ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተፈጠረዉ ከፍተኛ የቁጠባ እጥረት ዋናዉ ምክንያት የህወሀት አባላት ንብረት የሆኑት የንግድ ባንኮች መሆናቸዉ ታወቀ

ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከህዝብ የሚቀርብበትን ከፍተኛ ተቃዉሞ አቅጣጫ ለማስቀየር ሲል ያለምንም በቂ ጥናትና ዝግጅት ከአቅሙ በላይ እዚህና እዚያ ያስቀመጣቸው ፕሮጄክቶች የአገሪቱን የካፒታል ጥሪት እንዳራቆተ በግልጽ የሚታወቅ ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚታየዉ የቁጠባ ካፒታል እጥረት በዋና ምክንያትነት ሊጠቀሱ የሚችሉት በህወሀት ባለስልጣኖች ቁጥጥር ስር የሚገኙት የግል ንግድ ባንኮች ናቸዉ ሲሉ አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ ምሁር ገለጹ።

እኚህ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያካሄዱት የኤኮኖሚክስ ምሁር ለግንቦት ሰባት ድምጽ በላኩት ጥናታዊ ጽሁፍ የወያኔ አገዛዝ ዉስጥ ዉስጡን የሚከተለዉ የገንዘብ ፖሊሲ የአገሪቱ አንጋፋ ባንክ የሆነዉን የእትዮጵያን ንግድ ባንክ እንደሚጎዳና በህወሀት አበላትና በቤተሰቦቻቸዉ የተያዙትን የግል ንግድ ባንኮች እንደሚጠቅም ለማወቅ ተችሏል።ይህ ጸረ አገር የሆነ የወያኔ ፖሊሲ የአገሪቱን የቁጠባ መጠን ከዚህ ቀደም ታይቶ ወደማይታወቅ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ማድረሱን እኚሁ አገር ወዳድ ምሁር የላኩልን ጥናታዊ መረጃ በግልጽ ያሳያል።

በቅርቡ አለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባወጣዉ መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ የህዝብም ሆነ የመንግስት ቁጠባ ያተኮረዉ በህዳሴዉ ግድብ ላይ ብቻ በመሆኑ አገሪቱ በካፒታል እጥረት የተነሳ ሌሎች ህዝብን የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶችን ማስጀመርም ሆነ የተጀመሩትን ማስጨረስ አቅቷታል ብሏል። ይህ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ያተኮረ የእንቨስትመንት ፖለሲ የአገሩቱ ባንኮች በተለይ አንጋፋዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገር ልማት ላይ ሊጫወት የሚችለዉን ትልቅ ሚና አሳንሶታል ሲሉ በዙ በግል ንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች በማጉረምረም ላይ መሆናቸዉ ታዉቋል።

በአጠቃላይ የወያኔ አገዘዝ እየተከተለ ያለዉ የገንዝብና የልማት ፖሊሲ የአገር ዉስጥ ባንኮችን የቁጠባ መጠን እጅግ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ አድርሶታል። ይህንን አገዛዙ እራሱ ሆን ብሎ የፈጠረዉን አደገኛ አዝማሚያ ለማስተካከል መንግስት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ተጽዕኖ ማድረግ መጀመሩንና ጅምሩ የባንኩን ባለስልጣኖችና ሠራተኖች እያበሳጨ መሆኑን የአገር ዉስጥ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

በዚህ መንግስት በቀየሰዉ የማስተካከያ ፖሊሲ መሠረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህብረተሰቡ ዉስጥ እየገባ ከእጅ ወደ አፍ የሚኖረዉን ገበሬና ሠራተኛ የቁጠባ መጠናችሁን ጨምሩ እያለ ማስጨነቅ መጀመሩን ከብዙ የአገሪቱ የገጠር አካባቢዎች የሚደርሱን ዜናዎች ያስረዳሉ። በተለይ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ በደረሱን ዜናዎች መሠረት ይህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ያተኮረዉ ህብረተሰቡን የማስጨነቅ ስራ በወያኔ ባለኃብቶች ቁጥጥር ስር የሚገኙትን የንግድ ባንኮች እንደማይመለከት ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በህወሀት ባለስልጣኖችና በቤተሰቦቻቸዉ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ባንኮች ወያኔ የፈጠረላቸዉን መንገድ በመጠቀም ከብሔራዊ ባንክና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብዛት ያለዉ ገንዘብ ተበድረዉ የዉጭ ምንዛሪ በመግዛት በቅርቡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተፈጠረዉ የዉጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ሆነዋል። በቅርቡ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለፓርላማዉ በሰጠዉ መግለጫ የዉጭ ምንዛሪ ችግር የለብንም ብሎ የጌቶቹን ዝረፊያ ለመደበቅ ቢሞክርም የወያኔ ባንኮች የሚሰሩት ስራ በእንድ በኩል የአገሪቱን የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ከፍተኛ አደጋ ላይ የጣለዉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የአገሪቱን የብድር ካፒታል ልማታዊ ላልሆነ ስራ በመጠቀም የአገር ዉስጥ ባለኃብቶችን እንቅስቃሴ ያደከመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።