31ኛ ክ/ጦርአዛዥ ኮ/ል ፀጋዬ ማርክስ ትግሬ
2 33ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ኪዳኔ ትግሬ
3 35ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ምስገናው አለሙ አገው
4 24ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ወርቅአይኑ ትግሬ
5 22ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ድኩል ትግሬ
6 8ኛ ሜ/ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ጀማል መሃመድ ትግሬ

ሰሜን እዝ

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 14ኛ ክ/ጦርአዛዥ ኮ/ል ወዲ አንጥሩ ትግሬ
2 21ኛ ክ/ጦርአዛዥ ኮ/ል ጉእሺ ገብሬ ትግሬ
3 11ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ወርቂዱ ትግሬ
4 25ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ተስፋይ ሳህል ትግሬ
5 20ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ተክላይ ክላሽን ትግሬ
6 4ኛ ሜ/ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ህንጻው/ጊዮርጊስ ትግሬ

ደቡብ ምስራቅ እዝ

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 19ኛ ክ/ጦርአዛዥ ኮ/ል ወዲ ጉአኤ ትግሬ
2 44ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ዘውዱ ተፈራ አገው
3 13ኝ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ሸሪፎ ትግሬ
4 12ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ሙሉጌታ ብረሀ ትግሬ
5 32ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል አብርሃ ጸሊም ትግሬ
6 6ኛ ሜ/ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ገ/መድህን ፈቃደ ትግሬ

ምእራብ እዝ

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 23ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ወልደ ብእላሎም ትግሬ
2 43ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ወዲ አባተ ትግሬ
3 26ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል መብራቱ ትግሬ
4 7ኛ ሜ/ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ገብረገ/ማርያም ትግሬ

የመከላከያ ልዩ መምሪያዎች

ተራ/ቁ የስራ ምድብ ወታደራዊ ማእረግ ስም ዘውግ/ዘር/ጎሳ
1 አግአዚ ኮማንዶ ክ/ጦር አዛዠ ብ/ጄ መሃመድ ኢሻ ትግሬ
2 አ/አ ዙሪያ ጥበቃ ክ/ጦር አዛዠ ኮ/ል ዘነበ አማረ አገው
3 ቤተ መንግስት ጥበቃ ሃላፊ ኮ/ል ገረንሳይ ትግሬ
4 የባንኮች ጥበቃ ሃላፊ ኮ/ል ሃዋዝ ወልዱ ትግሬ
5 ኤንጂኔሪንግ ኮሌጅ አዛዥ ኮ/ል ሃለፎም እጅጉ ትግሬ
6 ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዛዥ ብ/ጄ ተስፋይ ግደይ ትግሬ
7 ሙሉጌታ ቡሌ ቴክኒክ ኮሌጅ አዛዥ ኮ/ል መለያ አማረ ትግሬ
8 ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ አዛዥ ኮ/ል ለታይ ትግሬ
9 ስታፍና ኮማንድ ኮሌጅ ብ/ጄ ሞግስ ሃይለ ትግሬ
10 ብላቴን ማሰልጠኛ ማእከል ኮ/ል ሳልህ በሪሁ ትግሬ
11 ውርሶ ማሰልጠኛ ማእከል ኮ/ል ነጋሽ ህሉፍ ትግሬ
12 አዋሽ አርባ ማሰልጠኛ ማእከል ኮ/ል ሙዜ ትግሬ
13 ብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ማእከል ኮ/ል ነጋሲ ሽኮርተት ትግሬ
14 መከላከያ አስተዳደር መምሪያ ሃላፊ ብ/ጄ መሃሪ ዘውዴ ትግሬ
15 መከላከያ ደጀን አቬሽን ሃላፊ ብ/ጄ ክንፈ ዳኘው ትግሬ
16 መከላከያ ጥናትና ምርምር ሃላፊ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ ትግሬ
17 መከላከያ ፍትህ መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል አስካለ ትግሬ
18 ኤታ/ሹም ጽ/ቤት ሃላፊ ኮ/ል ጸሃየ ማንጁስ ትግሬ
19 ኢንዶክትሪኔሽን ማእከል ሃላፊ ብ/ጄ አከለ አሳየ አማራ
20 መገናኛ መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ስብሃት ትግሬ
21 ውጭ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ሃሰነ አማራ
22 ልዩ ሃይሎች ማስተባበሪያ ማእከል ሃላፊ ብ/ጄ ፍስሃ ማንጁስ ትግሬ
23 ኦፐሬሽን መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ወዲ ጠውቅ ትግሬ
24 እቅድ ዝግጅትና ፕሮግራም መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ተክላይ አሸብር ትግሬ
25 መከላከያ ኢንዱስትሪዎች ማስትባበሪያ ሃላፊ ኮ/ል ወዲ ነጋሽ ትግሬ
26 መከላከያ ፋይናንስ መምሪያ ሃላፊ ብ/ጄ ዘውዱ ትግሬ
27 መከላከያ ግዥ መምሪያ ሃላፊ ኮ/ል ግደይ ትግሬ
28 መከላከያ በጀት መምሪያ ሃላፊ አቶ ብርሃነ ትግሬ

 

አጭር ማጠቃለያ

1.  በሃገሪቱ -ውሰጥ ባሉት 61 ቁልፍ የመከላከያ ሃላፊነቶች ከተመደቡት ግለሰቦች መሃል በዘውግ ተዋጽኦዋቸው

 • 57 ትግሬዎች
 • 2 አገዎች
 • 2 አማሮች ይገኙበታል

2.  ከላይ የተቀመጠው አሃዝ የበለጠ ሲተነትን

 • በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ 7 ቁለፍ ቦታዎች 6 መምሪያዎቸና የኤታማዦር ሹምነቱን ጨምሮ በሙሉ የተያዙት በትግሬዎች ነው
 • ከእዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ሃይሉ ውሰጥ የሚገኙ 28 የጦር አዛዦች መሃል 26ቱ ትግሬዎች ሲሆኑ የተቀሩት ሁለቱ አገዎች ናችው። በደረሰን መረጃ መሰረት ሁለቱም አገዎች ለስም የተቀመጡ ሲሆኑ ማንኛውም ሰልጣን ያለው በስራቸው ባሉ የትግራይ መኮንኖች ፈላጭ ቆራጭንት የሚፈጸም ነው። ይህ አሰራር የትግራይ ተወላጆች በሃላፊነት ባለተመድቡባቸው ቦታዎች በሙሉ በስራ ላይ የዋለ ነው። በሰራዊቱ ውስጥ አልፎ አልፎ በተለያዩ ቦታዎች በሃላፊነት የተመደቡ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች ያልሆኑ ቢገኙም አንዳቸውም ስልጣን የሌላቸው በስራቸው በተመደቡ ትግሬዎች የሚታዘዙ ናቸው
 • ከላይ ከተጠቀሱት 61 ከፍተኛ ቁልፍ ሃላፊነቶች መሃል በአጠቃላይ 25 ጄነራሎች ሲገኙ ከእነዚሀ መሃል 22 ትግሬዎች ሲሆኑ 2 አማራዎች 1 አገው ይገኙበታል። ከሁሉ የሚገርመው ከላይ ከተጠቀሱት ቁልፍ 61 የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ለይስሙላ እንክዋን ቢሆን አንድም የኦሮሞ ተወላጅ አለመገኘቱ ነው። ይህ በወታደራዊ ዘረፉ ከፍተኛ ዘረኛነት የሚንጸባረቅበት አሰራር በሲቪል አስትዳደሩና መንግስታዊ በሆኑ ተቅዋማት በሙሉ የሚታይ ነው። በእዚህ በዘረኛነት መጠቃቀም በሚያዝ ስልጣን በመጠቀም በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ የተቀመጡት የትግራይ ተውላጆች በሙስናና እንዳሻችው ራሳችው ለመጠቀም በሚያወጡት መመሪያ አማካይነት የከፍተኛ ሃብት ባለቤቶች ሆነዋል።
 • ከእዚህ በተጨማሪ አሁን በስልጣንና በስራ ላይ ከሚገኙት 39 ጄነራሎች መሃል 28ቱ ትግሬዎች ሲሆኑ 5 ኦሮሞ 4 አገው 2 አማሮች ይገኙበታል። ቀደም ብለን እንደጠቀስነው አምስቱም የኦሮሞ ጄነራሎች ምንም ሃላፊነት በሌለው ቦታ የተመደቡ ናቸው። የጀነራሎቸ ሹመት የፖለቲካ ሹመት ሲሆን ሹምት ስጭው መለስ ዜናዊ ለብሄራዊ ተዋጽኦ ተጨንቆ የሚፈጽመው መሆኑን ስንስማ ይህ ጭንቀት በሌለበት ከጄነራልነት በታች ለሚገኙ ማእረጎች የሚስጥ ሹምት ምን ያህል በዘረኛነት የተጨማልቀ አንደሚሆን ማሰቡ የሚሰቀጥጥ ይሆናል።
 • አሁን በስራዊቱ ውስጥ ያለው ዘረኛ አደረጃጀት ቀድሞ ከነበረበት አስክፊ ደረጃ አሁን ወደሚገኘበት የባሰ ደረጃ የደረስው ከምረጫ 97 በሁዋላ ነው። በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደላችሁም በሚል ስበብ በጅጅጋ (2800) በሃረር(1800) በውርሶ፣ ብላቴ፣ አዋሳ፣ ታጠቅ፣ ጦላይ፣ ደዴሳ፣ ብር ሸለቆ፣ ፓዊ፣ አዘዞ፣ ጢጣ (ደሴ)፣ ሽሬ፣ ኩያ፣ አዋሽ አርባ( 520) ሰመራ በተባሉት ቦታዎች ታስረው ከ4 ወር እስከ 17 ወር ከተንገላቱ ብሁዋላ የጡረታ መብታቸው እንክዋን ሳይጠበቅ፣ ወደ ትውልድ ሃገራቸው መሳፈሪያ ሳይሰጣቸው ከሰራዊቱ ተባረዋል። ይህ በማአከል የሚታውቁ እስር ቤቶች ሲሆኑ በየከፍለ ጦሩና በየሻለቃው የታሰሩና የትስቃዩ በርካታ ወታደሮች እንደነበሩ ይታወቃል። የታሰሩትና የተባረሩት ከኮነኔል አንስቶ እስክ ተራ ወታደር የሚያካትት ሲሆን የተባረሩት ጄነራሎችንም ይጨምራል። ዛሬ ከመቼውም በላይ አይኑን አፍጦ የምናየው ዘረኛነት የእዚህ በዘር ላይ ያነጣጠር በሰራዊቱ ወሰጥ የተሰራ የዘር ማጽዳት ስራ ነው።
 • ይህ ዘረኛ አስራር በፖሊሱና በደህንነት ሃይሉ ውስጥ ስንመለከተው የምናገኘው ጭብጥ ከስራዊቱ የከፋ ነው።
 • የሃገሪቱ ሃብት በዘረኛ ዘረፋ ምን ያህል እንድሚዘረፍ በእዚህ ላይ ደምረን ስንመልከተው እውን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን እጀ ወይንስ በባእድ ወራሪዎች እጅ የሚያስኝ ጥያቄ የሚያስንሳ ነው
 • ይህ የማያስቆጣን ከሆነ ሌላ ምን ሊያስቆጣን ይችላል። ከዚህ በላይ የግልና የሃገር ውርደትና ሞት ይኖራል ወይ?