Archive for January, 2010

ወደ አረብ አገር ለግርድና ከሚላኩና በጉዲፈቻ ከሚሰጡ ዜጎች ወያኔ በርካታ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ያገኛል

ወያኔ ወደ አረብ አገር ለግርድና በሚላኩ ኢትዮጵያዊያንና በጉዲፈቻና በማደጎ ስም ለውጭ አገር ዜጎች ከሚሰጡ ህጻናት በአመት እስከ ከአንድ ቢልዮን ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር

የሰሞኑ የእነ መለስ ውሳኔ የነገረን ቁም ነገር ወያኔን ለማስወገድ መፍጠን እንዳለብን ብቻ ነው!!!

ሰሞኑን እነ መለስ በግንቦት7 አመራር አባላትና በመከላከያ ሠራዊት፣ በፖሊስ እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ የአንድን ዘውግ የበላይነት ለማንገስ ተብሎ የተዘረጋን ዘረኛ አደረጃጀት በይፋ በመቃወማቸው ምክንያት በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተሳትፈዋል ብለው በከሰሷቸው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች

የአውሮፓ ህብረት በግንቦት ሰባት አባላትና ወታደራዊ ምኮንኖች ላይ የተላለፈውን የሞት ውሳኔ አወገዘ

የአውሮፓ ህብርት የወያኔው ፍርድ ቤት በ5 የግንቦት 7 አባላትና ሲቪሎች ላይ የተላለፈውን የሞት ውሳኔ አውግዞ፣ የሞት ፍርድ በኢትዮጵያ እንዲቀር አጥብቆ ጠይቃል። የአውሮፓ ህብረት የወያኔው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ጭካኔ የተሞላበትና ሰባዊነት የጎድለው ነው ሲል ካውገዘ በሁዋላ፣

በወያኔ አምባገነን አገዛዝ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ ነው ሲል የአፋር ህዝብ ፓርቲ አስታወቀ

ፓርቲው ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ በወያኔው አምባገነንና ጨቋኝ አገዛዝ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ምንም አይነት የተመቻቸ ሁኔታ የለም ብሏል::

የወያኔ ቁንጮዎች በፍትህ አካላቱ ላይ ቀጥተኛ ጣልቃገብነት እንዳላቸው አንድ ዲፕሎማት ገለጹ

መለስ ዜናዊ በግንቦት 7 አባላትና በወታደራዊ መኮንኖች ላይ የተሰጠውን የይስሙላ ፍርድ በተመለከተ የሰጠው አስተያየት አገዛዙ በፍትህ አካላቱ ላይ ያለውን ቀጥተኛ ጣልቃገብነት ያሳያል ሲሉ አንድ ዲፐሎማት ገለፁ ።

የወያኔውን የእርዳታ አሰጣጥ ዘዴ የተቹና ለአለማቀፍ ድርጅቶች ያጋለጡ ገበሬዎች በመታሰር ላይ ናቸው

ወያኔ በረሀብ ለተጠቃው ወገናችን የተላከውን የእርዳታ እህል ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ ማዋሉን ተከትሎ አለማቀፍ ተቋውሞው እየጠነከረ በመጣበት ማግስት፣ ጉዳዩን ያጋለጡ ገበሬዎች በመታሰር ላይ መሆናቸውን ብሉም በርግ የተባለው ታዋቂ ድህረገጽ ዘግቧል።

የጂማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ካለፈው ሰማንት ጀምሮ አድማ ላይ ናቸው፤ በአድማው የተሽበረው ወያኔ በአዲስ አበባና በሌሎች ቦታዎች ሰራዊቱን አስፈሯል

ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን ሪፖርተራችን ከስፍረው ዘግቧል። ተማሪዎቹ የወያኔው አገዛዝ የወላጆቻቸውን የእርሻ መሬቶች እየቀማ ለአበባ እርሻ እንዲውሉ ማድረጉን በእጅጉ የተቃወሙ ሲሆን፣

ወ/ት ብርቱካን በግፍ የታሰረችበት የመጀመሪያው አመት በአዲስ አበባና በተለያዩ የውጭ አገራት ከተሞች ታስቦ ዋለ

የፈላጭ ቆራጩ መለስ ዜናዊ አገዛዝ የነጻነት አርበኛ የሆነችውን ወ/ት ብርቱካንን ያሰረበት አንደኛ አመት በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤትና በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በሻማ ማብራትና በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ታውቋል። በአንድነት ጽ/ት ቤት ግቢ ውስጥ በተደረገው የሻማ ማብራት

የወያኔ አገዛዝ “ኤርትራ ተቃዋሚዎችን በሱዳን በኩል ሊታዘምትብኝ ነው ሲል” አምቆት የከረመውን ፍርሀቱን ይፋ አደረገ

የወያኔው የደህንነት ክፍል ሃላፊ ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በመቀሌ ከተማ ውስጥ ሲካሄድ በነበረው የኢትዮ ሱዳን የኢኮኖሚና የዳርድንበር ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለተገኙት የሱዳን ባለስልጣናት እንደተናገረው ፣ ኤርትራ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን አስታጥቃ በሱዳን በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ዝግጅት እያደረገች ነው ብሎአል።

© 2008-2009