Archive for the ‘የዜና ትንታኔ’ Category

‘’የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ’’

“በአይኑ ምሰሶ ይዞ ከሌላው አይን ጉድፍ ላውጣ ይላል”፤ “አመድ በዱቄት ይስቃል”…እና የመሳሰሉት፤ አባቶቻችን ከሃይማኖት እና ከልምድ ወስደው የባህል እና ቋንቋችን አካል ያደረጓቸው አባባሎች ናቸው። ሃፍረተ-ቢስነትን እና ግብዝነትን ይገስፃሉ። በሌሎች ከመፍረዳችን በፊት እራሳችንን አጥርተን እንድንመለከት ይጋብዙናል።

የዘረኛው የመለስ ዜናዊ የቅንድብ ዘፋንና ሊያስተላፍ የፈለገው መልዕክት

የመለስን ቅንድብ የሚያሞጋግሰው ዘፈን ሲወጣ፣ አንዳንዶቻችን በሳቅ ሃይል ተሸንፈን የምንለውን አጥተን ዝም ስንል፣ ሌሎች በዘፋኙ ላይ ውርጅብኝ በማውረድ ተጠምደው ነበር። የዘፈኑ መውጣት ግን የድምጻዊውን አድርባይነት ከማሳየት ይልቅ ከፍ ያለ እንድምታ አለው። በተለይም በአገዛዙ ሰዎች ዘንድ ያገኘው ድጋፍ ከበድ ያለ ጉዳይ ነጸብራቅ ነው።

ዜጎች አማራጭ መረጃን የመፈለግ እና የማግኘት መሰረታዊ መብታቸው እንዲከበር

በውሸት ላይ የተመሰረቱ አገዛዞች ህልውናቸውን ለማስጠበቅ የመረጃ አውታሮችን መቆጣጠር የግድ ይላቸዋል። የመረጃ ተቀናቃኝ እንዲኖራቸው አይፈልጉም። የአንድ አካል የህልውና መሰረት ውሸት ሲሆን፤ ከዛ ውሸት ውጪ ሌላ የሚናገርን ተቋም የሚያየው እንደ አደጋ ነው። መወገድ እንዳለበት አደጋ።
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝም ታዲያ ከዚህ የተለየ አይደለም።

ዘረኛውን አገዛዝ አስወግደን ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ስርአት የመንገንባት ሂደት ልንጀምር ይገባል

ወያኔ በተደጋጋሚ የብሔረሰቦችን መብት ስለማስከበሩ እንደሚያወራ ይታወቃል። እውነታው ግን፣ የብሔረሰቦች መብት ለወያኔ ዘረኛነቱን ለመሸፈን ከሚጠቀምባቸው ጭንብሎች አንዱ ከመሆኑ ባሻገር በተግባር ያሳየው ነገር አይደለም።
በመሰረቱ ዘረኛ የሆነና ከአንድ መንደር እና ቤተሰብ የመጡ ሰዎች በአገሪቱ ላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት እንዲኖራቸው ተግቶ የሚሰራ ቡድን የብሔረሰቦችን መብት በእውነት ሊያስከብር አይችልም። ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ብቸኛ ነገሮች ህዝቡን ለማታለል የተዘጋጁ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሞትን ፈርቶ ለጨቋኞች እና ለዘራፊዎች አይንበረከክም

ከግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነፃነቱ ሲታገሉ በባዕዳን ፋሺስቶችና ዬኔ ብሎ በሚላቸዉ ጨካኝ ልጆቹ የተጨፈጨፉ አያሌ ሰማዕታት ልጆች አሉት። በ1928 ዓም በወርሃ ዬካቲት የፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች ሽማግሌ ከህፃንና ጎበዝ ከደካማ ሳይለዩ በሕይወት ቆሞ ሲሄድ ያዪትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጭካኔ በመግደል በአንድ ጀምበር ከ30ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያንን ጨፍጭፈዋል። በ1969 ዓም እና በ1997 ዓም ደግሞ ኢትዮጵያን [...]

ሁለገብ አመጽ ወይም ግዞት!

ሁለገብ አመጽ ወይም ግዞት!
መለስ ዜናዊ በምርጫ ስም ፈላጭ ቆራጭ ዘውድ-ቀረሽ ንጉስ ሆኗል፤ ለዴሞክራሲ የተጀመረው ትግል ከዚህ ወዴት?
ተስፋ በመሰረቱ ጥሩ ነገር ነው። የማይጨበጥ ተስፋ ግን አደገኛ ነው። ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ሊፈጽሟቸው የሚገባቸውን አንገብጋቢ ውሳኔዎች ከማድረግ ያግዳቸዋልና። ፍዝዝ ብለው የማይሆነውን ሲጠብቁ ቀን ይጨልማል። በዚህ ምክንያት የማይጨበጥን ተስፋ ከሞኝነት ልንቆጥረው እንችላለን። ብዙ ጊዜም ተስፋና ሞኝነት እየተወናበዱ መዘናጋት [...]

© 2008-2009