ትምህርት የእውቀት አድማስን ካላሰፋ፤ አዳዲስ ክህሎቶችን ካላሳወቀ፤ የእለት ከእለት ኑሮን ካላሻሻለ እና አዎንታዊ የባህርይ ለውጥ ካላመጣ ፋይዳው እምን ላይ ነው?
የወያኔ የትምህርት ሥርዓት ከላይ ከዘረዘርናቸው ውስጥ ለአንዱም የተዘጋጀ አይደለም። ወያኔ ትምህርት ቤቶችንና ዩኒቨርስቲዎችን ከእውቀትን መገበያያነት ይልቅ እጅግ ኋላቀር የሆነ ዘረኛና ጎጠኛ አስተሳሰብ ማራቢያና ማሰራጫ ተቋማት አድርጎዓቸዋል።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሳት) በዚህ ሳምንት እንደገና መታፈኑን እና ስርጭቱ መቋረጡን ድርጅቱ በለቀቀው መግለጫ አስታወቀ።
መግለጫው አፈናውን የሚያኬሄደው ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ስለመሆኑም ድርጅቱ ማስረጃ እንዳለው ገልጿል። አገዛዙ ኢሳት ቴሌቪዥንን ለማፈን በሚያካሄደው
አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ክፍላት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የንግድ ድርጅቶቻቸው በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት ምክንያት እየተንገላቱ ባሉበት ወቅት የወያኔ አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል ለጎረቤት አገሮች ለመሸጥ ዝግጅቶች አጠናቅቄያለሁ ማለቱ ተዘግቧል።
ኒውስዊክ የተባለው ታዋቂ የአሜሪካ ጋዜጣ ሰሞኑን ባወጣው ጽሁፍ እንደ ወያኔ ያሉ አፋኝ አገዛዞች ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በማፍሰስ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ እያደረጉ ነው ብሏል።
የተለያዩ አምባገነናዊ አገዛዞች በአሜሪካን አገር የሚገኙ የሎቢ ድርጅቶችን በከፍተኛ ገንዘብ በመቅጠር የአሜሪካ ህግ አውጪ አካል እና አስተዳደር እነሱን በሚመለከት
የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አሎ አላዳይስ ከግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የወያኔ አገዛዝ በፌዴሬሽን ስም የሚነግድ እንጂ እውነት ፌዴሬሽን እንዲሰራ የሚፈልግ አይደለም ብለዋል።
አቶ አሎ እሁድ እለት ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት ቃለ መጠይቅ፥ የአፋር ክልል የራሱ የሆነ መንግስት አለው ማለት የማይቻልበት ሁኔታ እንዳለ ገልጸዋል። ተሰሚነት
ገዢው ፓርቲ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄደው ግምገማ ከውስጥ ሆነው ስራዬን አበላሽተውብኛል ያላቸውን ካድሬዎቹን ከፓርቲ ማባረሩን አዲስ ነገር ኦንላይን የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል።
የወያኔ የአዲስ አበባ ቢሮ ሃላፊ በሆነው ሬድዋን ሁሴን በተመራው በዚህ ግምገማ ላይ፥ በሚቀጥለው ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በግንቦት 15ቱ የምርጫ ተውኔት ካገኙት ያነሰ
የወያኔ አገዛዝ የውጭ አገር ቤተክርስቲያናትን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የያዘውን እቅድ ለማስፈጸም ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ለቤተክርስቲያኒቱ አመራር ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ በላኩት መረጃ አስረድተዋል።
ሐምሌ 14፣ 2002 ቀን በጂጂጋ ከተማ አንድ ወጣት ልጅ በአካባቢው በሚገኘው የወያኔ ጦር ተገድሎ በከተማው በሚገኝ እስር ቤት ፊት ለፊት መጣሉን ኦጋዴን ኦንላይን የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል።
ሃሰን የሱፍ አሊ የተባለው ወጣት ከሶስት አመታት በፊት ደገሃቡር ከሚገኝ ቡድህሌ የተባለ መንደር ተወስዶ እስር ቤት እንደቆየ ድረ-ገጹ የገለጸ ሲሆን፤ ከመገደሉ በፊት በወያኔ
የዴሞክራሲያዊ መብት አስከባሪነት ጭንብሉ ሙሉ በሙሉ እንደወደቀበት የተረዳው ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ፣ እራሱን እንደ ልማት መንግስት ለመቅረጽ የሚያደርገውን ጥረት ማጣጧፉን ከሰሞኑ የሚደርሱን ዘገባዎች አሳይተዋል።
አገዛዙ የኢትዮጵያውያንን አመለካከት እንደ መለስ ዜናዊ
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በአራጣ አበዳሪዎች ላይ እያካሄደ ያለው ፍርድ እንደ ወትሮው የአገዛዙ አሰራር በአድሎ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ዘገባ አስረድቷል።
የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከአዲስ አበባ አጠናቅሮ በላከው ዘገባ መሰረት ሰሞኑን አቶ አየለ ደበላ የተባሉ ሰው በአራጣ አበዳሪነት ተከሰው የ22 አመት እስራት እና 12 ሚሊዮን ብር ተፈርዶባቸዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም. በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በደረሰው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ፤ የአካልና የስነልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል። ግንቦት 7 በዚህ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን የኡጋንዳና የሌሎች አገራት ዜጎችም ሃዘን ይጋራል።
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ የስልጣን ዕድሜውን ለማራዘም እንዲያስችለው ኢትዮጵያውያን ስለ አገዛዝ ሥርአቱ የልማት መንግሥትነት አንድ አይነት አመለካከት እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያካሄደውን ዘመቻ አጧጡፎ እንደቀጠለበት ከሰሞኑ
ረኔ ለፎ የተባሉ እና ላለፉት 40 አመታት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ሲጽፉ የቆዩ ፈረንሳዊ ጋዜጠኛና ጸሃፊ በዚህ ሳምንት ባወጡት ጽሁፍ፣ በኢትዮጵያ ሰፍኖ ያለው በዘውግ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም በአገሪቱ ውስጥ ላለው ዘረኛ ስርአት እንደ ሽፋን ሆኖ የሚያገለግል ነው ሲሉ መስክረዋል። [...]
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በአንዳንድ የአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ከፍተኛ ጥበቃ እያካሄደ መሆኑን ሰሞኑን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።
የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከሰሜን ኢትዮጵያ አጠናቅሮ በላከው መረጃ መሰረት በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ እና በደሴ ከተሞች ፖሊሶች በየ100 ሜትር እንዲቀመጡ ከመደረጋቸው
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በአፋር ክልል በሚተነኩሰው ግጭት በርካቶች እየተገደሉ ነው ሲል የአፋር ህዝብ ፓርቲ በለቀቀው መግለጫ አስታወቀ።
በቅርቡ ባዱ በሚባል አካባቢ በተከሰተ ግጭት 30 ሰዎች ሞተው 50 የሚሆኑ ሴቶች፣ ህፃናት እና አዛውንቶች መቁሰላቸውን ፓርቲው ገልጿል። ከሁለት ወራት በፊትም በክልሉ የጋዋኔ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆነው [...]