መደማመጥና መነጋገር ከቻልን የማንፈታቸው ልዩነቶች የሉም!!!

አገራችን እና ሕዝቧ በአንድ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መዳፍ ውስጥ ናቸው። በአገራችን የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የግለሰብም ሆነ የቡድን መብቶቻቸው ተረግጠው በባርነት እየተገዙ፤ ጉልበታቸውና ሃብታቸው እየተመዘበረ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምገኝ ዜጎችና ማኅበረሰቦች ሁሉ እጣ ፈንታችን ተሳስሯል። ሁላችንም ነፃ ካልወጣን በስተቀር ማናችንም በተናጠል የነፃነት አየር መተንፈስ አይቻለንም። ስለሆነም ለራሳችን የግልም የሆነ የቡድን ጥቅም ስንል እያንዳንዳችን ስለሁላችን ማሰብና መጨነቅ ግዴታችን ነው። read more

ጠላት ጆሮው እየሰማ ዓይኑም እያየ ለክብራችን በአንድነት ጸንተን እንቆማለን!!!

ህወሃት ልዩነቶቻችንን አብዝቶና አርብቶ ክብራችንን አዋርዶ ረግጦ ሊገዛን ዘመኑን ሙሉ ሠርቷል። ለብዙ ግዜም አንዱን ህዝብ የአንዱ ጠላት አድርጎ ሲሰብክ ኑሯል። ይህንንም እውነት ለማስመሰል በበደኖ ፤በአርባ ጉጉ፤ በሃረርጌና በሌሎች ሥፍራዎች የብዙ ንጹሃን ዜጎችን ደም አፍስሶ ለርካሽ ፖለቲካ ፍጆታ አውሎታል። በደኖ ላይ አፈር ገፍቶ ይኖር የነበረ አማራ የተባለ ዘር የተጨፈጨፈው በህወሃት ፊታውራሪነት ነው። በአርባ ጉጉ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ሰቆቃ አዛዥና አስፈጻሚው read more

በምእራብ ጎጃም ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሁለት ፖሊሶችና አንድ ሌላ ጄሌ መቁሰላቸው ተዘገበ

በአማራ ክልል ሥር በሚገኘው የምዕራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ ሁለት የወያኔ ሹሞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ ጄሌ ባለስልጣን ከፉኛ መቁሰላቸውን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከስፍራው በላከልን ዜና ገለጸ።

እንደዘጋቢያችን ሪፖርት ባለፈው ረቡዕ ጥር 2 ቀን ለወያኔ በጄሌነት አድረው ህዝባቸውንና አገራቸውን በመበደል ላይ የሚገኙት የወረዳው ባለስልጣናት የጨረቃ ቤቶችን ለማፍረስ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ፣ ህዝቡ ቤታችንን አታፈርሱም በማለት አጥብቆ ተቃውሞ ነበር። read more

በአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚያደርጉትን አድማ እንደቀጠሉ ነው። በነቄምት ዩኒቨርሲት 2 ተማሪዎች መገደላቸው ተዘገበ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን ኢሳት እንደዘገበው ከሳምንት በፊት የተጀመረው የአወሊያ ኮሌጅ ተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የወያኔ የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተው የኮሌጁን ግቢ ዘግተው ተቀምጠዋል።

መንግሥት ተብዬው አገዛዝ ያሰማራቸው የኮሌጁ ባለሥልጣናት አለአግባብ የትምህርት ይዘቱን read more

በዘረኛው መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ በሽብርተንነት የ11 አመት እስር የተፈረደባቸው የስዊድን ጋዜጠኞች ጉዳይ አለም አቀፍ ትክረት መሳቡን ቀጥሎአል

ሥልጣንን በሃይል የሙጥኝ ብለው የአገራቸውን ሃብትና ንብረት ሲቦጠቡጡ በኖሩት የሰሜን አፍርካና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አምባገነን መሪዎች ላይ የደረሰው ህዝባዊ ቁጣ ያስደነበረው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ፤ የመረጃ ፍሰትን ለመገደብ በሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ በደመ ነፍስ የወሰደ የድንጋጤ እርምጃ አገዛዙን በመላው አለም ይበልጥ እያጋለጠው እንደሚገኝ ጉዳዩን የተከታተለው የዝግጅት ክፍል ባልደረባችን ገለጸ። read more

ወያኔ በአፋር ህዝብ ላይ እያደረሰ ላለው አፈናና ሰቆቃ ዋጋ ይከፍላል ሲል የአፋር ህዝብ ፓርቲ መግለጫ አወጣ

ወያኔ በአፋር ክልል እየፈጸመ ያለው አፈናና ሰቆቃ እየተባባሰ መሆኑን በመግለጽ ከትናንትና ወዲያ ማክሰኞ መግለጫ ያወጣው የአፋር ህዝብ ፓርቲ፤ አባቃላ እየተባለ በሚጠራው የማጎሪያ ካምፕ ውስጥ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ዘመዶች እና አገዛዙን የሚቃሙ አፋሮች በብዛት እየታጎሩ ነው ብሎአል። read more

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ፣ የሚደነቅ ነው ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ መናገራቸው ተዘገበ

የቀድሞው የኦሮሞ ፌደራሊስት መስራችና ሊቀመንበር እንዲሁም አሁን የንቅናቄው የክብር ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በጄኔራል ከማል ገልቹ የተመራው ኦነግ የወሰደው እርምጃ የኦሮሞ ህዝብ ያለበትን ስቃይና መከራ ለመቅረፍ ወደፊት አንድ እርምጃ የሚያስከድ ነው በማለት እንደሚያደንቁት መናገራቸውን ኢሳት ዘገበ። read more

በጋምቤላ ክልል በአኙዋኮች ላይ ለተፈጸመው ዕልቂት ተጠያቂ ከሆኑኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስ ዜናዊም እኩል ተጠያቂ ይሆናል ሲል የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ፕሬዝደንት መግለጹ ተዘገበ

የህወሃት ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ ለጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንትነት ሥልጣን የበቃው ኦሞት ኦባንግ አሎም ከ8 አመት በፊት በጋምቤላ ለተፈጸመው የአኝዋኮች ጭፍጨፋ በሃላፊነት ተጠያቂ ሆኘ “እኔ ከታሰርኩ መለስም ይታሰራል” በማለት በከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ፊት መናገሩን soldiarity movemnet for new Ethiopia ወይም በአማሪኛ አጠራሩ ለአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተባለው ድርጅት ድህረገጽ ላይ የወጣ ዘገባ አስታወቀ። read more

አሸባሪው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ -ክርስቲያን ህንፃዎች ህገ-ወጥ ናቸው በማለት ማፍረሱ ተቃውሞን አስከተለ

ለበርካታ አመታት በተለያዩ ጊዚያቶች ሆን ብሎ የንግድ ቦታዎችን በማቃጠል ነዋሪዎችን ሲያፈናቅልና ለችግር ሲዳርግ የቆየው አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ፊቱን ወደሃይማኖት ተቁአማት በማዞር ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ -ክርስቲያን ህንፃዎች ህገ-ወጥ ናቸው በማለት ማፍረሱን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ። read more

“የመጨረሻ መሮኛል፣ መሮኛል፣ መሮኛል!!!” በኤምሬት የምትገኝ እህታችን የቁጭትና እልህ ለቅሶ

በደረሰባቸው በደል የተቆጡ በአረብ አገራት የሚገኙ እህቶቻችን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ምሬታቸውና ቁጭታቸውን እየገለጹ ነው። በቅርቡ በአባይ ግድብ ሰበብ የእነዚህ ምስኪን ኢትዮጵያዊያንን የድካም ውጤት ለመዝረፍ ወደ አረብ ኤምሬት ያመራው የዘረኛው መለስ ዜናዊ አገዛዝ ልዑካን ቡድን ያልጠበቀው የቁጣ ናዳ ወርዶበታል።

የአንድ ሥርዓት ምንነት በገሃድ ከሚገልጹ ነገሮች አንዱ የሴቶች መብት አያያዝ ነው። ለሴቶች ከበሬታ read more

ሃሰትን እንድናገር ያስገደደኝ መንግስት ነው ማለት አያዋጣም!!!

በዘረኛው ቡድን አማካኝነት የአገራችን የሞራል እሴቶች ሆን ተብለው እየተዋረዱ ነው።ድሮ ድሮ “እውነትን ተናግሮ ከመሸበት ማደር” የሚባል መልካም አባባል ነበረን። ዛሬ ይህን የመሰሉ አባባሎች ከል እንዲለብሱ በመደረጉ እውነትን  የሚናገር በግዞት ተይዞ የመከራ እንጀራ ይበላል የመከራ ውሃም ይጠጣል። read more

በጀኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደውን አቋም በመደገፍ ግንቦት7ና ጥምረት መግለጫ አወጡ

በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጥላ ሥር ከሌሎች የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑን ገሃድ ማድረጉን ተከትሎ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከትናንትና በስቲያ መግለጫ አውጥቶአል።

“የጋራ ትግል የጋራ አገር” በሚል ርዕስ ግንቦት7 ባወጣው በዚህ መግለጫ “በኢትዮጵያ የሰፈነውን ዘረኛ አምባገነን ሥርዓት አስወግደን በምትኩ የግልና የወል መብቶች የተከበሩባት፤ ፍትህና እኩልነት የሰፈኑባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር በምናደርገው ትግል ውስጥ በጀኔራል ከማል ገልቹ read more

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ደንበኞቻቸው ከ200 ሺ ወይም ከ10 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ሲያስገቡም ሆነ ሲያስወጡ ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የመረጃ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዙ

የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን በፍርሃት ለማሸምቀቅ ተብሎ በዘረኛው መለስ ዜናዊ የተቋቋመው የጸረ ሽብር የመረጃ መእከል የተባለው መሥሪያቤት ለግልና ለመንግስት ባንኮች ባወረደው መመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ አገር ዜጋ ከ200 ሺ ብር ጀምሮ በባንኮች ለማስቀመጥ ወይም ለማውጣት በሚሄድበት ጊዜ፣ ባንኮች የግለሰቦችን ስምና ማንነት ለብሄራዊ የጸረ ሽብር የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማእከል ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። read more

ወያኔ አኬልዳማ በሚል ርዕስ ያስተላለፈው ድራማ ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከፕሬሶች ጋር በተገባው እልክ መሆኑን በረከት ስምኦን ለፓርላማ ተናገረ። አብዛኛው ህዝብ-ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዓመታዊ ግብር አልከፍልም ማለቱንም በረከት አልሸሸገም

የወያኔ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆነው በረከት ስምኦን ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ተብየው የካድሬዎች ምክርቤት ሪፖርት ሲያቀርብ እንደተናገረው በሽብርተኝነት ተከሰው ፍርድቤት እየተመላለሱ ካሉ ዜጎች ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ፓርቲዎችና የተቃዋሚነት ሚና ያላቸው ፕሬሶች፤ መንግስት አለአግባብ እሥር እየፈፀመ መሆኑን በመጥቀስ” ሰዎቹ ነፃ ናቸው” በሚል ብይን መስጠት በመጀመራቸው፤ በኀብረተሰቡ ውስጥ ‘‘ሰዎቹ ለምን ታሰሩ?’’ የሚል ጥያቄ በመፈጠሩ የተነሳ read more

የገናን በአል ምክንያት በማድረግ የእርድ እንስሳት ዋጋ እንደጨመረ ተዘገበ

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዥን ኢሳት እንደዘገበው የገናን በአል ተከትሎ የእርድ እንስሳት ዋጋና በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የእርድ ከብት ከ12 ሺ ብር ጀምሮ በመሸጥ ላይ ነው።

በአዲስ አበባ ዶሮ ከ170 እስከ 200 ብር፣ በግ ከ1200 ብር እስከ 1700 ብር፣ ፍየል ከ1000 እስከ 1800 ብር በመሸት ላይ ነው። ቅቤ በኪሎ በአማካኝ 130 ብር ዘይት 24 ብር ፣ አንድ ኪሎ ስጋ ደግሞ 90 ብር እየተሸጠ ነው። ስኳር በኪሎ 14፣ ሽሮ ደግሞ 26 ብር በመሸጥ ላይ ነው። read more

Page 1 of 7212345»102030...Last »
© 2008-2012