በደቡብ አፍሪቃ በመካሄድ ላይ ያለው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ በአገራችን የእግር ኳስ መሠረታዊ ችግሮች ላይ እንድናተኩር እድል ሰጥቶናል። ኢትዮጵያ በወጣቶች የተገነባች እና ከፍተኛ የሆነ የእግር ኳስ ፍቅር ያለባት አገር ናት። በትላልቅ የእግር ኳስ ሜዳዎችና ግጥሚያዎች ኢትዮጵያዊያንንና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ለማየት ግን አልታደልንም። አገራችን እንኳንስ በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ልትወዳደር ቀርቶ ራሷ ካስጀመረችው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ እንኳን ከተባረረች ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ሆኗል። read more
ወያኔ በተደጋጋሚ የብሔረሰቦችን መብት ስለማስከበሩ እንደሚያወራ ይታወቃል። እውነታው ግን፣ የብሔረሰቦች መብት ለወያኔ ዘረኛነቱን ለመሸፈን ከሚጠቀምባቸው ጭንብሎች አንዱ ከመሆኑ ባሻገር በተግባር ያሳየው ነገር አይደለም።
በመሰረቱ ዘረኛ የሆነና ከአንድ መንደር እና ቤተሰብ የመጡ ሰዎች በአገሪቱ ላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት እንዲኖራቸው ተግቶ የሚሰራ ቡድን የብሔረሰቦችን መብት በእውነት ሊያስከብር አይችልም። ሊያደርጋቸው የሚችላቸው ብቸኛ ነገሮች ህዝቡን ለማታለል የተዘጋጁ read more
ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ በቡድን 20 ወይም ጂ20 ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ካናዳ የሚያደርገው ጉዞ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
በካናዳ የሚገኙ ሶማሊዎች ማህበር የሆነው “ካኔዲያን ሶማሊ ኮንግረስ” በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ ካናዳ መለስ ዜናዊን ለስብሰባው በመጋበዟ ማዘኑን ገልጿል። የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በኢትዮጵያውያን እና በሶማሊዎች ላይ የሰብአዊ መብት ረገጣን የሚያደርግ፤ ዴሞክራሲያዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚጨቁን፤ read more
የወያኔ ምርጫ ቦርድ የድጋሚ ምርጫ አይካሄድም በማለት ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም መድረክ ፓርቲ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ማቅረቡ ታወቀ።
የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ ለሬውተርስ የዜና አገልግሎት በሰጡት ቃል፤ 87 ገጽ ያለው የማስረጃ ሰነድ ለምርጫ ቦርድ ቢያቀርቡም፣ አንድም ማብራሪያ ወይም ምስክሮች እንዲያቀርቡ read more
የምርጫ ተውኔቱ ከመካሄዱ በፊት ማስፈራራት ሲደርስባቸው በነበሩ ዜጎች ላይ የአገዛዙ ሎሌዎች የበቀል ጥቃት መፈጸም መጀመራቸውን ዘገባዎች እያሳዩ ነው።
ኢትዮሚድያ በሚባለው የዜና ድረ-ገጽ ላይ ሰሞኑን እየወጡ ያሉ ተከታታይ ዘገባዎች እንደሚያስረዱት፤ በተለይም በደቡብ ክልል በዜጎች ላይ በሰፊው ጥቃት እየደረሰ ነው። የምርጫ ታዛቢዎች በሃሰት እየተወነጀሉ እና ክስ ሳይመሰረትባቸው ለረዥም ቀናት ታስረው እንዲቆዩ እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። read more
ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ወይም ኢሳትን አፍኗል ተባለ። ኢሳት ቅዳሜ እለት ባስተላለፈው ዘገባ፣ የጣቢያው ማኔጅመንት የወያኔ አገዛዝ የቴሌቭዥን ድርጅቱን ስለማፈኑ ማስረጃ ለማሰባሰብ ችሏል ብሏል።
የሳተላይት አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያው በበኩሉ የአፈናውን ምንጭ ለመረዳት ምርመራውን እንደቀጠለ እና በቂ ማስረጃ ሲያገኝም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ መግለጹን የኢሳት መግለጫዎች አሳይተዋል። read more
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) የወያኔ አገዛዝ ባለፈው ወር ብቻ በኦጋዴን 71 ንጹሃን ዜጎችን መግደሉን ለዜና አውታሮች በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ግንባሩ በመግለጫው፥ ወንዶች ቤተሰቦቻቸው ፊት ሲገደሉ፤ ሴቶች ተደብድበዋል፣ ተደፍረዋል፣ ተገድለውማል ማለቱን ሬውተርስ የዜና አውታር ዘግቧል። ጉዳዩን አስመልክቶ የተጠየቀው የበረከት ስምኦን ምክትል ሽመልስ ከማል አገዛዙ ጉዳዩን እየመረመረ እንደሚገኝ እና እስካሁን የተደረገው ምርመራ መሰረተ ቢስ read more
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ለባሰ ድህነት የዳረገው የዋጋ ግሽበት ወያኔ እንደሚለው እድገት የፈጠረው ሳይሆን በአገዛዙ የገንዘብ ፖሊሲ ምክንያት የተፈጠረ ነው ተባለ።
ባለፉት አራት አመታት በኢትዮጵያ ከቁጥጥር ውጪ በወጣ መልኩ ከሚታየው የዋጋ ግሽበት የተነሳ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት እያቃታቸው የኑሮ ደረጃቸው ወደከፋ ደረጃ ማሽቆልቆሉ እና read more
የወያኔ ጦር ከፍተኛ የሆነ የወታደሮች ፍልሰት ችግር እንዳለበት የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ከኢትዮጵያ በላከው ዘገባ አስታውቋል።
ዘጋቢው ከሰሜን ኢትዮጵያ ባስተላለፈው መረጃ፣ በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ በጠገዴ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ተሰማርቶ የነበረው የ4ኛ ሻለቃ ልዩ ሃይል በደረሰበት የወታደሮች ፍልሰት በመዳከሙ አገዛዙ በአዲስ ምሩቆች ሊሞላው ተገዷል። አብዛኞቹ ወታደሮች በክህደት እንደሚለቁ የታወቀ ሲሆን፤ read more
በኬንያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢሚግሬሽን ካውንስለር ሆና በቅርቡ የተመደበችው ግለሰብ ለስራው የሚያስፈልገውን ብቃት የሌላት እና የወያኔ አገዛዝ ዘረኛ ፖሊሲ ተጠቃሚ ነች ሲሉ የኤምባሲው ምንጮች ስሞታ አሰምተዋል።
ለግንቦት 7 ድምጽ ከስፍራው የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አለም ተክሉ የተባለችው ግለሰብ የወያኔ የቀድሞ ታጋይ ስትሆን፣ የተማረችው እስከ ሶስተኛ ክፍል ድረስ ብቻ ነው። ኤምባሲው read more
ፍሬደም ሃውስ የተባለው አንጋፋ አለም አቀፍ የነፃነት ተሟጋች ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው አመታዊ ሪፖርት የወያኔ አገዛዝ የዘር አድሎን በሰፊው እንደሚፈጽም፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሁኔታ ከቀደመው አመት የከፋ መሆኑን ገልጿል።
ተቋሙ የወያኔ አገዛዝ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የዘር አድሎ እንደሚፈጽም እና ከትግራይ ለሆኑ ሰዎች እንደሚያደላ ተናግሯል። በሌሎች ብሔረሰቦች ላይም በሰፊው አድሎ እንደሚፈጸም መስክሯል። read more
ከግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱና ለነፃነቱ ሲታገሉ በባዕዳን ፋሺስቶችና ዬኔ ብሎ በሚላቸዉ ጨካኝ ልጆቹ የተጨፈጨፉ አያሌ ሰማዕታት ልጆች አሉት። በ1928 ዓም በወርሃ ዬካቲት የፋሺስት ኢጣሊያ ወታደሮች ሽማግሌ ከህፃንና ጎበዝ ከደካማ ሳይለዩ በሕይወት ቆሞ ሲሄድ ያዪትን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጭካኔ በመግደል በአንድ ጀምበር ከ30ሺ በላይ ኢትዮጵያዉያንን ጨፍጭፈዋል። በ1969 ዓም እና በ1997 ዓም ደግሞ ኢትዮጵያን read more
ግንቦት 15 2002 ዓ.ም
የተከበራችሁ ወዳጆቼ በመጀመሪያ እዚህ አርፍጄ በመገኘቴ ይቅርታ ልጠይቅ ይገባኛል። የኔ ጥፋት አይደለም። ። የኢትዮጵያን ህዝብ ገንዘብ መለስ ዜናዊ ለደላላ ኩባንያዎች እንዳሻው እያርከፈከፈ እንደሚያባክነው ብናውቅም ፣ እኔንም እንዲሁ በነዚሁ ደላላ ኩባንያዎች አማካኝነት ለመደለል ጥረት ሲያደርግ ቢከርምም ያሁኑን ጉዞዬን መቼም የኮንቲኔንታል አየር መንገድን ጉቦ ከፍሎ እዚህ ዘግይቶ እንዲደርስ እንዳላደረገው እጠረጥራለሁ። የሞከረም አይመስለኝም። read more
ለኢትዮጵያ የሚድያ አውታሮች በሙሉ
ከግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ጽ/ቤት
የሰኔ 1 1997 ዓ.ም የዴሞክራሲ ስማእታትን በሚመለክት የተላለፈ መልእክት
ሰኔ 1 2002 ዓ.ም
ዛሬ ሰኔ 1 ቀን ነው:: የዛሬ 5 አመት በእዚህ እለት በምርጫ የሰጠነው ድምጻችን ይከበር በማለት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄ ለማቅርብ በወጡ የሃገሬው ዜጎቸ ላይ የመለስ ዜናዊ አምባገነናዊ አገዛዘ በወሰደው አረመኒያዊ የእመቃ እርምጃ ከ40 በላይ የሚሆኑት ህይወታቸው አልፏል። በሽህ የሚቆጠሩ ዜጎችም አሰቃቂ ቅጥቀጣና የወህኒ እጎራ ተፈጽሞባቸዋል። read more
ሽምግልና ተዋረደ!!! ራሳቸውን “የሃገር ሽማግሌ” ብለው በሚጠሩ የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች ምክንያት ሽምግልና ረከሰ!!! ሽምግልና በደልን ማርዘሚያ ሆነ!!!
ሽምግልና አያት፣ ቅድመ-አያቶቻችን አዳብረው ያቆዩልን እጅግ የተከበረ ማኅበራዊ ተቋም ነው። ሽምግልና ተደጋግፎ ለመኖር፤ ግጭቶችን ለመቀነስ እና ፍቅርን ለማብዛት ማኅበረሰባችን በብዙ ምዕተ ዓመታት ልምድ ያዳበረውና ሞገስን የቸረው በየጊዜውም እያሻሻለው የሚሄድ ማኅበራዊ እሴት ነው። read more