ረኔ ለፎ የተባሉ እና ላለፉት 40 አመታት በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ሲጽፉ የቆዩ ፈረንሳዊ ጋዜጠኛና ጸሃፊ በዚህ ሳምንት ባወጡት ጽሁፍ፣ በኢትዮጵያ ሰፍኖ ያለው በዘውግ ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም በአገሪቱ ውስጥ ላለው ዘረኛ ስርአት እንደ ሽፋን ሆኖ የሚያገለግል ነው ሲሉ መስክረዋል። [...]
ከኢትዮጵያ ህዝብ ስድስት በመቶ የሚሆነውን የሚወክሉት የትግራይ ተወላጆች በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣንን እና ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ተቆጣጥረው እንዳሉ ጸሃፊው ገልጸዋል።
የግንቦት 7 ድምጽ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቸው ጥናታዊ ጽሁፎች እና ዘገባዎች የወያኔን ዘረኛነት ሲያጋልጥ እና ሲያወግዝ መቆየቱ ይታወቃል።
ረኔ ለፎ በዚሁ ጽሁፋቸው ላይ፥ አገዛዙ የትግራውያን የበላይነት እንዲቀጥል መስራቱ እውነተኛ ዴሞክራሲ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይኖር እንዳደረገ እና ለአገሪቱ አለመረጋጋትም ዋና ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል።