ዘረኛውና አምባገናዊው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ስርጭት እንደገና ማፈኑ ታወቀ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሳት) በዚህ ሳምንት እንደገና መታፈኑን እና ስርጭቱ መቋረጡን ድርጅቱ በለቀቀው መግለጫ አስታወቀ።

መግለጫው አፈናውን የሚያኬሄደው ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ስለመሆኑም ድርጅቱ ማስረጃ እንዳለው ገልጿል። አገዛዙ ኢሳት ቴሌቪዥንን ለማፈን በሚያካሄደው ጥረት በገዛ ቁጥጥሩ ስር የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት የሳተላይት ስርጭትም አብሮ ማፈኑ ታውቋል። ኢሳት በመግለጫው ከራሱ ስርጭት በተጨማሪ የሌሎች ድርጅቶች ስርጭቶችም በአፈናው እንደተጎዱ ገልጾ፤ በዚህ እኩይ ተግባር ከተጎዱ አካላት ጋር በመተባበር ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚጥር ገልጿል።

የወያኔ አገዛዝ ኢሳት መቋቋሙን እንደተረዳ ከቻይና የማፈኛ መሳሪያ በብድር ማስመጣቱን እና የድርጅቱ ስርጭቶች እንደጀመሩም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል በማፍሰስ እያፈነ እንዳለ አዲስ ነገር ኦንላይን የተባለውን ድረ-ገጽ በመጥቀስ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

© 2008-2009