አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በነጻነት የሔልማን ሃሜት የመናገር ሽልማት አሸናፊዎች ሆኑ

ከኒውዮርክ ይወታ ዘገባ እንደሚያመለክተው አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች የ2012 ን በነጻነት የመናገር ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ይህን ሽልማትም ያገኑት በዓለማችን የመናገር ነጻነት ተረግጦና ታፍኖ በሚገኝባት ኢትዮጵያ በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብት ለመጠቀም ያደረጉትን ጽናትና ርምጃ ከግምንት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ተሸላሚዎቹ ታዋቂዎቹና በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ  የጭካኔ ርምጃ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ርእዮት ዓለሙ፣ እንዲሁም የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየና እንዲሁም የአዲስ ነገር ኦን ላይኑ መስፍን ነጋሽ መሆናቸው ታውቋል። እነኝህ አራት ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ለዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማት የበቁት ከ 19 ሃገራት መካከል ከ41 ጋዜጠኞች ጋር ተወዳድረው ባገኙት ብልጫ መሆኑ ታውቋል።

አራቱም ተሸላሚ ጋዜተኞች በግፈኘአው የወያኔ አገዛዝ አሻንጉሊት ፍርድ ቤት ሽብርተኞች ናችሁ ተብለው የተከሰሱ መሆኑ በስፋት ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህን ሽልማት ለነኝህ ታዋቂ ጋዜጠኞች የሸለመው ተቋም ጋዜጠኞቹ ሽብርተኛ ሳይሆኑ በኢትዮጵያ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብጥ አፈኛኝ ጠቁመውኛ ጠጋፍተው የሚጭሉጥኝ ሑሉ ያደረጉ ኛጨው ብሏጨዋል።

ሄልማን ሃሜትስ በሁለት ታዋቂ አሜሪካዊያን ጋዜተኞች ስም የተሰየመ ተቋም ሲሆን በሂዩማን ራይትስ ዋች ስር የምኒተዳደርና በየዓመቱም በየሃገሮቻቸው ሃሳብን በነጻነት በመግለጽ ትግል ታዋቂ የሆኑ ጋዜጠኞችን በመምረጥ የሚሸልምና የሚያበረታታ ተቋም ነው።