Archive for March, 2011

የመጨረሻዉ ደወል

ከሁለት ምዕተ አመታት በፊት ትልቅነቷ ተዳስሶ የማያልቅ ትመስል የነበረቺዉ ይቺ የምንኖርባት ምድር ዛሬ ቴክኖሎጂ እንደ አበሻ ቀሚስ ጥለት ጠልፎና አጠላልፎ ሁሉም ሰዉ በአንድ ግዜ መተያየት የሚችልበት ክብ ጠረቤዛ አስመስሏታል። ዛሬ የአሜሪካ ህዝብ ምሽት ላይ የሰማዉን ሰበር ዜና አፍሪካን ጨምሮ የሌላዉ ዓለም ህዝብ የሚሰማዉ አሜሪካኖች ዜናዉን የሰሙበትን የቴሌቭዥን ጣብያ ሳይቀይሩት ነዉ። ይህ የሚያሳየን ወደ አገሮች ዉስጥ […]

በጋሞጎፋ ዞን የ8 ወረዳዎች ህዝብ ለወያኔ አልገዛም በማለት ተነሳ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የውስጥ ምንጮቹን በመጥቀስ የካቲት 29 ቀን 2003 ዓም ባወጣው ዘገባ በጋሞጎፋ ዞን የ8 ወረዳዎች ህዝብ ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ እያደረሰበት ባለው ግፍና በደል በመማረር ለወያኔ አልገዛም በማለት  መነሳቱንና አካባቢውም በፌደራል ፖሊስና ጦር ሃይል  መወረሩን ገልጹአል::

የእስልምና እምነት ተከታዮች በጂማ ክርስትያኖች ላይ እያደረሱ ባሉት ወንጀሎች የወያኔ እጅ እንዳለበት ታወቀ

ህዝብን በዘር በሃይማኖትና በጎሳ በመከፋፈል የስልጣን እድሜውን ማራዘም ስራየ ብሎ የተያያዘው ዘረኛው የወያኔ አምባገነን አገዛዝ፡  በቱኒዚያ የተነሳው ህዝባዊ አብዮት በኢትዮጵያችን ሊነሳ ይችላል ከሚል ስጋት ለዘመናት ተፋቅሮ እና ተከባብሮ በሚኖረው የሙስሊሙና ክርስቲያኑ ህብረተሰብ መካከል ሆን ብሎ ግጭቶችን እየቀሰቀሰ መሆኑን ለሥር ዓቱ ቅርበት ያላቸው የግንቦት 7 ታማኝ ምንጮች ገለጹ።

የዘረኛው አገዛዝ ቁንጮ ባለቤት የሆነቺው አዜብ መስፍን የቅንጦት ኑሮ መጋለጡን ቀጥሉአል

የዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ ባለቤት አዜብ መስፍን ለሸቀጣ ሸቀጥ ሸመታ የካቲት 19 ቀን 2003 አም በቻርተር አውሮፕላን ወደ ዱባይ በረራ አድርጋ እንደነበር የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን የአየር መንገድ  ምንጮችን በመግለጽ ዘግቦአል። እንደ ኢሳት ምንጮች መረጃ አዜብ መስፍን

ወያኔ አርሶ አደሮችን የፓርቲ አባል ካልሆናችሁ እያለ በማንገላታት ላይ መሆኑ ተገለጸ

ህዝብን እንደ ጠላት እየፈራ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ሰሞኑን በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ አርሶ አደሮችን የልማት ስብሰባ በማለት እየጠራና የፓርቲው አባላት እንዲሆኑ እያስገደዳቸው መሆኑን  ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ከላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።  እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በቱኒዚያ ፈንድቶ የሰሜን አፍሪቃ ሃገራትን እየለበለበ ያለው  የህዝብ አመጽ እንደማይቀርለት የተረዳው ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ  የህዝብ ተቃውሞ ወደገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል እንዳይስፋፋ በማሰብ በአርሶ […]

ወያኔ በያዝነው የበጀት አመት ወደ ውጪ የላከው የቡና ምርት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ መሁኑ ተዘገበ

በያዝነው የበጀት አመት አጋማሸ ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ሃገር ይልካል ተብሎ የታቀደ የቡና ምርት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ሮይተርስ የተባለው የዜና አውታር ዘገበ። እንደዘገባው ከሆነ በአፍሪካ በቡና አቅራቢነቱዋ የምትታወቀው ሃገራችን ከምርቱ ከፍተኛ ገቢ በማግኘት በዘርፉ ላይ የተሰማሩትን ገበሬዎች ማጠናከር ብሎም ከድህነት አረንቁዋ ማውጣት የምትችልባቸው አጋጣሚዎች ሰፊ ሆነው ሳሉ ወያኔ በተገቢው ማከናወን አለመቻሉ በርካታ ታዛቢዎችን እንዳስገረመም አክሎ  ገልጾአል።

የዘረኛው አምባገነን አገዛዝ ፓርላማ ምክር ቤት ተሰናባቾች የካድሬነት ስራቸውን ጀመሩ

ከተለያዩ ክልሎች በህዝብ ተመርጠናል ብለው በፓርላማ ምክር ቤት የቆዩት የዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ሆድ አደሮች ከፓርላማ ምክር ቤት ከተሰናበቱ በሁአላ እዚያው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች እንዲቀጠሩ ተደርገው የካድሬነትን ስራ እንዲያከናውኑ መመደባቸውን የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ሃይልአ ቅርቦት እጥረትና የመጠጥ ውሃ ችግር እየተባባሰ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ ቀደም ብሎ የነበረው የውሃና የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር እንደተባባሰና በአንዳንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች በውሃ እጥረት ምክንያት ህብረተሰቡ አሁንም እየተጉላላ መሆኑን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ዘገባ ገለጸ:: እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በተከሰተው የውሃ

ሊያመልጠን የማይገባ መልካም አጋጣሚ

ሁኔታዎቸን በአንክሮ የአስተዋለ ሰው ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ዋዜማ ላይ መሆኗን መረዳት አያቅተውም፡፡ ህዝብ የለውጡን አይቀሬነት ተቀብሎ አሁን እያስጨነቁት ያሉት “ህዝባዊው አመጽ መቸ፣ የትና እንዴት ይነሳል” የሚሉት ጥያቄዎችን መመለስ ሆኗል:፡ ከሳምንታት በፊት ባህሬን፣ ሊቢያና የመን በተመሳሳይ ሁኔታዎች ውስጥ ነበሩ፡፡

የሰሜን አፍሪቃ ህዝባዊ አመፆችና ያገራችን እጣ ፈንታ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ – እሁድ ፌብሩዋሪ 13፣ 2011 ዓ:ም:: በዳላስ ከተማ ግንቦት ሰባት በጠራው ሀዝባዊ ስብሰባ ላይ የቀረበ ንግግር ሆሳም ካሊፍ የ50 አመት እድሜ ባለጸጋ የሆነ ግብጻዊ መሃንዲስ ነው:: ጣህሪር አደባባይ ሲዘዋወር ያገኘውን አንድ ምእራባዊ ጋዜጠኛ ተጠግቶ እኛ ከቱኒዝያ ምን እንደተማርን ታውቃለህ? ይለዋል:: የደረሰን መልእክት የሚለው “ራስህን አታቃጥል: ማቃጠል ያለብህ በውስጥህ የሰፈረውን ፍርሃት ነው:: የሚለውን […]

የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ዘረኛውን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ ለማስወገድ ቃል የሚገባበት ነው ተባለ

የግንቦት ሰባት ዘጋቢ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ወጣቶች የዘንድሮው የአድዋ ድል  መታሰቢያ ለነጻነታቸው ቀናይ የሆኑት አያት ቅድሜ አያቶቻችን በጣሊያን ፋሽስት ጦር ላይ የዛሬ 115 አመት ያገኙትን ድል 20 ዓመት ሙሉ በጫንቃችን ላይ ሆኖ የወደፊት ተስፋችንን በማጨለም በባርነት እየገዛን ባለው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ላይ ለመድገም ለራሳችን ቃል የምንገባበት እለት ይሆናል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል::

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የፍሪኩዌንሲ ለውጥ አደረገ

በቱንዚያ የተቀጣጠለው የህዝብ አብዮት በርካታ ሃገራትን እንደ እሳት እየለበለበ መሆኑ እንቅልፍ የነሳው የወያኔው አምባገነን አገዛዝ ዓለም አቀፉን ታዋቂ የዜና አውታር አልጃዚራን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃንን ኢትዮጵያዊያን እንዳይከታተሉ እያደረገ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል::

የማሌዢያው ፔትሮናስ ኩባንያ የነዳጅ ቁፋሮ ሥራውን ዘግቶ ጓዙን ጠቅልሎ ወጣ

ፔትሮናስ የነዳጅ ቁፋሮ ኩባንያ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦጋዴን ክልል አካባቢ ጀምሮት የነበረውን የነዳጅ ቁፋሮ ስራ በማቁዋረጥና ፕሮጀክቶቹንም ለዘረኛው አምባገነን አገዛዝ በማስረከብ ቦታውን ለቆ መውጣቱን ለአገዛዙ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ከስፍራው ባስተላለፉልን ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል።

የፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንዳር ደምሳሽ ሃይሉ በወያኔ ዘረኛነት ተማርረው ከሃገር ኮበለሉ

የዘረኛውና አምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊና የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮማንደር ደምሳሽ ሃይሉ በወያኔ ዘረኛነት ተማረው ስራቸውንና አገራቸውን ለቀው በስደት እንግሊስ አገር መግባታቸው ታወቀ::

የወያኔ የማሟያ ምርጫ ላይ የአዲስ አበባ ህዝብ ድርሽ ሳይል ቀረ። የካድሬዎች ውትወታና ልመና ጆሮ ዳባ ልበስ ተባለ

ከትናንትና በስቲያ ዕሁድ የካቲት 20 ቀን 2003 ዓም እንዲደረግ ታስቦ በነበረው የማሟያ ምርጫ ተቢዬ የወያኔ ድራማ፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ድርሽ ሳይል እንደቀረ የግንቦት 7 ዜና ዘጋቢ ከአዲስ አበባ በላከው ሪፖርት አስታወቀ።

Page 3 of 4«1234»
© 2008-2012