Archive for March, 2010

ሥነ-ምግባር ደህና ሰንብት

ሰሞኑን መለስ ዜናዊ “ተቃዋሚዎች በምርጫ ክርክር ወቅት የሚናገሩትን እንቀዳና ከምርጫ በኋላ በማስረጃነት ተጠቅመን እንከሳቸዋለን” በማለት በፓርላማ ውስጥ ያደረገውን ንግግር የምርጫ አፈፃፀም ሥነ-ምግባር ደንብን የጣሰ ስለመሆኑ ደንቡን የፈረሙ ፓርቲዎች አመራሮች መግለጫ ሰጥተውበታል።
በእኛ እምነት የመለስ ዜናዊ ከላይ የተጠቀሰው ንግግርና ሌሎቹም የሰሞኑ መግለጫዎቹ በጥቅሉ ሲታዩ የጣሱት አንድ የምርጫ አፈፃፀም ሥነ-ምግባር ደንብን ሳይሆን ባጠቃላይ ሥነ-ምግባርን ነው። እንዲህ ዓይነት ንግግሮችን [...]

አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከምርጫው በኋላ ለፍርድ የሚቀርቡ ይኖራሉ ሲል መዛቱ ተሰማ

በአምባገነንነቱና በዘረኝነቱ የሚታወቀው መለስ ዜናው አሻንጉሊት በሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቀው በቀጣዩ ምርጫ ከመጫወቻ ሜዳው ወጥተው በህግ ጥሰት ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን ፓርቲዎች መንግስት ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል በመዛት አስታውቋል። እንደመለስ አገላለጽ የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ እየሰሩ የሚገኙ ሃይሎች በተለያየ ደረጃ የሚታዩ መሆናቸውን፣ ይህን አደናቃፊ ስራ የሚሰሩ ሃይሎች ደግሞ ሆን ብለው [...]

የወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ

በአረመኔአዊው የወያኔው አገዛዝ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በግፍ ታስራ የምትገኘው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመን በር ወ/ት ብርቱካና ሚደቅሳ ህክምና በመከልከሏ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከወህኒ ቤቱ አካባቢ ከተገኙ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህመሟ ከወህኒ ቤቱ ክሊኒክ አቅም በላይ በመሆኑ ለአንድ ግዜ ወደ ሆስፒታል መላኳን የገለጹት የመረጃ ምንጮች፣ ህክምና ያደረገላት ሀኪም ተጨማሪ ህክምና እንደሚስፈልጋትና በሌላ [...]

ወያኔ አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እየላከ መሆኑ ታወቀ

አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ሰላማዊና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ እያለ በሚናገርበት ባሁኑ ሰዓት አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እየጫነ መሆኑን የደህንነት ምንጮቻችን ገለጹ። ምንጮቻችን እንደገለጹት ወያኔ መጋቢት 4 ቀን 2002 ዓ.ም ደማቅ አረንጓዴ ቀለም ባላቸው 8 ቮልቮ ተሳቢ የጦር ካሚዮኖች 16 ኮንቴይነር የጦር መሳሪያ ወደሁመራ አቅጣጫ ማጓጓዙ ታወቋል። በነኚሁ ከ16 በላይ [...]

የቀድሞው የባንድ ኤይድ ዳይሬክተር ህወሀት የርዳታን ገንዘብ ለጦር መሳሪያ ግዢ ማዋሉን አረጋገጡ

ደይሊ ሜይል የመረጃ ድረ ገጽ ባወጣው ጽሁፍ ቦብ ጊልዶፍ ቀደም ብሎ በቢቢሲ ሪፖርተር የቀረበውን ዘገባ ማጣጣሉንና መረጃ ከተገኘ ግን ይህን መንግስት እፋረዳለሁ ማለቱን አውስቶ፣ በወቅቱ የባንድ ኤይድ ዳይሬክተር በመሆን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈረንጆች አቆጣጠር ከ1985-91 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩትን የ 85 ዓመቱን ጆህን ጄምስ በመጥቀስ በርግጥም ከርዳታው ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነው ለጦር [...]

የአማራ ክልል አስተያየት ሰጪዎች ወያኔ የሃገሪቱን ሉአላዊነት አስከብራለሁ ማለቱ ንቀት ነው አሉ

“ለሁለት አስርተ ዓመታት የስልጣን ወንበሩን የሙጥኝ በማለት የኢትዮጵያን ህዝብ ወደደም ጠላም እንደፈለግሁ ረግጬ እገዛዋለሁ” በሚል ከንቱ ቅዠት ውስጥ የተዘፈቀው የወያኔው አገዛዝ፣ “ከመረጣቺሁኝ የሃገሪቱን ሉአላዊነት አስከብራለሁ ማለቱ እጂግ በጣም አሳፋሪና ለኢትዮጵያ ህዝብም ያለውን ንቀት አጉልቶ የሚያሳይ” መሆኑን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ያነጋገራቸው አንዳንድ የደብረ ማርቆስ ነዋሪዎች ገለጸዋል። አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ አስተያየት ሰጪ ለዘጋቢያቺን በሰጡት አስተያየት [...]

በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውሀ ካዩ አምስተኛ ቀናትን ማሳለፋቸውን ገለጹ

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች በደረሰው የውሃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት በርካታው የህብረተሰብ ክፍል ለአለፉት አምስት ቀናት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰቃየ መሆኑ ተገለጸ። አዲስ አበባ የሚገኘው የግንቦት ሰባት ዜና ዘጋቢ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተዘዋውሮ አንዳንድ ነዋሪዎችን ያነጋገረና የተፈጠረውን የውሃ አቅርቦት እጥረትም በቅርብ የታዘበ ከመሆኑም በላይ ይህ የውሃ እጥረት ከተከሰተ አምስተኛ ቀኑን እያስቆጠረ እንደሆነም ገልጿል። ከዚሁ ጋር [...]

ሂዩማን ራይትስ ወች በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ እጂግ አሳሳቢ መሆኑን ገለጸ

ሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ላለው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ጥሰት ‘’አንድ መቶ ጫና መፍጠሪያ መገዶች’’ በሚል ርእስ ባወጣው 64 ገጽ ጽሁፉ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በስፋትና በጥልቀት በመዳሰስ የአሜሪካን፤ የካናዳ፤ የኖርዎይ፤ የአውሮፓ ዩኒየን አባል ሃገራት እንዲሁም የዓለም ባንክ ሊወስዷቸው ስለሚገቡ ርምጃዎች ዝርዝር ሀሳቦችን አቅርቧል።
ሂይማን ራይትስ ወች በዚሁ ጽሁፉ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ [...]

የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በወያኔ የሰራዊት አባላት ላይ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ

ኦጋዴን ኦንላይን የተባለው ድህረ ገጽ እንደዘገበው ከማርች 5 2010 ጀምሮ በተደጋጋሚ በወያኔ የጦር አባላት ላይ በሰነዘረው ጥቃት በአስራዎች የሚቆጠሩትን መግደሉንና ቁስለኛ ማድረጉን ገልጿል።
ማርች 8 ቀን 2010 ዐም በቆራሄ አካባቢ በተደረገ ውጊያ 8 የወያኔ ወታደሮች መገደላቸውንና 8 ደግሞ ክፉኛ መቁሰላቸውን የጠቀሰው ኦጋዴን ኦን ላይን፣ በማርች 11 እና 15 በተደረጉት ውጊያዎች ደግሞ 10 ወታደሮች መገደላቸውና 11 ደግሞ [...]

ምርጫ 97 በ2002 ዓ.ም በትግራይ

ምርጫ 97 ኢትዮጵያዊያን ለዲሞክራሲ ያላቸውን ጥማት እና በጠመንጃ ኃይል ሥልጣን ላይ የወጣውን ወያኔን በምርጫ ካርድ ለማውረድ የነበራቸውን ጉጉት ያሳዩበት ነበር። በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ውስንም ብትሆን ነፃነት ካገኙ የመቶ ዓመታት ልምድ ካካበቱ አገሮች ሕዝቦች ባላነሰ ጨዋነት በተሞላበት ሥነ-ሥርዓት የሚበጃቸውን ለመምረጥ የማይቸገሩ መሆኑ እና ድምፃቸውን ለማስከበር መስዋዕትነት ለመክፈል የተዘጋጁ መኖራቸውን በግልጽ አሳይቶናል። ምርጫ 97 በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ [...]

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የሚፈጽመውን ሰቆቃ የሚያጋልጥ ስብሰባ በታላቋ ብርታኒያ ፓርላማ ውስጥ ተካሄደ

ባለፈው ሰኞ የመጋቢት6 ቀን 2002 ዓም ‘የሰብአዊ መብት ጥሰትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ’ በሚል ርእስ በታላቋ ብሪታንያ ፓርላማ ውስጥ አንድ ታላቅ ስብሰባ መካሄዱንና ስብሰባውም የተዘጋጀው የሁሉም ፓርቲዎች የፓርላማ ቡድን አባላት ያሉት የሶስተኛው ዓለም ትብብር በተሰኘ ድርጅት አሰባሳቢነት መሆኑ ታውቆአል።፡ በዚህ ስብሰባ ላይ በእንግሊዝ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈው እንደነበር ተያይዞ ተዘግቦአል።

የወያኔ የደህንነት ባልስልጣን ጌታቸው አሰፋ የስለላ ሰራተኞቹን ሰብስቦ ጥብቅ ት ዕዛዝ አስተላለፈ

የነፍሰ ገዳዩንና አምባገነኑን መለስ ዜናዊ ሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም በወያኔ ታማኝ የስለላ ሰራተኞች የተማከለው የደህንነትና ኤሚግሬሽን ሃላፊ ጌታቸው አሰፋ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ስብሰባ ጠርቶ በአገዛዙ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ተቃውሞ የሚያደራጁትን በጥብቅ እንዲከታተሉና አፋጣኝ የሆነ የአፈና እርምጃ እንዲወስዱ ጥብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ለደህንነት መሥሪያ ቤቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።

ኢትዮጵያ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ እየገባች ነው ሲል ታዋቂው ዘ ኢንዲፐንደንት ጋዜጣ ዘገበ

ኢንዲፐንደት ጠለፋ፣ አስገድድኦ መድፈር፣ ጋብቻ፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ነጻ ይወጡ ይሆን? በሚል ርእስ ባሰፈረው ጽሁፍ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አገሪቱን ወደ ወታደራዊ አገዛዝ እየለወጣት በመምጣቱ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና ተባብሶ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል ብሎአል።

መድረክ በመቀለ ከተማ በጠራው ስብሰባ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ ሰው መሳተፉ ተገለጸ

የ8 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ ባለፈው ዕሁድ መጋቢት 5 ቅውን በመቀሌ ከተማ ባደረገው ስብሰባ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱን የተለያዩ የዜና ምንጮች ገልጸዋል። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በየቀበሌዎች እየተዘዋወሩ ህዝቡ ለስብሰባ እንዳይወጣ ሲቀሰቅሱና ሲያስፈራሩ የነበረ ቢሆንም ህዝቡ ግን ቅስቀሳውንና ማስፈራሪያውን ከጉዳይ ባለመቁጠር በነቂስ ወጥቶ ስብሰባውን ለመታደም እንደቻለ ከስፍራው የተገኙ ዘገባዎች አመልክተዋል።
ወያኔ የድጋፍ መሰረቴ ነው ብሎ [...]

በባህርዳር እና በመቀሌ ከተሞች ወታደራዊ ሹም ሽር መደረጉ ተሰማ

ከየካቲት 23 እስከ የካቲት 28 ቀን፣ 2002 ዓም በሙሉአለም አዳራሽና በመቀሌ ከተማ በተደረገው ወታደራዊ ስብሰባዎች አገዛዙን ለማፍረስ ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ወታደራዊ መኮንኖች ማእረጋቸውን የተነጠቁ ሲሆኑ፣ ለአገዛዙ ታማኝ ናቸው የተባሉት የሰራዊቱ አባላት ደግሞ ከመቶ አለቅነት ጀምሮ ያሉ የማእረግ እድገቶች ተሰጥቶአቸዋል።
በልዩ ጥበቃ የተከናወነው የመኮንኖች ግምገማና ሹም ሽር ከእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው [...]

Page 1 of 3123»
© 2008-2009