የወያኔ ሰራዊት ዘረኛ አመራር የተዘፈቀበት አሳፋሪ የንቅዘት ደረጃ

ሰኔ 4 ቀን 2001 ዓ.ም
በግንቦት 7 ንቅናቄ የህዝብ ግንኙነት የተቀናበረ ልዩ ዝግጅት

ከጥቂት ሳምንታት በፊት የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ምን ያህል ዘረኛ በሆነ መንገድ የተደራጀ እንድሆነ የሚያሳይ መረጃ አቅርበናል። ይህ መረጃ የሃገሪቱ መከላከያ ሃይል በሙሉ በጥቂት የትግራይ መኮንኖች ቁጥጥር ስር መዋሉን ያሳያል። በእዚህ ጽሁፍ የምናቀርብላችሁ መረጃ ደግሞ ወያኔ በወታደራዊ ተቅዋማቱ ውስጥ ይሁን እንዲሁም በሌሎች አስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካዳሚያዊና ሌሎች ተቅዋማት ውስጥ ለምን ዘረኛ አደረጃጀትና አሰራር ለማስፋፋት እንደፈለገ የሚያሳይ ይሆናል። ቀና አመለካከትና ጤነኛ አእመሮ ያላችውን ዜጎች በሙሉ ግራ ሲያጋባ የኖረውን ይህንን ለማንም የማይበጅ የወያኔን የዘረኛነት እብደት መረዳት የሚቻለው በእዚህ ሰነድ የቀረበውን መረጃ በሚገባ በማጤን ብቻ ነው የሚል እምነት አለን። ይህ ሰነድ መለስና በዙሪያው ያሰባሰባችው ዘረኞችና ለእነዚህ ዘረኞች በእሽክርና ለማገልግል የቆረጡ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተውጣጡ ሆድ አድሮች ለምን ይህንን አደገኛ ዘረኛ ስርኣት በሃገራችን ለመትከልና እድሜውንም ለማራዘም እንደሚጥሩና በሃገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ወንጀል በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

መለስ ዜናዊ ዘረኛና አምባገነናዊ መንግስታዊ ስርአቱን የአብዮታዊ ዴሞክራሲና የልማት መንግስት ብለን እንድንጠራለት ይፈልጋል። የመለስ ዜናዊ መንግስት ግን ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሆነ ከልማት ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። እንዳው እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይህ መለስ ዜናዊና በዙሪያው የኮለኮላችው ደናቁርት ትርጉሙን በሚገባ የማያውቁትን አብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ስርአት። ከነሁዋላቅርነቱና ከነችግሮቹ በቀጥታ በስራ ላይ አውሎት ቢሆን ኖሮ፣ ሌላው ቢቀር ሃገራችን ዛሬ ከምትገኝበት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ባልተገኘች ነበር። በዘር ፍጥጫ፣ በባህልና የሞራል ዝቅጠት፣ በተማረ የሰው ሃይልና የሃብት ፍልሰት፣ በዜጎቸ መሃል በሚታይ አሰቃቂ የሃብት መበላለጥ የሚገለጽ ከፍተኛ ችግር በሃገራችን ባልታየ ነበር።

ይህንን ለማለት ያነሳሳን መለስ ዜናዊ በሃገራችን የዘረጋውን የፖለቲካ ስርአት ቀንና ማታ አብዮታዊ ዴሞከራሲ ብሎ ስለጠራው ብቻ መለስን ለመተቸት የተነሱ የቀድሞ ጉዋደኞቹ ሆኑ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መለስ ለማጭበርበሪያነት የሚጠቀምበትን የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጩህት እንደ እውነተኛ የስርአቱ መገለጫ አድርገው ሲተቹ መታየታቸው ነው። ይህ የትችት አካሄድ መለስ ዜናዊና በዙርያው የተሰባሰቡ የትናንት ሰዎች በሃገራችን እየገነቡት ያለውን ዘረኛ ስርአት በእውነተኛ ስሙ በህዝብ እንዳይታወቅ እንቅፋት ሆንዋል።

የዚህ ጽሁፍ አላማ መለስ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በመባል የሚታወቀው የፖለቲካ ንድፈሃሳብ መለስ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ እያለ ከሚያጭበረብርበት በድንቁርና የተሞላ ትንተና ይሁን በተግባር ከሚፈጽመው ድርጊት ጋር ምንም አይነት ተያያዥነት የሌለው መሆኑን በዝርዝር ለማሳየት አይደለም። ነገር ግን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ተበሎ የሚታወቀው የፖለቲካ ንድፈ ሃሳብ በዋነኛነት ለዘረኛነት ቦታ የማይስጥ፣ ሃገራዊ አርበኛነትንና ሃገራዊ ፍቅርን መሳሪያ በማድረግ ብሄራዊ ባለሃብቱን የሃገሪቱን ከፍተኛ ምሁር ተማሪውን አስተማሪውን የፋብሪካ ሰራተኛውንና አርሶአደሩን በማስተባበር የአንድን ሃገር ኢኮኖሚያዊ ምሁራዊ የሳይንስና የምርምር አቅምን ብቃት በማሳደግ ፈጣን እድገት ለማምጣት አልሞ የተነሳ ርእዮት እንደነበር ህዝብ እንዲያውቅ ማድረግ ተገቢ ነው የሚል እምነት አልን። በተለይ የአንድ ሃገር የእርሻ፣ የእንዱስትሪና የካፒታል አቅም ከውጭ በግፍ በሚገቡ፣ ለመሰረታዊ ልማት እርባና በሌላቸው ሽቀጦች እንዳይጎዳ የሚከላከል፣ የሃገሩ ህዝብ በሃገሩ በሚመረቱ ምርቶች የመጠቀም ሃገራዊ ሃላፊነትና ኩራት እንዲሰማው የሚያደርግ እምነት አምቆ የተነሳ ርእዮት ነበር አብዮታዊ ዴሞክራሲ። በተለይ የፖለቲካና ወታደራዊ ሃይሉ የልማትና የስነምግባር ምሳሌዎች የሚሆኑበት የእነዚህ ተቅዋማት አባላት ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል አባላት ይበልጥ የግልና ጋራ መስዋእትነት የሚከፍሉበትን ሃገራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ አስገብቶ የተነሳ የፖለቲካ ርእዮት ነበር።

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ወይም በሌላ መጠሪያው ብሄራዊ አብዮት በመባል የሚታወቀውን የፖለቲካ ርእዮት በስራ ላይ ለማዋል ተነስተው ከነበሩ ቻይናን በመሰሉ ሃገሮች የተሞከረው ይህ ነበር። ተሳክትዋል አልተሳካም የሚለው ነጥብ ሌላ ጉዳይ ሲሆን፣ ይህንን ሙከራ መለሰ ዜናዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲ እያለ ሲያናፋብን ከሚውለው ጩህት ጋር በአንዲት ነጥብ እንክዋን የሚመሳሰልበት ነገር ማግኘት እንደማይቻል ግልጽ ያደርጋል።

ስለዚህም ነው በዘረኛነት፣ በሃገራዊ ጥላቻን፣ የባእድ የሆነን ነገር በሙሉ በአምላኪነትን፣ በጸረ ምሁርነትን፣ ይሉኝታ በሌለው መንገድ ሃገራዊ ሃብትን በዘረኛነት ለተብዋደኑ ብድኖች በሙስና በማከፋፈል፣ የሃገር ሃብት ከሃገር እንዲሸሽ በማድረግ፣ በሃገር ውስጥም የሃገር ሃብት ለጥቂት ዘረኞች ገድብ የሌለው የቅንጦት ኑሮ ማኖሪያ በማድርግ እራሱን የሚገልጸው የመለስ አገዛዝ ሊጠራ የሚገባው መለስ በመረጠው አብዮታዊ የልማት መንግስት ስም ሳይሆን ዘረኛ፣ የእበት ዴሞክራሲና የንቅዘት መንግስት በሚለው እውነተኛ መጠሪያው ሊሆን ይገባዋል የምንለው።

ከእዚህ ቀጥሎ የምናቀርበው ሰነድ የመለስ ዜናዊ ዘረኛ እበታዊ ዴሞክራሲያዊ የንቅዘት መንግስት ራሱን በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የሚገልጽበትን ማስረጃ ነው።

የወያኔን የጦር  አለቆች የሙስና ደረጃ የሚያሳይ  አነስተኛ ማስረጃ

ወያኔ የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የትግራይ ተወላጆች የሆኑትን የጦር አለቆች ከፍተኛ የሆነ ሃብት እንዲያካብቱና ዘረፋ እንዲፈጽሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ከጀመረ ሰንብትዋል። ይህ ሂደት የሚከተለውን ይመስላል።

መለስ ዜናዊ በ1989 ለአ/አበባ አስተዳደርና ለመከላከያ ሚ/ር መ/ቤት ለ25 የወያኔ የጦር መኮንኖች፣ ለእያንዳንዳቸው በሽልማት በአዲስ አበባ ውስጥ 500 ካሬ ሜትር 1ኛ ደረጃ መሬት እንዲሰጣቸው ትእዛዝ አስተላለፈ። በትእዛዙ መሰረት ለሁሉም ቦሌ መድሃኔአለም ፊት ለፊት ቦታ ተሰጣቸው። መሬቱ እንዲሰጣቸው ብቻ ሳይሆን ከሙገር ስሚንቶ ፋብሪካ ቅድሚያ እንዲያገኙ፣ ስሚንቶውን የሚያጓጉዙበት መኪና መከላከያ እንዲመድብላቸው፣ ሌሎች የዶዘርና የግሬደር የግንባታ መሳሪያዎች ደግሞ የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ እንዲሸፍን ተደረገ። ሌላውን ወጭ በዘረፋ አምዋልተው ከአንድ ፎቅ አንስቶ እስከ ሰባት ፎቅ የሚደርሱ ዘመናዊ ህንጻዎች ገነቡ። በአሁኑ ሰአት እነዚህን ዘመናዊ ህንጻዎች በከፍተኛ ዋጋ አከራይተው ይገኛሉ። የእነዚህ የወያኔ የጦር መኮንኖች ስም ዝርዝር፣ የጎሳ ጀርባቸውና መለስ ዜናዊ የአዲስ አበባን ከተማ በመዝረፍ በሰጣቸው መሬት አማካይነት ያከማቹት ሃብት እንደሚቀጥለው ይቀርባል።

የወያኔ የጦር መኮንኖች የአዲስ አበባን ከተማ በመዝረፍ ያከማቹት ሃብት

ተራ/ቁ ማእረግ ስም ቦታው የሚገኝበት ወርሃዊ ኪራይ በብር የዘውግ መግለጫ
1 ሌ/ጄ ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ቦሌ 25,000 ከ4 ዓመት በፊት ትግሬ
2 ጄኔ ሳሞራ የኑስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
3 ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ቦሌ 38,000 ትግሬ
4 ሌ/ጄ ገዛኢ Aበራ ቦሌ 170.000 ትግሬ
5 ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ ቦሌ 38,000 ትግሬ
6 ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ 35,000 ትግሬ
7 ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ቦሌ 1,2 ሚሊየን መሬቱን የሽጠ አገው
8 ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት ቦሌ 2.5 ሚሊዮን መሬቱን የሽጠ ትግሬ
9 ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል ቦሌ 34,000 ትግሬ
10 ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል ቦሌ 28,000 ትግሬ
11 ሜ/ጄ አባ ዱላ ገመዳ ቦሌ 45,000 ትግሬ/ኦርሞ
12 ሜ/ጄ አለሙ አየለ ቦሌ መሬቱን በ1.7 ሚሊዮን የሸጠ አገው
13 ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ ቦሌ 28,000 ትግሬ
14 ሜ/ጄ ሃየሎም አርAያ ቦሌ ? ትግሬ
15 ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ ቦሌ 40,000 ትግሬ
16 ሜ/ጄ ባጫ ደበሌ ቦሌ 20,000 ኦሮሞ
17 ብ/ጄ ታደሰ ጋውና ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን ብር የሽጠ ትግሬ
18 ብ/ጄ ተክላይ አሽብር ቦሌ 60,000 ትግሬ
19 ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ ቦሌ 30,000 ትግሬ
20 ብ/ጄ ፓትሪስ ቦሌ 34,000 ትግሬ
21 ብ/ጄ መስፍን አማረ ቦሌ 23,000 ትግሬ
22 ብ/ጄ ምግበ ሃይለ ቦሌ 20,000 ትግሬ
23 ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ ቦሌ 22,000 ትግሬ
24 ኮ/ል ታደስ ንጉሴ ቦሌ 48,000 ትግሬ
25 ኮ/ል ጸሃየ መንጁስ ቦሌ መሬቱን 1.2 ሚሊዮን የሽጠ ትግሬ

 

ከእነዚህ የጦር አለቆች ውስጥ ባሁኑ ሰዓት በተራ ቁጥር 1, 8, እና 17 ከስርአቱ ውጭ ሲሆኑ፣ በተራ ቁጥር 14 እና 24 ያሉት ደግሞ በህይወት የሌሉ ናቸው።

ከላይ  ከተጠቀሰው  በተጨማሪ  ወያኔ  ለጦር  አለቆቹ  የሚሰጠው  ጥቅማ  ጥቅም  የሚከተለውን  ይመስላል።

  1. እነዚህ የጦር አለቆች በነጻ መሬት ወስደው ቤት በዘረፋ ከሰሩ በህዋላም በከተማው ውስጥ በመንግስት እጅ ከሚገኙ ምርጥ ቪላዎች መሃል ተመርጦ በተሰጣቸው ቤቶች ውስጥ በነጻ መኖር ቀጥለዋል።
  2. የውሃ የመብራት የስልክ ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ የወያኔ መንግስት ይከፍላል። እነዚህ ሞልቃቃና ቅምጥል የጦር አለቆች በሚኖሩበት ቪላ ውስጥ ብርዱን አልቻልንም በማለት ቤታችውን ሙሉ በሙሉ በውድ ምንጣፍ ማሽፈናቸው አልበቃ ብሉዋቸው ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሃይል ፍጆታ የሚያስፈልጋችው የኤሌትሪክ የቤት ማሞቂያ መሳሪያዎች በየክፍሉ አስገጥመዋል። ምንጣፍ ለሚጠርገው የኤሌትሪክ መጥረጊያ ሆነ ለኤሌትሪክ ማሞቂያዎቹ የሚወጣው ክፍተኛ ወጪ፣ እንዲሁም እንዳሻቸው ለሚያፈሱት ውሃ በነጻ ተገልጋዮች እንዲሆኑ ተደርገዋል። በእዚህ ላይ ነጻ የሆነውን የሞባይልና የቤት ስልክ አገልገሎት ስንጨምርው በነጻ የሚያገኙት አገልግሎት በሽዎች የሚቆጠር ብር ይደርሳል።
  3. የጦር አለቆቹ ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው፣ ከእዚህም አልፎ አባትና እናቶቻቸው ሳይቀሩ እሰከ ውጭ ሃገር ድረስ በመሄድ የሚሰጥ ነጻ ህክምና ያገኛሉ።
  4. ሁሉም የጦር አለቆች ተጨማሪ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በመቀሌ በባህር ዳር፣ አንዳንዶቹም በአ/አበባ ከተማ፣ በድጋሚ መሬት እንዲወስዱና እንዲገነቡ ተደርገዋል። ከእዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በዱከም በናዝሬትና በሌሎች ቦታዎች ለንግድና ለመኖሪያ ቤት የሚሆኑ ቦታዎች በመውሰድ ይህን መሬት በቀላሉ ለማያገኙ ሌላ የሃገሪቱ ዜጎች በከፍተኛ ዋጋ በመቸብቸብ ያካበቱት ሃብት ገደብ የሌለው ሆንዋል። ታደስ ወረደ፣ ወዲ እምቤቲ፣ ፍስሃ ኪዳነ፣ ገዛኢ አበራ የተባሉት የጦር አለቆች በዚህ ድርጊት በዋንኛነት ከሚጠቀሱት መሃል ናችው።
  5. ይህ አልብቃ ብሎ እነዚህ የጦር አለቆች በመከላከያ ሚኒስትር በተያዘ ከፍተኛ የመስተንገዶ በጀት በመጠቀም የሚኖሩትን የቅንጦት ኑሮ ለተመለከተ ሃገራችን በምን አይነት የቀን ጅቦች እንደተወረረች ለማየት የሚያስችል ይሆናል። በ1992 ዓ/ም መከላከያ ሚኒስቴረ ለመስተንግዶ ብቻ የመደበው በጀት 280,000,000 (280 ሚሊዮን) ብር ነበር። በእዚሁ በ1992 ዓ/ም የሶማሊያ ክልል አመታዊ በጀት በተመሳሳይ 280 ሚሊዮን ብር እንደነበር ስናስታውስ፣ ይህ ለጦር አለቆቹ የተመደበው በጀት ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መረዳት ይችላል የሚል እምነት አለን። በእዚህ የመስተንግዶ በጀት በመጠቀም የጦር አለቆቹ በየቀኑ ብፌ እያዘጋጁ ራሳቸውን ሲቀልቡ ከእዚህም አልፈው እንደጥንቶቹ መሳፍንት ግብር እንዲያበሉ፣ ውድ የሆኑ የውስኪ አይነቶች እንደ ውሃ እያፈሰሱ የሚኖሩበትን ሁኔታ አመቻችቶላቸዋል።
  6. በእዚህ የመስተንግዶ በጀት አማካይነት የወያኔ የጦር አለቆች ከትንሹ ሹካና ማንኪያ ጀምሮ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሶፋዎች የምግብ ጠረጴዛዎች አልጋዎችና ሌሎችም በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ታዋቂ ሃብታም ዘፋኞችና የፊልም ተዋንያኖች የሚገልገሉባቸውን የቤት ቁሳቁሶች መግዛት ችለዋል። የጦር አለቆቹ እነዚህን የቤት ቁስቁሶች በየአመቱ የመቀየር መብት ስለተሰጣችው በእዚህ መብት ስም የሚያባክኑት የህዝብ ሃብት እጅግ በርካታ ነው።
  7. እያንዳንዱ የወያኔ የጦር አለቃ ከሁለት በላይ ውድና ዘመናዊ መኪናዎች ተሰጥቶታል። እነዚህ መኪናዎች በየአመቱ በአዲስ ሞዴል መኪናዎች ይተካሉ። የወያኔ ጄኔራል አንድ መኪና ለራሱ ሌላ መኪና ለሚስቱና ለልጆቹ በመውሰድ፣ እነዚህን መኪናዎች በግላቸው ያለምንም ወጪ እንዳሻቸው ከመገልገል አልፎ የኮንትሮባንድ እቃዎች ማመላለሻ አድርገው ይገለገሉባቸዋል። የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከድሬደዋ፣ ሃረር፣ ጅጅጋ አርቲሸክና ሞያሌ በማመላለሱ ስራ ተሰማርተው ከሚገኙት መሃል ጎልተው የሚታወቁት ሌ/ጄ ታደስ ወረደ፣ ሌ/ጄ ሳረ መኮንን፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ ሙሉጌታ በርሀ፣ ሜ/ጄ አለሙ አየለና ሌሎችም በርካታዎች ናቸው። በሌላ መንገድም የተሰጣቸውን መኪና፣ ከመንግስት ያለምንም ገደብ ከሚወስዱት ነጻ ነዳጅ ጋር እያከራዩ የሚጠቀሙ ጄነራሎች ብዙ ናቸው። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት በርካታዎች መሃል ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብርን መጥቀስ ይቻላል። የመከላከያ ሚኒስቴር በ1993 አ/ም ብቻ በአንድ ግዜ ለመለስ የጦር አለቆች መገልገያ የሚሆኑ 300 ኮብራ ቶዮታ ላንድ ክሩዘር አስገብተዋል። ኢትዮጵያን በመሰለ ደሃ ሃገር ውስጥ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በአንድ ግዜ ብቻ ይህንን ያህል የውጭ ምንዛሪ ሲባክን አይቶ የማይደነግጥ ሃገር ወዳድ ዜጋ ይኖራል የሚል እምነት የለንም።
  8. ከእዚህ በተጨማሪ በመከላከያ ስር ያሉ ወታደራዊ መደቦችና ክበቦች የወያኔ የጦር አለቆች የግል ንብረቶችና መገልገያዎች እንዲሆኑ ተደርገዋል። የጎልፍ ክበብ፣ መኮንኖች ክበብ፣ ደብረዘይት የአየር ሃይል ክበብና በየክልሉ የሚገኙ ትላልቅ ክበቦችን ጨምሮ እነዚህ የጦር መኮንኖች እንዳሻችው ያለምንም ወጪ የሚሰክሩባቸውና የሚዝናኑባቸው ናቸው። ወታደራዊ መደብሮቹ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲያስግቡ የተፈቀደላቸው በመሆናቸው ማንኛውም የውስጥ እቃዎቻቸውና ድርጅታቸው በልዩ በጀት የተሙዋሉላቸው በመሆናቸው ከፍተኛ ገቢ ያላቸው አትራፊዎች ናቸው። ይህ ትርፍ፣ በየጦር ሰፈሩ የሚሸጠው ሳር፣ ዛፍ፣ አትክልት፣ ውዳቂ ብረታ ብረትና አላቂ እቃዎች፣ የሚረቡ የወተት ከብቶችና የሚደልቡ የስጋ በሬዎች በሙሉ የውያኔ የጦር አለቆች ተጨማሪ የግል ገቢዎች ምንጮች ናቸው።

ለማጠቃለል ከላይ የገለጽነው በትግራይ የወያኔ የጦር አለቆች ዘረኛ የበላይነት የተደራጀው፣ በዘረፋና በሙስና የተጨማለቀን የጦር አለቆቹ ኑሮ ምን እንደሚመስል ያቀረብነው ዘገባ በሃግራችን የተንሰራፋውን የዘረኛነትና የሙስና ባህር ስፋትና ጥልቀት ይገልጽዋል የሚል እምነት የለንም። ዘገባችን አባይን በጭልፋ ለመጨለፍ ከሚደረግ ከንቱ ሙከራ የተለየ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋልን። እንዲያው ትንሽ ለማከል ያህል ጥቂት እንበል።

በ1992 አ.ም መለስ ዜናዊ ከጽህፈት ቤቱ ባወጣው መመሪያ መሰረት ከትግሉ ገዜ ጀምሮ 20ና ከሃያ አመት በላይ ያገለገሉ በሙሉ በአዲስ አባባ የመኖርያ ቤት እንዲያገኙ መመሪያ ባስተላለፈበት

ወቅት ይህ መመሪያ ሊጠቅም የሚችለው ከተመሰረተ ረጅም እድሜ ያለውን የህውሃት አባላትን ብቻ እንደሆነ ይታወቅ ነበር። ይህ መምሪያ የታሰበለትን ኢላማ በመምታት በአንድ ገዜ በሽዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን በአዲስ አበባ ውስጥ በሲኤምሲ በላፍቶ በገርጂ በየካ አካባቢዎች የ175 ካሬ ሜትር የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ አስችሉዋቸዋል። ከእዚህ የመሬት ሽልማት ጋር ለእነዚህ ከወርቅ ለተሰሩ የመለስ ጀሌዎች እንዲሰጥ የታዘዘውን ባለ32 ግራም የወርቅ ሜዳልያ ሽልማት ማስታወስ እንወዳለን።

በምርጫ 97 ቅንጅት አዲስ አበባን ማሸነፉ በታወቀበት ሰአት ደግሞ ቦታውን ለቅንጅት ያስረክባል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የአርከበ እቁባይ አስተዳደር የቀረችውን የስልጣን ዘመኑን በመጠቀም የወያኔ አባላት በተለይ የጦር አባላቱ የአዲስ አበባ ከተማ ባለቤቶች እንዲሆኑ ከወያኔ ስራ አስፈጻሚ በተሰጠው መመሪያ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በወያኔዎች እንዲፈጸም የተደረገው የመሬት ዘረፋ እጅግ የሚሰቀጥጥ ነበር። አንዳንድ የወያኔ አባላት የሰራዊቱ አባላት ተውካዮች በመሆን ባቀረቡት የተጭበረበር ማመልከቻ መሰረት በግላቸው ለአስር ሰዎች ቤት መሰሪያ የሚሆን መሬት ወስደዋል። ይህንን ውድ የሆነ ከተማ ቦታ እየቸበቸቡ ያገኙትን ብር በውጭ ምንዛሪ መንዝረው ወደ ፈረንጅ ሃገር ባንኮች ያዘዋወሩ ወይም በውጭ ሃገር ቤትና ንብረት ያደራጁ የወያኔ የጦር አለቆችና የጦር አባላት ቁጥር በርካታ ነው።

እንዳልነው በሰራዊቱ ውስጥ የሚካሄደው በዘር ላይ የተመሰርተ ዘረፋ ተዘርዝሮ አያልቅም። እነኝህ የወያኔ የጦር መኮንኖች የገቡበትን አጠቃላይ የሞራል ዝቅጠት፣ በዘረኛ ዘራፊነታቸው ላይ ደምሮ ላጤነው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ወያኔ በሃገራችን ታሪክ ካየናቸው የትኛዎቹም መንግስታዊ ስርአቶች በሁሉም መልኩ እጅግ አስፈሪ በሆኑ ዘረኞችና ዘራፊዎች የተበከለ ስርአት መሆኑን ማየት የሚያዳግት አይሆንም።

መለስ ዜናዊ የሃገሪቱን ሰራዊት የደህንነትና የፖሊስ ተቅዋማት ስልጣን ሙሉ በሙሉ አይን አውጥቶ ያለምንም ይሉኝታ በጥቂት የትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ስር ያደረገበት ምክንያት፣ ወያኔ ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ላይ የሚያኪያሂደውን ዘረፋ ተቃውሞ የሚነሳን ማናቸውንም ሃይል ከእነዚህ የዘርና የዘረፋ ተባባሪ ወርቅ ወንድሞቹ ውጭ በታማኝነት ሊጨፈልቅ የሚችል ሃይል ሊኖር እንደማይችል ስለሚያውቅ ነው። የመለስ ዜናዊ የልማት መንግስትና በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መርህ የተገነባ ስራዊት እንግዲህ ይህንን ይመስላል።

እንግዲህ እንዲህ አይነት በንቅዘት የተሞላ ዘረኛ የሆነ አደረራጀትን የሚከተልን በአንድ ፈላጭ ቆራጭ ትእዛዝ የሚዘወርን ራሱን የሃገር መከላከያ እያለ የሚጠራን የሌቦች ስብስብ የኢትዮጵያ ህዝብ የመብቱና የጥቅሙ ቀበኛ የሆነ የውጭ ወራሪ ሃይል አድርጎ ማየቱ ይበዛበት ይሆን?

በሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ የአማራና ከሌሎችም ዘውጌ ቡድኖች የተሰባሰቡ መኮንኖችና ተራ ወታደሮች በመከላከያና በሌሎችም መንግስታዊ ተቅዋማት ውስጥ የሚያዩትን ዘረኛ የስልጣንና የዘረፋ አደረጃጀት ተቃውመው ቢነሱ የሚያስደንቅ ይሆን?

የግንቦት 7 ንቅናቄ የኢትዮጵያን ህዝብና ለራሳቸው ክብር ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ፍቅር ያላቸውን የሰራዊት አባላት በእነዚህ ዘረኛ ዘራፊዎች ተዋርደው ከሚገዙ እነዚህን ዘረኞች ለማስወገድ ቆርጠው እንዲነሱ ጥሪ ማቅርቡ የሚያስገርም ይሆን?

ዛሬ በኢትዮጵያችን የሚደረግ ትግልስ በእነዚህ ዘረኞች ፈቃድ ሊደረግ የሚችል የምርጫ መብቶች የማስከበር ትግል ነው? ወይንስ ሃገርን የማዳን የወያኔን ዘረኛ የአፓርታይድ ስርአት ከሃገራችን ለመንቀል የሚደረግ የነጻነት ትግል?

እንዲህ አይነቱን በንቅዘት የተሞላ ዘረኛ ስረአት ማጋለጥ፣ የእዚህ ዘረኛ ስርአት ዋና መሃንዲሶችና ዋና ተጠቃሚዎች ጥቂት ሆዳም የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ መለስና አሽከሮቹ ሊያሳምኑን እንደሚሞክሩት በትግራይ ህዝብ ላይ የጥላቻ ዘመቻ መክፈት ውይንስ የትግራይ ህዝብ በስሙ በሚነግዱት፣ በሚዘርፉትና በሚገድሉት ጸረ ሃገር ሃይሎች ላይ በቃኝ ብሎ እንዲነሳ ወገናዊ ጥሪ ማቅረብ?

በእዚህ ምንም አድርገን ልንደብቀው በማንችለው መረጃ በሚታየው፣ በትግራይ ህዝብ ስም መለስና ግብረ አበሮቹ በሚያራምዱት ዘረኛና የዘረፋ እምነትና ድርጊት ፊት የትግራይ ምሁራንና የመለስ ተቃዋሚዎችስ አቅዋም ምንድነው?

ለእነዚህ ጥያቄዎች በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የሚገኘው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ መልሱን ስጥትዋል። ትግላችን ሃገር የማዳን የነጻነት ትግል ነው ብልዋል። ትግላችን ለዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለበት የዜጎችና የብሄረስቦች እኩልነት የመፍጠር ትግል እንጂ የጥቂት ዘርኞች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ባርያ ለመሆን አይደለም ብለዋል። ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልስ ያልመለሱትን የጥቂቶች መልስ ለመስማት የኢትዮጵያ ህዝብ በትእግስት ይጠባበቃል። ኑ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለማናችንም፣ ለራሳቸው ለዘረኛ ዘራፊዎቹ ጭምር የማታ የማታ የማይበጅን ይህንን የዘረኞችና የዘራፊዎች ግፈኛ ስርአት እስካሁን ካደረሰው ጉዳት የበለጠ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በአንድ ላይ ተባብረን ከምድራችን እንጥረገው ይላል።