ወያኔ በድንገት የብርን የምንዛሬ ምጣኔ በ20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ ቀድሞ በ13.62 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር በብር 16.35 እንዲመነዘር አዟል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንደ ወታደራዊ ተቋም በትዕዛዝ የሚመራ በመሆኑ ለምንዛሪው ምክንያት መጠየቅ ያለበት መለስ ዜናዊ እንጂ የባንኩ ገዢ ወይም “ቦርድ” የተባለው ስብስብ አይደለም። የባንኩ ገዢም ሆነ ቦርዱ አስፈፃሚዎች እንጂ ወሳኞች አይደሉም። የገንዘብንም የበጀትንም [...]
የአፋር ሕዝብ ፓርቲ፣ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነትና የፍትህ ንቅናቄ ተቀናጅተው “ጥምረት ለነፃነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ በኢትዮጵያን” መፍጠራቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ አብስረዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዚህ ጥምረት መሥራች አባል በመሆኑ የተሰማውን ደስታ በድጋሚ ይገልፃል።
አንድን ነገር ደጋግሞ እየሠራ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ አዕምሮው በትክክል የማይሠራ ሰው ብቻ ነው ይባላል። ወያኔ አዕምሮዓቸው በትክክል መሥራት በማይችል ሰዎች የተሞላ ድርጅት መሆኑ ድርጊቱ ይመሰክራል። ባለፉት አምሳ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሲደረግ የቆየው በባዶ ቁጥሮች በተነፋ እቅድ የመኩራራትን “ስልት” ዛሬ እነ ግርማ ብሩ እንደ አዲስ ጥበብ ያስተዋውቁን ይዘዋል። የወያኔ የሰሞኑ ማደንቆሪያ “አዲሱ” የአምስት ዓመት እቅድ [...]
ሰሞኑን መለስ ዜናዊ ስለልዩ ልዩ ጉዳዮች በቀባጠረበት ጋዜጣዊ መግለጫ ከግንቦት 7 ጋር ሊኖር ስለሚችል ድርድርም ጥቂት ዓረፍተ ነገሮችን ተናግሯል። መለስ እንዲህ ጊዜ እየጠበቀ በሚወረውራቸው ዓረፍተ ነገሮች አዲስ አጀንዳ እየሰጠ ኢትዮጵያዊያንን ከትግል ማዘናጋት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ተጠቅሞበት ውጤታማ የሆነበት ስልት እንደሆነ እናውቃለን። አሁንም ይህንን ሲወረውር ተመሳሳይ ውጤት እንደሚያስገኝለት
የወያኔ ዘረኝነት፣ ትምክህት እና የስሌት ስህተት እርስበርስ የሚመጋገቡ ናቸው። ትዕቢቱ “ስህተቱን” ግዙፍ ሲያደርገው፤ ዘረኝነቱ ደግሞ “ስህተቱን” አስነዋሪና አሳፋሪ ያደርገዋል። በዘረኝነትና ትዕቢት ከተነዱ በርካታ ስህተቶች አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።
ወያኔ ለእኩልነት ታገልኩ ብሎ ለዘረኝነት ተቋማዊ መሠረት ሰጠ። ማንም እንደሚገነዘበው ለእኩልነት በመታገል እና ዘረኝነት በማስፈን መካከል ያለውን ልዩነት የትየለሌ ነው። ይህም በመሆኑ “እኩልነትን አሰፈንኩ” ባለበት አገር [...]
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን (ኢሳት) በሚመለከት ሰሞኑ አዲስ አበባን ያዳረሰው ጭውውት የሚከተለውን ይመስላል።
“ዳዊት ጎልያድን ገደለ!”
“በምን?”
“በወንጭፍ!”
“ኢሳት ኢቲቪን ከሳተላይት አወረደ !”
“በምን?”
“ገና ባልታየው ችሎታው”
ይህ ጭውውት እንደ እረኛ ዘፈን ምስጢሮችንና ሕዝባዊ መልዕክቶችን ይዟል።
ትምህርት የእውቀት አድማስን ካላሰፋ፤ አዳዲስ ክህሎቶችን ካላሳወቀ፤ የእለት ከእለት ኑሮን ካላሻሻለ እና አዎንታዊ የባህርይ ለውጥ ካላመጣ ፋይዳው እምን ላይ ነው?
የወያኔ የትምህርት ሥርዓት ከላይ ከዘረዘርናቸው ውስጥ ለአንዱም የተዘጋጀ አይደለም። ወያኔ ትምህርት ቤቶችንና ዩኒቨርስቲዎችን ከእውቀትን መገበያያነት ይልቅ እጅግ ኋላቀር የሆነ ዘረኛና ጎጠኛ አስተሳሰብ ማራቢያና ማሰራጫ ተቋማት አድርጎዓቸዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም. በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በደረሰው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ፤ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል። ግንቦት 7 በዚህ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን የኡጋንዳና የሌሎች አገራት ዜጎችም ሃዘን ይጋራል።
በአገዛዞች ተወዳጅ የሆኑት ጉልበት፣ ትዕቢትና ጉራ በተገዢዎች ልብ ውስጥ ፍርሃትን ብቻ ሳይሆን ቂምና የአመፃ ስሜትንም መትከላቸው ፈጽሞ የማይቀር ነገር ነው። በዚህም ምክንያት አገዛዞች ጉልበትንና ትዕቢትን ከማባበልና መደለል ጋር ቀላቅለው ያቀርባሉ። ይህ አገር በቀል አምባገነኖችም ሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ቅኝ ገዢዎች ሲጠቀሙበት የኖረ ዘዴ ነው። ፈረንጆች ይህን ዘዴ “ዱላና ካሮት” ብለው ይጠሩታል። ይህ መሰሪ [...]
ለመሆኑ ወያኔ አስመዘገብኩ ስለሚላቸው ስኬቶች ዓለም ዓቀፍ ገምጋሚዎች ምን ይላሉ? ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነትያላቸው ሶስት ዋና ዋና የስኬት ወይም የውድቀት መለኪያች ላይ እናተኩራለን።
1. የጨነገፉ መንግሥታት መለኪያ
ይህ መለኪያ በዓለም ያሉ የ177 አገሮች መንግሥታት ሕዝባቸውን በመምራት ረገድ ያሉባቸውን ድክመቶች በአስር ዋና ዋና መመዘኛዎች ይለካል።
እነዚህም
ፈጣን የሕዝብ ብዛት የሚፈጥረው ውጥረት፣
የሕዝብ ከመኖሪያ ቦታው መፈናቀል፣
የቡድኖች (የማኅበረሰብ) በሥርዓቱ መማረር፣
በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጥናትና ምርምር ኮሚቴ የተዘጋጀ: ሐምሌ 2002
1. መግቢያ
ስለ መተባበር ጠቀሜታ በመዘርዘር ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም። በአገራችን ለዘመናት የተንሰራፋው የግፍ አገዛዝ ያፋፋቸው እና እኛንም በዓለም ፊት እያዋረዱን ያሉት ድህነት፣ ችጋር፣ በሽታና ማይምነት ከመቸውም በላይ ህልውናችንን እመፈታተን ደረጃ ላይ የደረሱት ችግሮቻችንን ለመቋቋም ተባብረን መቆም ባለመቻላችን እንደሆነ አከራካሪ ጉዳይ አይመስለንም። እነዚህን ችግሮች ተባብረን ለማስወገድ [...]
የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች በአንድ ድምፅ ወያኔን “አፈርንብህ” እያሉት ነው። ምዕራባዊያን በተለይም መንግሥታቱ በወያኔ ላይ የተወሰነ ተስፋ ነበራቸው። ከመለስ በርካታ ምላሶች አንዱ በዚህ ተግባር ሰልጥኗልና ለዘመናት በጮሌነት ሲያታልላቸው ኖሯል። ዘንድሮ – በ2002 ዓ.ም. በምርጫ ስም ተፈጽሞ በዓይናቸው ያዩት ነገር በጆሮዓቸው ሲሰሙት የቆየውን ፈጽሞ አይስልም። በዚህም ምክንያት ምዕራባዊያን ሚዲያዎች በወያኔ ላይ የተሰማቸውን እፍረት በዝርዝር እየነገሩን ነው። ባለፉት [...]
መረጃ ኃይል ነው። መረጃ እውቀትና ሃብትም ጭምር ነው። በሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ለልማት ከሚያስፈልጉ ግብዓቶች መረጃ ቀዳሚው ሥፍራ ይዟል። መረጃን አፍኖ ትምህርትን፣ የጤና አገልግሎትን፣ ንግድን እና ሌሎችን የልማት ሥራዎችን በጥራት ማሳደግ አይቻልም። መረጃን አፍኖ መልካም አስተዳደርና ፍትህን ማስፍን የዜጎችን ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶችን ማስከበር የማይታሰብ ነው።
በደቡብ አፍሪቃ በመካሄድ ላይ ያለው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ በአገራችን የእግር ኳስ መሠረታዊ ችግሮች ላይ እንድናተኩር እድል ሰጥቶናል። ኢትዮጵያ በወጣቶች የተገነባች እና ከፍተኛ የሆነ የእግር ኳስ ፍቅር ያለባት አገር ናት። በትላልቅ የእግር ኳስ ሜዳዎችና ግጥሚያዎች ኢትዮጵያዊያንንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለማየት ግን አልታደልንም። አገራችን እንኳንስ በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ልትወዳደር ቀርቶ ራሷ ካስጀመረችው የአፍሪካ እግር ኳስ [...]
ሽምግልና ተዋረደ!!! ራሳቸውን “የሃገር ሽማግሌ” ብለው በሚጠሩ የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች ምክንያት ሽምግልና ረከሰ!!! ሽምግልና በደልን ማርዘሚያ ሆነ!!!
ሽምግልና አያት፣ ቅድመ-አያቶቻችን አዳብረው ያቆዩልን እጅግ የተከበረ ማኅበራዊ ተቋም ነው። ሽምግልና ተደጋግፎ ለመኖር፤ ግጭቶችን ለመቀነስ እና ፍቅርን ለማብዛት ማኅበረሰባችን በብዙ ምዕተ ዓመታት ልምድ ያዳበረውና ሞገስን የቸረው በየጊዜውም እያሻሻለው የሚሄድ ማኅበራዊ እሴት ነው።