Archive for April, 2010

ከወጣት ቢያንሳ ዳባ ጋዲሳ መስዋትነት ስለ ሁለገብ ትግል የምንማረው ቁም ነገር

የሰላማዊ ታጋይ የወጣት ቢያንሳ ዳባ ጋዲሳን ሞት የሰማነው በሃዘን ነው። በትግራይ በአቶ አረጋዊ ገብረዮሃንስ መገደል ምክንያት ከደረሰብን ሃዘን ሳናገግም አሁን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ተመሳሳይ ግፍ ተፈጽሟል። ቢያንሳ ረዥም ህልም የነበረው የ23 ዓመት ወጣት ተማሪ ነበር። ይህ ወጣት በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ በማመኑ መድረክ እንዲመረጥ ሲቀሰቅስ ነበር። የወያኔ ተላላኪ የኦህዴድ ካድሬዎች ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ [...]

የወያኔን የምርጫ ግርግር የሚመለከቱ ቅኔ ብጤዎች

1
ተውሥሳክ ይዞን ኢንፍሉዌንዛ
እጅግ ተጎዳን እንደዋዛ፣
ሻከረ ጉሮሮአችን
እጅግ ታፍኖ ድምፃችን•።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በአውሮጳ ምክር ቤት በተካሄደ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር አደረጉ

የግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኖት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፥ “የአፍሪቃ ቀንድ ፈተናዎች” በሚል ርእስ በአካባቢው በሚታዩት አሳሳቢ የፖለቲካ ችግሮች ላይ ግንዛቤ ለማስያዝ በአውሮጳ ምክር ቤት በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ከትናንት በስቲያ በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የውጭ እርዳታ የገዢውን ፓርቲ የአፈና ምህዳር ለማስፋፋት እየዋለ መሆኑ መጋለጡን ቀጥሏል

ሄለን ኤፕስቴን የተባሉ የጤና ጥበቃ ተመራማሪ፥ የኢትዮጵያን የጤና ጥበቃ እስትራተጂ ለማጥናት በአገሪቱ ውስጥ ቆይታዎችን ካደረጉ በኋላ በቅርቡ ባወጡት ሪፖርት፤ ከውጭ የሚመጣው እርዳታ የገዢውን ፓርቲ የአፈና እና የቁጥጥር ምህዳር ለማስፋፋት ከመዋሉ ባሻገር የዜጎችን ህይወት እየለወጠ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

በካናዳ አገር ቶርንቶ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወያኔ የጠራውን ስብሰባ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ

ከተለያዩ ድርጅቶችና ማህበራት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ወያኔ ጠርቶት የነበረውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ እንደወጡ አንድነት ለሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የሚባለው ድርጅት ማክሰኞ እለት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ ገልጿል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አባል የሆኑ ግለሰብ በወያኔ አባላት በደረሰባቸው ድብደባ መሞታቸው ታወቀ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አባል የሆኑ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ሃይሎች በጠብመንጃ ሰደፍ ተደብድበው ለሞት መብቃታቸውን ሮይተርስ የዜና አገልግሎት የፓርቲውን አመራር በመጥቀስ ዘግቧል።
አቶ ቢያንሳ ዳባ የተባሉት ግለሰብ መጋቢት 29 ቀን 2002 አመተ ምህረት፥ ወደ መኖሪያ ቤታቸው መጥተው አባል ለሆኑበት ፓርቲ ሰዎችን መመልመሉን እንዲያቆሙ ባዘዟቸው የገዢው ፓርቲ አባላት በጠብመንጃ ሰደፍ

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አሁንም እርዳታን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል መቀጠሉን አዲስ መረጃዎች አሳይተዋል

ከሃያ አምስት አመታት በፊት ጀምሮ እርዳታን ለፖለቲካና ለግል ጥቅም ማዋሉ በበርካታ አካላት የተረጋገጠበት ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አሁንም በህገ-ወጥ ተግባሩ እንደቀጠለበት መሆኑ ታወቀ።
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የወባ በሽታን ለመከላከል በእርዳታ ያገኛቸውን የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበሮች ባደባባይ ለአገዛዙ ካድሬዎች፣ ለዘመዶቻቸውና በመጪው ምርጫም ወያኔን ሳይወዱ በግድ ለመምረጥ ቃላቸውን ለሰጡ ግለሰቦች እያደለ መሆኑን የደረሰን ዜና አሳውቋል።

ከኢትዮጵያ ተባረው የነበሩ ኤርትራዊያን ንብረቶች የሆኑ ቤቶች በወያኔ ካድሬዎች በህገ-ወጥ አራጣ ተሽጠው እንደነበር ታወቀ

በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ ተባረው የነበሩ የኢትዮጵያ ወይም የኤርትራ ዜግነት የነበራቸው በርካታ ኤርትራውያን ንብረቶች በወያኔ ካድሬዎች በህገ-ወጥ አራጣ ተሽጠው እንደነበር የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ለማወቅ ችሏል።
በወቅቱ የኤርትራውያኑን ቤቶች ከወያኔ ካድሬዎች ህገ-ወጥ በሆነ አኳኋን ገዝተው የነበሩት ግለሰቦችም፣ በቅርቡ የወያኔው አገዛዝ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ንብረቶቻቸውን እንዲወስዱ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ኢትዮጵያውያን ከእሰጣ ገባ የፖለቲካ ጭቅጭቅ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ

የግንቦት 7 የነፃነት፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እሁድ፣ ሚያዝያ 17 ቀን 2002 ዓም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ውይይት መድረክ በመባል ለሚታወቀው ማህበር በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ኢትዮጵያዊያን ገንቢ ካልሆኑ አተካራዎች በመቆጠብ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን አሜሪካን ካውንስል የባራክ ኦባማ አስተዳደር በመጪው ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ሊካሄድ የታቀደውን የምርጫ ተውኔት ውጤት እንዳይቀበል ጥሪ አደረገ

ድርጅቱ ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ የዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ አገዛዝ ከመጪው ወር ምርጫ ተብዬ በኋላ እራሱን አሸናፊ ብሎ እንደሚያውጅ ከወዲሁ የታወቀ እንደሆነና፤ ይህንንም እውን ለማድረግ አገዛዙ ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ ሲሰናዳ መቆየቱን ገልጿል።

በረከት ስምኦን፥ ለኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ በመቀስቀሳቸው የተገደሉት አቶ ቢያንሳ ዳባ የገዢው ፓርቲ አባል ናቸው አለ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አባል የሆኑት አቶ ቢያንሳ ዳባ መጋቢት 29 ቀን በወያኔ ካድሬዎች ድብደባ ደርሶባቸው ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ሚያዝያ 8 ቀን ህይወታቸው ማለፉን ሬውተርስ የዜና አገልግሎትን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወሳል።
የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ባለስልጣን የሆነው በረከት ስምኦን ግን በግለሰቡ ላይ የተደረገ ድብደባ

በትግራይ ክልል በአዲ ዳይሮ ከተማ የተከሰተ ፍንዳታ አምስት ሰዎችን ገድሎ ከ20 በላይ ማቁሰሉ ተዘገበ

ቅዳሜ፥ ሚያዝያ 16፣ 2002 አመተ ምህረት በትግራይ ክልል አዲ ዳይሮ ከተማ ቡና ቤት ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ አምስት ሰዎች ሞተው ከሃያ በላይ መቁሰላቸውን ሬውተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ፍንዳታው በተከሰተበት ቀን በሰአታት ውስጥ የወጣው የሬውተርስ ዘገባ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት የሆነው ጸጋይ በርሄን ጨምሮ የክልሉ አስተዳዳሪዎች እንደተለመደው ለወንጀሉ የኤርትራ መንግስት ተጠያቂ ነው ማለታቸውን ዘግቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ ፍንዳታ በደረሰ ቁጥር [...]

የግቤ ግድብ ግንባታን ይቃወማሉ ተብለው የሚገመቱ ዜጎች እስራትና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑ ታወቀ

የግቤ ግድብ ግንባታ በአካባቢው ነዋሪዎች እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በሚል ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ዜጎች እስራትና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑ ተዘገበ።
ኢንተርናሽናል ሪቨርስ የተባለ ድርጅት ቅዳሜ እለት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው ዘገባ፥ የግድቡን መገንባት የሚቃወሙ ቃላት ያሉበትን ካናቴራ ባለማወቅ የለበሰ ግለሰብ መታሰሩን ገልጿል። በግድቡ ግንባታ ላይ ጥናት ለማድረግ ለመጡ

በሙስና የነቀዘው የወያኔ ሥርዓት በፍጥነት መወገድ አለበት፤ ይህን ማድረግ ደግሞ ይቻላል!!!

የዘረፋ መሠረቶችን በማስፋት እና አዳዲስ የአዘራረፍ “ጥበቦችን” በመፈልሰፍ ረገድ የወያኔን ያህል የተሳካለት የማፍያ ድርጅት ማግኘት አይቻልም። ወያኔ ለዓለም ያስተዋወቃቸው የዘረፋ ዓይነቶችና ስልቶችን ለመዘርዘር ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም ለጊዜው በአራት ዋና ዋና ክፍሎች መድበን ማየት እንችላለን፦ 1ኛ/ ግልጽ ዘረፋ፣ 2ኛ/ ከፊል ግልጽ ዘረፋ፣ 3ኛ/ ድብቅ ዘረፋ፣ እና 4ኛ/ ይሉኝታ ቢስ ዘረፋ።

የግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ በአራት አዳዲስ ሞገዶች ላይ ስርጭቱን ማስተላለፍ መጀመሩን አስታወቀ

የግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ ወያኔ በአገር ውስጥ ስርጭቱ ላይ የሚያደርገውን ጃሚንግ ወይም አፈና ለመቋቋም ሲል የስርጭት ሞገዶቹን በእጥፍ በመጨመር፤ ስርጭቱን በአራት አዳዲስ ሞገዶች ላይ እንደሚያስተላልፍ አስታውቋል።
ከሚያዚያ 12 ቀን 2002 አመተ ምህረት ጀምሮም፥ በ41 ሜትር ባንድ ላይ በ7185፣ በ7140 ወይም በ7175 ኪሎ ኸርዞች ላይ፤ እንዲሁም በ49 ሜትር ባንድ በ6100 ኪሎ ኸርዝ፤ ላይ የግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ [...]

Page 1 of 41234»
© 2008-2009