የውጭ ምንዛሪ ለውጡ እውነተኛ ምክንያቶች እና መውሰድ የሚኖርብን እርምጃዎች
ወያኔ በድንገት የብርን የምንዛሬ ምጣኔ በ20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ ቀድሞ በ13.62 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘር የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር በብር 16.35 እንዲመነዘር አዟል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንደ ወታደራዊ ተቋም በትዕዛዝ የሚመራ በመሆኑ ለምንዛሪው ምክንያት መጠየቅ ያለበት መለስ ዜናዊ እንጂ የባንኩ ገዢ ወይም “ቦርድ” የተባለው ስብስብ አይደለም። የባንኩ ገዢም ሆነ ቦርዱ አስፈፃሚዎች እንጂ ወሳኞች አይደሉም። የገንዘብንም የበጀትንም ፓሊሲዎች የሚቀርፀው ወይም እንደተመቸው የሚጫወትባቸው መለስ ዜናዊ እንደሆነ አገር ያወቀው ጉዳይ ነው። እናም መለስ ዜናዊ ይኸን ድንገተኛ የምንዛሬ ለውጥ ያደገረባቸውን እውነተኛ ምክንያቶችን ማወቅ ይጠቅማል።

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ባደረገው መጠነኛ ምርምር እና ስለወያኔ ባህርይ ካለው እውቀት በመነሳት የውጭ ምንዛሪው ለውጥ እውነተኛ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል።

ፈጣን ዘረፋ – ይህ ከፍተኛ የምንዛሪ ለውጥ ድንገተኛ የሆነው ለተራው ኢትዮጵያዊ እንጂ ለወያኔ ባለሥልጣኖች እንዳልሆነ እኛ በተጨባጭ የደረስንበት ጉዳይ ነው። የምንዛሪው ለውጥ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት በፊት ጀምሮ ወያኔ “አሜሪካ ገንዘብዋን ልትቀይር ነው” የሚል ውዥንብር በማስወራት የዋሁ ነጋዴ የያዘውን የውጭ ገንዘብ እንዲቀይር ገፋፋው። የወያኔ ባለሥልጣኖችና ተላላኪዎቻቸው ደግሞ  በጎን በስፋት ወደ ገበያ የቀረበውን የውጭ አገር ገንዘብ ሸመቱ። ግዢው ሲጠናቀቅ ትዕዛዙ ተላለፈና በአንድ ጊዜ ሃብታቸው በ20 ከመቶ እንዲያድግ ተደረገ። እንዲህ አይነት መሰሪ ተግባር በዘራፊነታቸው በታወቁ መንግሥታት ዘንድ እንኳን አስፀያፊ ተግባር ነው፤ ለወያኔ  ግን ብልህነት ነው።

“ተወዳዳሪነትን ማሳደግ” - ወያኔ ለም መሬት የመሸጥ ፉክክር ውስጥ ገብቷል። ቻይና መንግሥቷ እራሱ ነጋዴ ሆኖ መሬት እየሸመተ ነው። ህንድና ሌሎች አገራት ደግሞ የመሬት ግዢውን እንዲያጧጡፉ የየሃገራቸው ቱጃሮችን እያበረታቱ ነው። አፍቅሮተ-ንዋይ የማስተዋያ አዕምሮዓቸውን የሰለበባቸው የአፍሪቃ አገሮች ገዢዎች “ከእኔ ግዙኝ፤ ከእኔ ግዙኝ” በሚል ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። ወያኔ ለባዕዳን ለም መሬትን በሄክታር በአስር ዶላር እየሸጠ ቢሆንም ከዚህም በታች በማውረድ  “ተወዳዳሪነቱን” ከፍ ለማድረግ  ታጥቆ ተነስቷል። የቡናና የጫት የወጪ ንግድ እና የማዳበሪያና የመድሃኒት የገቢ ንግዶች በምንዛሪ ለውጥ ምክንያት እጅግም እንደማይለወጡ የታወቀ  ጉዳይ ነው። ለወያኔ በብር መርከስ ምክንያት የሚፋፋ ንግድ ያለው የመሬት ሽያጭ ብቻ ነው። እናም ወያኔ የብር ምንዛሪ በመቀነስ የኢትዮጵያን ለም መሬት በሳንቲሞች በመቸርቸር ለባህዳን አስረክቦ እማንወጣው ማጥ ውስጥ ሊያስገባን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ከድሃው ወደ ሃብታም የሚጎርፈው የሃብት ፍሰትን ማሳለጥ –  አሁን የተደረገው የምንዛሬ  ለውጥ ብዙም ጊዜም ሳይወስድ የአገር ውስጥ ዋጋዎችን ማስጨመሩ አይቀርም። በዚህም ምክንያት ለጥቂት ጊዜዓት ጋብ ብሎ የነበረው የዋጋ ግሽበት ይቀሰቀሳል። የዋጋ ግሽበት ደግሞ የወያኔ ጥብቅ ወዳጅ ነው። የዋጋ ግሽበት ድሃው የሚያጠራቅመውን ገንዘብ ስውር በሆነ  መንገድ እወያኔ ኪስ ውስጥ ይከትለታል። በዋጋ ግሽበት ምክንያት ሃብቱን በኢትዮጵያ ብር ያስቀመጠ ይከስራል፤ የኢትዮጵያ ብርን የተበደረ ደግሞ ይከብራል። በዛሬዋ ኢትዮጵያችን ውስጥ ሃብት በብር –  ለዚያው በትናንሽ ብሮች – የሚያስቀምጠው ድሃው ነጋዴና የመንግሥት ሠራተኛው ነው፤ በሚሊዮኖች የሚበደረው ደግሞ “ልማታዊ ባለሃብት” እየተባለ የሚቆላመጠው ወያኔ፣ የወያኔ ወዳጅ አልያም የወያኔ  ወገንተኛ ነው። እናም የሰሞኑ የምንዛሪ ለውጥ ሃብትን ከድሃው ሀገርተኛ  ወደ ወያኔው ሃብታም ሲያሸጋግር የነበረው የዋጋ ንረት እንዲቀሰቀስ ታስቦ የተደረገ ነው።

የትላልቅ ቁጥሮች ፍቅር – ወያኔ ትላልቅ ቁጥሮችን ይወዳል፤ ለህልውናው ያስፈልጉታልም። በውሸት የተሞሉ የቁጥር ቁልሎች የእርዳታው ምንጭ ናቸው። የብርን አንፃራዊ ዋጋ በ20 ከመቶ በመቀነስ የ15 በመቶ ዓመታዊ እድገት ህልሙን የማሳካት እቅድ አለው። ከዚህ አንፃር ሲታይ ይህ የምንዛሪ ለውጥ “የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን እቅዱ” አካል ነው። ዋጋዎች ሲጨምሩ ቁጥሮችም ይጨምራሉ። ወረቀት ላይ እስከታየ ድረስ እድሃው ማዕድ ላይ እድገቱ ባይታይም ዓለም ባንክን እምብዛም አይጨንቀውም።

እኛ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ወያኔ በኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ ላይ እንዲጨፍር እስከፈቀድንለት ድረስ እንዲህ የረቀቁ የዘረፋ ዓይነቶችን በመፈልሰፍ ማስደመሙን ይቀጥልበታል። የወያኔን የዘረፋ ጥበብን እየተከታተሉ ማጋለጥ ተገቢ ቢሆንም ዋነኛ ሥራችን መሆን ያለበት ግን በሁለገብ ትግል ወያኔን ፊት ለፊት ገጥሞ ማዳከም ብሎም ማስወገድ ነው።

ግንቦት 7 ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደገለፀው ሁሉ በውጭ አገራት የሚገኘው ኢትዮጵያዊ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ባለመሆን ብቻ እንኳን ወያኔን ማስጨነቅ ይችላል። የወያኔ ማባበያዎችን ተቀብለው ሃብታቸውን ወደ ኢትዮጵያ ያሻገሩ ወገኖች ዛሬ አባብለው በወሰዷቸው ሰዎች ተንኮል የንብረታቸው 20 በመቶ ማሙቷል። ይህ የምንዛሪ ለውጥ የመጨረሻው እንዳማይሆን ከወዲሁ ማስጠንቀቅ እንወዳለን። ወያኔ ጥቅም እስካገኘበት ድረስ ደግሞ ብርን ማዳከሙን ይቀጥልበታል። ወያኔ ለራሱ ካልሆነ በስተቀር ለማንም ደንታ የለውም። ይህን ከልብ ከተረዳን ደግሞ ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ ማትኮር ይኖርብናል።

በግንቦት 7 እምነት ዘላቂው መፍትሄ በተባበረ ክንድ ወያኔን ማስወገድ ነው። ለዚህ ወሳኝ ትግል ሁላችንም በጋራ እንነሳ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ትኩረታችን በዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ስርዓት ላይ ነው
ከዝግጂት ክፍላችን

ከጥቂት አመታት ወዲህ፣ ከዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ጋር በከፍተኛ ደረጃ በጥቅም እና በሙስና የተሳሰረ መደብ በኢትዮጵያችን መነሳቱ ሲወራ ቆይቷል። በተለይ በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ በሙስና ሳይዘፈቁ እና ከወያኔ ጋር የጥቅም ትስስር ወይም የንግድ ሽርክና ሳይፈጥሩ ሃብት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር እየተመናመነ እንደሆነ ይነገራል።

የአገዛዙን የድጋፍ ወይም የሽርክና ጥያቄ ያልተቀበሉ ነጋዴዎች በተፈበረከ ክስ ወደ እስር እንዲወርዱ፣ ከንግድ ሜዳ ተገፍተው እንዲወጡ ወይም ከአገር እንዲሰደዱ ሲደረግ ቆይቷል። የተቀሩት ግን በወያኔ የተጠየቁትን በማድረግ ንግዶቻቸውን እንደያዙ ለመቀጠል ወስነዋል፤ አገዛዙን ለማጠናከርም ተግተው ሲሰሩ ተስተውለዋል።

የወያኔን አገዛዝ በግልጽ ከሚደግፉት ነጋዴዎች ውስጥ አንዱ በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆኖ የሳኡዲ ዜግነት ያለው ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ ነው። ለዚህ ጽሁፋችን መነሻ የሆነንም፥ የቀድሞ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረውና አሁን በስደት የሚገኘው አሰግድ ተፈራ ስለዚሁ ግለሰብ የተናገረው ነው። ጋዜጠኛ አሰግድ፥ “ኢትዮጵያን የሚመራት ሼክ መሃመድ ነው” ብሎናል። እኛም ይህንን ለመመርመር መረጃ ቃርሚያ ወጣን።

ሼክ መሃመድ አላሙዲ በ1997ቱ ምርጫ ወቅት ለወያኔ መቀስቀሱና፤ ዘረኛው ቡድን ዜጎችን ባስጨፈጨፈበትና የቅንጅት መሪዎችን በግፍ ወደ እስር በወረወረበት አመትም 5.5 ሚሊዮን ብር ለገዢው ቡድን በስጦታ መልክ ማበርከቱ ይታወቃል። ግለሰቡ በተለያዩ መንገዶች ለወያኔ ለሚፈጽመው ውለታም፤ በአገሪቱ ውስጥ ቁጥጥር በማይደረግበት ሁኔታ እንዳሻው እንዲነግድ ተፈቅዶለታል ይባላል።

አዲስ ነገር ኦንላይን የተባለው የመረጃ ድረ-ገጽ ከሶስት ወራት በፊት ባወጣው ዘገባ፤ አዜብ መስፍን እና ስብሃት ነጋ በህወሃት ውስጥ በሚያካሄዱት ሽኩቻ አላሙዲ ከአዜብ ጎራ መሰለፉን፤ እንዲሁም የአዜብ ጎራ የወያኔ የደህንነት ሃላፊ የሆነውን ጌታቸው አሰፋን እንደሚያካትት ውስጥ አዋቂ ምንጮቹን ጠቅሶ ገልጿል። በአዜብ እና በስብሃት ሽኩቻ ላይ ከዚህ ቀደም ባቀረብናቸው ዘገባዎች፤ አዜብ በተለያዩ ጊዜያት አሸናፊ ሆና መውጣቷን ጠቅሰናል።

ከበርካታ ወራት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ ከሼክ አላሙዲን የንግድ እንቅስቃሴዎች ጋር የተያያዙ ሙስናዎችን በሚመለከት ተደጋጋሚ ዘገባዎችን ሲያወጣ፤ የጋዜጣው ባለቤት አማረ አረጋዊ ክፉኛ ተደብድቦ እንደነበር ይታወሳል። በርካቶች ሼኩ ወይም ለሱ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ለዚህ ስራ ተጠያቂዎች እንደሆኑና፤ ይህም ግለሰቡ ያለውን ከፍተኛ ጉልበት ያሳያል ይላሉ።

ነገር ግን በህወሃት ውስጥ በሚደረገው ሽኩቻ የግለሰቡን አሰላለፍ አተኩሮ ለተመለከተ ሰው ስእሉ ግልጽ ነው። ከአዜብ ጋር የተሰለፈ በቀላሉ ጠላቶቹን ሊያንበረክክ የሚችልበትን ጉልበት ይኖረዋል። ይህንን በተመለከተ ያናገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝም፥ ግለሰቡ ለጊዜው ከዚህ አሰላለፍ የተወሰነ ጉልበት አግኝቶ እንደሆን እንጂ፣ ከወያኔ ቁጥጥር ውጪ ማንም ምንም ሊያደርግ አይችልም ብለውናል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ጦሩን ጨምሮ የመንግስት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ያለው ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ ቡድን እንደሆነ ጠንቅቀን ለምናውቀው ሁሉ ግልጽ ነው።

አዲስ ነገር ኦንላይን የሁለቱን ቡድኖች ሽኩቻ አስመልክቶ ባወጣው ዘገባ ላይ፤ ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ከሽኩቻው እንዴት እየተጠቀመ እንደሆነ አስረድቶናል። መለስ ሽኩቻው ህወሃትን እንደማይጎዳ እስከተረጋገጠ ድረስ አይኖችን ከሱ ላይ የሚያነሳ በመሆኑ ደስተኛ ነው። ሁለቱንም የደገፈ መስሎ በመቅረብም እነሱ ከስር ሲጫረሱ እሱ ከላይ ቁጭ ብሏል።

እኛ በዚህ መሰረታዊ ትርጉም በሌለው የወንበዴዎች ሽኩቻ መካከል ገብተን፤ ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ገጽታዎች መሆናቸውን እያወቅን አንዱን የወንበዴ ጎራ ከሌላው ለይተን የማሳየት ፍላጎቱ የለንም። የአዜብ ቡድንም ሆነ የስብሃት፥ የአገራችንን ደም መጥጦ ልጆቻችንን ተስፋና እድል ፈንታ ሊያሳጣ የቆመው ዘረኛ አገዛዝ ስራ አስኪያጆች እና ዋና አጋፋሪዎች ናቸው።

ሼክ አላሙዲ እንደሆነ፥ ከወያኔ ፈቃድ እና ባርኮት ውጪ ምንም ሊያደርገው የሚችለው ነገር የለም። ወንጀል ሲፈጽም እና በሙስና ሲዘፈቅ ታይቶ እንደሆነ፤ አገዛዙ ስለፈቀደለት ነው። ይህ ሰው በወያኔ ምህረት ላይ ብቻ ተመክቶ የሚንቀሳቀስ ነው። አገዛዙ ቢፈልግ፥ በሙስና፣ ግብር ባለመክፈል፣ ወይም በሆነ ወንጀል አስሮ ሊከሰው ይችላል። ያ ባይሆን እንኳ በውጭ አገር ዜግነቱ ብቻ አንስቶ ቢያሽቀነጥረው ከልካይ አይኖረውም። በዘር ላይ በተመሰረተ አመራር የሚነዳና በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ያሰለፈ ጦር ያለው ወያኔ እንጂ ሼክ አላሙዲ አይደለም።

እንግዲህ ግለሰቦች ሁሉ ወንጀል መፈጸማቸው በማስረጃ ከተረጋገጠ፣ አንድ ቀን ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ፍርድ ቤት ፊት መቆማቸው አይቀርም። ወቀሳና ሂስም ሊቀርባቸው አይገባም። ይሁን እንጂ፥ በአሁኑ ሰዓት ዋናው ችግራችን ስልጣንን በጉልበት ተቆጣጥሮ ያለው እና ሙስና እንዲስፋፋ ሆን ብሎ የሚሰራው ዘረኛና አምባገነናዊ ስርአት ነው። የኛም ትኩረት ከዚህ ስርአት ላይ እንዳይነሳ የዘወትር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የወያኔ ተለጣፊ ፓርቲ የሆነው ኦህዴድ ለሶስት ተከፈለ፤ አባ ዱላ ገመዳ ከሊቀመንበርነቱ ተነሳ
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ወይም ኦህዴድ) በመባል የሚታወቀው የወያኔ ተለጣፊ ፓርቲ ለሶስት መከፈሉና በኩማ ደመቅሳ የሚመራው ቡድን አሸናፊ ሆኖ መውጣቱ ታወቀ።

ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለግንቦት 7 ድምጽ ካደረሱት መረጃ እንደተረዳነው፥ በፓርቲው ውስጥ በኩማ ደመቅሳ እና በአባ ዱላ ገመዳ የሚመሩ ትላልቅ ቡድኖች እና በጁነዲን ሳዶ የሚመራ አነስ ያለ ጎራ ተፈጥረው ለተወሰነ ጊዜ ሲሻኮቱ ቆይተዋል። በጎራዎቹ መካከል የነበረው ልዩነት መሰረታዊ ባህሪ የሌለው እና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የጠቆመው ዘገባ፤ በተለይ በአባ ዱላ እና በኩማ ደመቅሳ የሚመሩት ቡድኖች የመለስ ዜናዊን ድጋፍ ለማግኘት ሲሯሯጡ እንደሰነበቱ እና በስተመጨረሻም የኩማ ደመቅሳ ቡድን የዘረኛውን አምባገነን ድጋፍ እንዳገኘ ለማወቅ ተችሏል።

ፓርቲው ሰሞኑን በአዳማ ባደረገው ስድሰተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም ይኸው የኩማ ደመቅሳ ቡድን በአሸናፊነት በመውጣት ሊቀመንበሩን አባ ዱላን በመሻር አለማየሁ አቶምሳን ሹሟል። አባ ዱላ ገመዳ በአሁኑ ሰዓት የኦሮምያ ክልል ፕሬዚደንትም ሲሆን፤ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ የተመረጠው ሙክታር ከድር ያንንም ቦታ ሊረከበው እንደሚችል ያለውን ግምት ዘገባው ጠቁሟል።

የደረሰን ዘገባ ጨምሮ እንደሚገልጸው፥ አባ ዱላ እና የሚመራው ቡድን በተለይ ከመሬት ሽያጭ ጋር በተያያዘ ባካበቱት ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ይገኛሉ። እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን  ዘገባ መለስ ዜናዊ የአባ ዱላን ቡድን የሚቃወም መስሎ ለመታየት እንደሚሞክርና በኦህዲድ ውስጥ የተፈጠረው የርስ በርስ ርኩቻ ውስጥ ለውስጥ እንዲባባስ ጥረት እንደሚያደርግ ይህም ኦህዲዶች አንድ የመሆን አዚማሚያ ካሳዩ ከወያኔ ጋር ያላቸው ኢፍትሃዊ የጥቅም ግንኙነት አይናቸውን እንዲገልጡ ያደርጋቸውና  በአገዛዙ ላይ የማኩረፍ ዱለታ ውስጥ ሊከታቸው ይችላል ከሚል ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት ዘረኛው መለስ ዜናው በሚቀጥለው የሚንስትሮች ሹመት አባ ዱላ ገመዳን በአዲሱ ለገሰ ምትክ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነት አጭቶታል የሚል ተባራሪ ወሬ በቤተመንግሥት ዙሪያ እየተነዛ መሆኑን እንደማስረጃነት ያቀርባሉ።  በዚሁ የኦህዴድ ስብሰባ ላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሃላፊ ጁነዲን ሳዶ እና የቀድሞ የፓርላማ የወያኔ አገዛዝ ተጠሪ ሽፈራው ጃርሶ በማእከላዊ ኮሚቴው የነበራቸውን መቀመጫዎች አጥተዋል።

ዘገባውን ያደረሱን ውስጥ አዋቂዎች፥ የኩማ ደመቅሳ ማሸነፍ እንደተለመደው የመለስ ዜናዊን እድሜ ከማራዘም ውጪ ለኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር የሚያበረክተው እንደሌለ፤ በድርጅቱ ውስጥ እንደፈለገው የሚወስነው እና የድርጅቱ ራስ እና ጉልበት መለስ ዜናዊ እንደሆነ የኦሮሞ ህዝብ ሊረሳ አይገባም ብለዋል።

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በማይደግፉት ዜጎች ላይ የሚያካሄደውን ዘርፈ ብዙ ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል
በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት ወይም ደጋፊዎች የሆኑ፤ እንዲሁም ወያኔን ለመቀላቀል ፈቃደኞች ያልሆኑ ዜጎች ዘርፈ ብዙ ጥቃት እየተካሄደባቸው እንዳለ የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከአካባቢው ባደረሰን መረጃ ገልጿል።

በወልቃይት ጠገዴ፣ በዳንሻ፣ በሳንጃ፣ በጎንደር፣ በባህርዳር እና በመቀሌ የሚኖሩት ዜጎች በሰበብ አስባቡ ንብረታቸውን ከመወረስ አንስቶ በተፈበረከ ክስ ለእስር እስከመዳረግ፤ እንዲሁም ታፍነው የደረሱበት እስከማይታወቅበት ድረስ እየተጠቁ መሆኑን ዘጋቢያችን ያደረሰን መረጃ አሳይቷል።

በተለይም የመንግስት ሰራተኞች የሆኑት የጥቃቱ ሰለባዎች፤ ከበርካታ አመታት በፊት ህገ-ደንብ ጠብቀው የፈጸሙት የእቃ ግዢ ወይም የተቀበሉት የውሎ አበል በትክልል እንዳልተፈጸመ እየተነገራቸው እስር እየተፈረደባቸው ይገኛል።

በአርማጭሆ፣ በዳንሻ፣ በሳንጃና በጎንደር አካባቢ ደግሞ በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ያላቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በአገዛዙ የጸጥታ አባላት እየታፈኑ ተወስደው የደረሱበት አለመታወቁ ቤተሰብ እና ዘመዶቻቸውን ማስጨነቁን ሪፖርተራችን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል። የተቀሩት የጥቃቱ ሰለባዎች ደግሞ ግብር አልከፈላችሁም በሚል ከጥቃቅን የንድግ ቁሳቁሶች አንስቶ እስከ ከፍተኛ ማምረቻ ድርጅቶች ድረስ እየተወረሰባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

የብር ዋጋ መውደቁን ተከትሎ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበት ሸማቾችን ማስደንገጡ ታወቀ
በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባላፈው ሳምንት በአንድ ዶላር ዋጋ ላይ የ20% ጭማሪ በማድረግ ወደ 16 ብር ከ35 ሳንቲም ማሳደጉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበት ሸማቾችን ማስደንገጡን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል። የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ በአዲስ አበባ በመርካቶ አካባቢ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው፥ የስሚንቶ ዋጋ በ10 ብር የጨመረ ሲሆን፣ ለህንፃ ግንባታ የሚውል ብረት ዋጋም በኪሎ ግራም ሁለት ብር ጨምሯል። አዲስ ነገር ኦንላይን የተባለው የዜና ድረ-ገጽም በተለያዩ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ምንጮቻችን እንደገለጹት፥ የዋጋ ግሽበቱ በሸማቾች ላይ መደናገጥን እና አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ብዙዎችም ተጨማሪ ግሽበት እንዳይፈጠር በመስጋት በብዛት ሲሸምቱ ተስተውለዋል።

ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ በኢትዮጵያው አገዛዝ ላይ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ እንደሆነ የቀድሞ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ አቶ አሰግድ ተፈራ ተናገረ
የቀድሞ የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረውና በአሁኑ ሰዓት በውጭ አገር በስደት ላይ የሚገኘው አቶ አሰግድ ተፈራ ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ በወያኔ አገዛዝ ላይ ያለው ተጽእኖ ከፍተኛ እንደሆነ ከግንቦት 7 ድምጽ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልጿል።

ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ በ1997ቱ ምርጫ የወያኔን አገዛዝ በግልጽ የደገፈ ከመሆኑም ባሻገር፤ ዘረኛው አገዛዝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን ካስጨፈጨፈ በኋላም ድጋፉን አጠናክሮ እንደቀጠለ ይታወቃል። ወያኔ በየካቲት 1998 31ኛ አመት የልደት በአሉን ሲያከብር፣ ግለሰቡ 5.5 ሚሊዮን ብር ለዘረኛው ቡድን በስጦታ ማበርከቱ ይታወሳል። ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ ከወርቅ ማእድን አንስቶ የበርካታ መሬት ይዞታዎች ባለቤት እንደሆነ ይታወቃል።

አቶ አሰግድ ተፈራ ግለሰቡ ከወያኔ ጋር ያለው ግንኙነት ከጥቅም ትስስር ያለፈ እንደሆነ በመጠቆም፤ “ኢትዮጵያን የሚመራት ሼክ መሃመድ ነው” ብሏል። ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚገልጡት፥ አዜብ መስፍን እና ስብሃት ነጋ በህወሃት ውስጥ በሚያደርጉት ሽኩቻ፤ ሼክ አላሙዲ ጉልበት ካለው የአዜብ መስፍን ጎራ በመሰለፉ ለጊዜውም ቢሆን ከፍተኛ ሃይል ለማግኘት ችሏል።

የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት እንደቀጠለ ነው
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደቀጠለ ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ዜጎችን፣ በተለይም በንግድ የሚተዳደሩትን፣ ለእንግልት መዳረጉን ቀጥሏል።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ሳምንት በቀን እስከ ስድስት ሰዓታት ድረስ ባብዛኛው የመዲናይቱ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት እንደነበረ ዘጋቢያችን ያደረሰን መረጃ አመልክቷል። አንዳንድ አካባቢዎች ያለ መብራት ውለው ማደራቸውም ታውቋል። ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ የተለያዩ ክፍላተ ሃገራት፣ ያለ መብራት ውሎ ማደር እና መሰንበት የተለመደ ጉዳይ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።

የወያኔ አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ማስፋፋቱን ሽቦ የዘረጋባቸውን ከተማዎች በመቁጠር በየአመቱ ቢያስታውቅም፤ በነዚህ አካባቢዎች በቋሚነት የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የሚያገኙ ከተሞች የሉም። ለምሳሌ ወያኔ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ የኤሌክትሪክ ሽቦ የተዘረጋባት አንዲት በምእራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ነዋሪ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፣ መብራት ወደ ከተማይቱ ገባ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ በበጋ “የወንዝ ውሃ ቀነሰ”፤ በክረምት ደግሞ “ነፋሱ ምሰሶውን ጣለው” እየተባሉ በአመት ውስጥ መብራት የሚያገኙበት ጊዜ እጅግ በጣም የተወሰነ እንደሆነ ገልጸዋል። እኒሁ ነዋሪ ከጥቂት አመታት ወዲህ የኤሌክትሪክ ሃይል እጥረት መባባሱን እና መብራት ካሉባቸው ቀናት ይልቅ የሌለበት እንደሚበልጥ ተናግረዋል።

የወያኔ አገዛዝ ከውጭ የሚተላለፉ እንደ ቪ ኦ ኤ እና ኢሳት የመሳሰሉትን  መገናኛ ብዙሃን ላይ አፈና ለማካሄድ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል እንደሚያባክን በተደጋጋሚ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል። በሥራ ላይ የማይተረጎም ቃል መግባት የማይሰለቸው መለስ ዜናዊ ከ እንግዲህ በኢትዮጵያ ሻማ የሚፈለገው ለልዴት ቀን በ ዓል ብቻ ነው ባለ ጥቂት ቀናት ጀምሮ አዲስ አበባን በሚያክል አለም አቀፍ ከተማ ውስጥ መብራት በፈረቃ ጭምር የማይገኝባቸው ቀናት  እየተበራከተ መምጣቱ የተለመደ ሆኖአል።

የኢትዮጵያን ባንዲራ በማጥላላት ታሪኩ የሚታወቀው የወያኔ አገዛዝ “የባንዲራ ቀን” ለማክበር ደፋ ቀና ማለት ጀምሯል
በአንድ ወቅት ከዱቄት መቋጠሪያ ጨርቅ ያለፈ ጥቅም ወይም ክብር እንደሌለው በአደባባይ ይናገር የነበረው ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ከጥቂት አመታት ወዲህ የህዝቡን ልብ ለማማለል ይረዳኛል በሚል እምነት ለአገሪቱ ነጻነት ምልክት የሆነውን ባንዲራችንን አፍቃሪ መስሎ ለመታየት የባንዲራ ቀን ማክበር መጀመሩ  ይታወቃል።

የወያኔ አገዛዝ በ1997ቱ ምርጫ የኢትዮጵያን አንድነት ባቀነቀኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከተሸነፈ በኋላ እራሱን እንደ ኢትዮጵያዊ ቡድን ለመቅረጽ እያደረጋቸው ካሉት ሙከራዎች ውስጥ አንዱ የባንዲራ ቀን መሰየም ነበር። በዚህም አኳኋን አገዛዙ በመጪው መስከረም 10 ቀን “የባንዲራ ቀን” ለማክበር በተሾመ ቶጋ መሪነት ደፋ ቀና እያለ መሆኑ ታውቋል። በየአካባቢው በርእሱ ላይ እንዲሰብኩ የታዘዙት የአገዛዙ ካድሬዎች የባንዲራን ቀን ማክበር ወጣቶች አገራቸውን እና ባንዲራቸውን እንዲወዱ እንደሚያደርጋቸው ከቀበለ ቀበለ እየተዘዋወሩ መስበክ መጀመራቸውን  ለማወቅ ተችሏል።

የግንቦት 7 ድምጽ የአዲስ አበባ ዘጋቢ መጪውን በዓል በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው እነሱ ስለነገሩን አይደለም። ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን እንወድ ነበር፤ አሁንም እንወዳለን፤ ወደፊትም እንወዳለን። ይህ በደማችን ውስጥ ያለና መቼም ቢሆን ከልባችን ሊወገድ የማይችል ነገር ነው፤” ብለዋል።

በኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን እና ኮሚኒውኬሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ የሚሰሩ ሰራተኞች የተቋሙን ዘረኛነት አማረሩ
በዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ኮሚውኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኤጀንሲ አንዳንድ ሰራተኞች በተቋሙ ውስጥ አለ ስለሚሉት ዘረኛነት ማማረራቸውን የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ለዝግጅት ክፍላችን ባደረሰው ዘገባ አስታውቋል።

ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስሞታቸውን ያሰሙት ግለሰቦች፥ የወያኔ ሹም በሆነው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከሚመራው ተቋም ሰራተኞች ውስጥ ከ90% በመቶ በላይ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው ; ይህም ሊሆን የቻለው ተቋሙ በዘር አድሎ ላይ ተመስርቶ ሰራተኞችን ስለሚቀጥር ነው ሲሉ ገልጸዋል። የዝግጅት ክፍላችን የዚህን ቁጥር እውነተኛነት ከሌሎች ምንጮች ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው  ያልተሳካ ይሁን እንጂ በወያኔ አገዛዝ ስር ተቋማዊ ዘረኛነት በከፍተኛ ደረጃ ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የመስሪያ ቤቱ ህጋዊ የስራ ቋንቋ አማርኛ ቢሆንም፤ ከትግራይ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ መሆን የተነሳ አብዛኛውን ጊዜ የሚወራው ትግርኛ እንደሆነና አንዳንድ ጊዜ መስሪያ ቤቱ አዲስ አበባ ሳይሆን መቀሌ ያለ እንደሚመስላቸው ሰራተኞቹ ተናግረዋል። ይህም ከስራቸው የመገለልን እና የእንግዳነትን ስሜት እንደፈጠረባቸው እና፤ የህዝብ ንብረት በሆነው ተቋም ላይ እንደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የባለቤትነት ስሜት እንዳይሰማቸው መደረጋቸውን በስሞታቸው አክለዋል።

ሰራተኞቹ በመጨመርም፥ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ አቻዎቻቸው በነፃነት መንቀሳቀስ እና መስራት ሲችሉ፤ እነሱ ግን እንደማይታመኑ እና በስራቸው ላይም ሆነ በእረፍት ሰዓት ሻይ ለመጠጣት ሲወጡ ክትትል እንደሚደረግባቸው አስረድተዋል።

የፖለቲካ ተንታኞች የወያኔን የአምስት አመት እቅድ ማጣጣላቸውን ቀጥለዋል
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ለመጪው አምስት አመታት ያወጣው እቅድ በኢኮኖሚስቶች እና በፖለቲካ ተንታኞች ሲወገዝ ሰንብቷል።

ባላፈው ሳምንት ለዝግጅት ክፍላችን መልክት የላኩ አንድ የፖለቲካ ተንታኝም፣ አገዛዙ በዚህ እቅዱ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን አስመልክቶ ያሰፈረውን ቁጥር አጣጥለውታል። አዲስ አበባ የሚገኘው የሬውተርስ የዜና አገልግሎት ሪፖርተር ከማእድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አለማየሁ ተገኑ ጋር ሐሙስ ቃለ መጠይቅ አድርጎ፤ ሚኒስትሩ የወያኔ አገዛዝ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ምርት ከ2000 ሜጋ ዋት ወደ 10000 ሺህ ሜጋ ዋት እንደሚጨምር መናገሩን ዘግቧል።

ይህንን አስታከው አስተያየታቸውን የሰጡን የፖለቲካ ተንታኝ፥ የወያኔ አገዛዝ የዛሬ አምስት አመት ባወጣው እቅድ የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ከ15% ወደ 50% ከፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ እንደነበር አስታውሰዋል። ከሁለት ወራት በፊት በአገዛዙ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ ግን ባሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት የሚያገኙት ኢትዮጵያውያን 14 በመቶ ብቻ መሆናቸውን  መግለጹን ጠቅሰዋል። የፖለቲካ ተንታኙ፥ ወያኔ እራሱ የሚያወጣቸውን ቁጥሮች ላነጻጸረ፤ አገዛዙ የሃሰት ተስፋን ለመስጠት ሲል ብቻ ሊፈጽም የማይችለውን ቃል እንደሚገባ ግልጽ ነው ብለዋል።

መለስ ዜናዊ ከአምስት አመታት በፊት በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽፋን መቶ በመቶ እንደሚሆን መናገሩ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ፥ ከአምስት አመታት በኋላ ግን ያ ቁጥር 0.4 በመቶ ብቻ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ፥ ዘረኛው አምባገነን የዛሬ ሃያ አመት ገደማ የኢትዮጵያ ህዝብ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ እንደሚጀምር ከመናገር አንስቶ፤ በቅርብ ጊዜ በአገሪቱ ውስጥ የዔሌክትሪክ ሃይል ስለሚትረፈረፍ ከዚህ በኋላ ሻማ የሚበራው ለልደት ብቻ ነው ማለቱ የሚዘነጋ አይደለም።