የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች በከፍተኛ ጥበቃ ስር መሆን የአገዛዙን በራስ ያለመተማመን ያሳያል ተባለ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በአንዳንድ የአገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ከፍተኛ ጥበቃ እያካሄደ መሆኑን ሰሞኑን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከሰሜን ኢትዮጵያ አጠናቅሮ በላከው መረጃ መሰረት በባህር ዳር፣ በጎንደር፣ እና በደሴ ከተሞች ፖሊሶች በየ100 ሜትር እንዲቀመጡ ከመደረጋቸው በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊሶች፣ የመከላከያ እና ልዩ ሃይል ወታደሮች በከተሞቹ ተሰማርተዋል። እንደ ሪፖርተራችን ገለፃ፥ ጠብመንጃ ታጥቀው የሚዘዋወሩት ፖሊሶች እና ወታደሮች ከተሞቹን የጦር ቀጠና አስመስለዋቸዋል።

ጉዳዩን በሚመለከት ዘጋቢያችን ያናገራቸው ግለሰብ ይህ አገዛዙ ስጋት እንዳለበት እንደሚያሳያቸው ገልጸዋል። ግለሰቡ ጨምረው፥ ወያኔ በግንቦት 15ቱ ምርጫ ከራሱ ጋር ተወዳድሮ የፓርላማውን መቀመጫ ሙሉ በሙሉ ቢቆጣጠርም በራስ መተማመን እንደሌለው አመላካች ነው ብለዋል።

© 2008-2009