እስር ቤቱ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞችም የታሰሩበት ስፍራ እንደሆን የገለጹት ስዊዲንዊያኑ ጋዜጠኞች ክልሉ መያዝ ከሚገባው ከሁለት እጥፍ በላይ እስረኞች የታጎሩበት፣ የሚጋረፍ ወበቅ ያለበትና ሳምባ ነቀርሳን የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች ችግር የሚስተዋልበት ፍጹም ሲኦል የሆነ ቦታ እንደሆነ አብራርተዋል።
ጋዜጠኞቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ወደዚህ ሲኦል እስር ቤት ከመወርወራቸው አስቀድሞ ከፍተኛ ስቃይ ማየታቸውን ገልጸው ወንጀለኛነታቸውን ለማሳየት በሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዘደንት ዳይሬክተርነት ፊልም እዲሰሩ ከተደረጉ በኋላ ይሄንኑ ፊልም ፍርድ ቤቱ በማስረጃነት በመጠቀም በአስራ አንድ ዓመት
እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል።
በፊልሙ ቀረጻ ወቅት የሶማሌው ክልል ም/ፕሬዘደንት የተሰጣችሁን ሽብርተኛና ወንጀለኛ ነን እያሉ የሚናዘዙትን ባህሪ በደንብ አልተጫወታችሁም በማለት እንደገና እንዲለማመዱ በማድረግ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች እንዳስቀረጻቸውም ተናግረዋል።
የፍርድ ቤቱ የችሎት ሂደት ጨዋታ ነበር ያሉት ስዊዲናዊያኑ ማርቲን ሽብዬና ጆሃን ፒርሰን የወንጀለኝነቱን ብይን ፍርድ ቤቱ ከመስጠቱ ሃያ ቀናት በፊት በቴሌቪዥን የሰጠው መለስ ዜናዊ ነበር ብለዋል።