በወ/ት ብርቱካን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ሁላችንም እንቅልፍ ሊነሳን ይገባል
ከግንቦት7 የተሰጠ መግለጫ
መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም
በአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ቀጭን ትእዛዝ በቃሊቲ እስር ቤት በግፍ ታስራ የምትገኘው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ መገኘቱን ለመረዳት ችለናል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና እርዳታ ያደረጉላት ዶክተሮች ተጨማሪ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ቢያሳስቡም፣ በዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ህክምና የማግኘት ሰብአዊ መብቷን እንደትገፈፍ ተደርጓል። read more
በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሀፊ የሆኑት አምባሳደር ካርሰን የአሜሪካ መንግስት በአፍሪካ ላይ የሚከተለውን ፖሊሲ ለመመርመር በተጠራ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መሄዱን ገልጸው፣ አገዛዙ ይህን ሁኔታ እንዲያስተካክል ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካን ሁኔታ በዳሰሰው ጽሁፋቸው “አንዳንድ ምሁራንና የፖለቲካ ተንታኞች የአፍሪካ ዲሞክራሲ ከተራራው አናት ላይ ደርሶ ወደታች ተመልሶ እየወረደ መሆኑንና በምሳሌነትም በአፍሪካ ውስጥ read more
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የወያኔው አገዛዝ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑትን ሁሉ እያሳደደ በመምታት ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህም ምክንያቱ በቁጥር በርካታ መሆናችንና ብዙ የተፈጥሮ ሀብት ያለን በመሆኑ ነው ብለዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ መድረክ የተባለውን ድርጅት ከመሰረቱት ፓርቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜም በተለያዩ አካባቢዎች ለምርጫ read more
በአዲስ አበባ ጉምሩክ ጽህፈት ቤት ውስጥ ታስረው የሚገኙትን በርካታ ነጋዴዎች አነጋገሮ ዘገባውን ያጠናቀረው ሪፖርተራችን እንደገለጸው፣ ነጋዴዎቹ በቫት ማጭበርበር ስም ታስረው የሚገኙት ድርጊቱን በመፈጸማቸው ሳይሆን ድርጅቶቻቸው ለወያኔ ኩባንያዎች ከፍተኛ ተወዳደሪ ሆነው በመቅረብና ስጋት በመፍጠራቸው ነው። እንደ ዘጋቢያችን ገለጻ የአያት ሪል ስቴት ባለቤትን ጨምሮ በርካታ የከተማው ነጋዴዎች በጉምሩክ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ለመመልከት መቻሉን ገልጿል። የአዲስ አበባ ነጋዴዎች በከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ read more
የትግራይ ተወላጆቹ ‘’የህዝቡን ጆሮ በማፈን እውነትን መሸፈን አይቻልም’’ በሚል ርዕስ ያወጡት የአቋም መግለጫ፣ ከምርጫ በኋላ አንዳንድ ተቃዋሚዎችን ወደ ፍርድ እናቀርባለን በማለት አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሁም የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮን ከሩዋንዳ እልቂት ጋር በማመሳሰል ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት እንደሚያፍን በይፋ መናገሩን የሚያወግዝ ነው።
የትግራይ ተወላጆቹ በዚሁ መግለጫቸው በቅርቡ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የይስሙላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሓዊና ሚዛናዊ እንዳይሆን የወያኔው አምባገነን አገዛዝ በምርጫው ለመሳተፍ እየተንቀሳቀሱ read more
የቪኦኤው ዘጋቢ ፒተር ሃይንላይን ከአዲስ አበባ በላከው ሪፖርት ላይ እንደገለጸው ብርቱካን ሚዴቅሳን ለመጎብኘት ቃሊቲ ድረስ ሄደው የነበሩ ባልደረቦቿንና ጓደኞቿን መጎብኘት አትቺሉም በማለት መከልከሉን ዘግቧል። ፒተር በዚሁ ዘገባው ባለፈው ቅዳሜ እለት የወያኔው አምባገነን አገዛዝ ትእዛዝ ፈጻሚ በሆነው አበበ ዘሚካኤልና የመድረክ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አካላትን ጨምሮ በሌሎች ጎብኚዎች መካከል ቃሊቲ እስር ቤት መግቢያ በር ላይ መፋጠጥ መፈጠሩን ገልጾ፣ በር ላይ በነበረው ፍጥጫ የሃገሪቱን የእስር ቤት ህግና ደንብ በሚያውቁት በነአቶ ስየ አብርሃ read more
በግንቦት97 ምርጫ ማግሰት በርካታ የወያኔ ባለስልጣናት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ውጭ አገር ማሸሻቸው በተለያዩ አለማቀፍ ሚዲያዎች ከተዘገበ በሁዋላ ፣ በዚህ አመትም ተመሳሳይ ድርጊት እየተፈጸመና ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ከውስጥ ወደ ውጭ በመሸሽ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ገንዘባቸውን በማሸሽ ላይ ከተሰማሩት ማካከል ቅድሚያውን የሚይዙት የወያኔ ባለስልጣናት መሆናቸውን የአዲስ አበባው ሪፖርተራችን ከባንኮች የተገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የዘገበ ሲሆን፣ በከፍተኛ የስልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙት ሰዎች ባለፉት read more
በሎንዶን የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የዘረኛና አምባገነኑን መለስ ዜናዊን ወደ እንግሊዝ መምጣት ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የተቃዉሞ ሰልፍ አደረጉ። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ የውጭ ሓገራት መንግስታትን ሳይቀር የፈለግሑትን አደርጋለሑ ምንስ ታመጣላችሑ የሚልና ፍጹም የሖነ አምባገነንነቱንና ጨካኝነቱን በግልጽ የሚያሳዩ ተግባራትን እያከናወነ ያለው ዘረኛው መለስ ወደለንደን የመጣበት ዋነኛው ምክንያት ቀደም ብሎ በኮፐን ሓገኑ ስብሰባ እንዳሰበው ያልተሳካለትን ነገር ግን ጥቂትም ፍርፋሪ ቢሖን ወደካዝናየ ማስገባት አለብኝ በሚል ቅዠት ቆርጦ የተነሳበትን የገንዘብ ማጋበስ ሕልም ተግባራዊ ለማድረግ እንደሖነ ታውቋል።
በትናንትናው እለት በተካሔደው በዚሑ የለንደኑ የኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዊያን ባሰሙት ጩኸት የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ጎርደን ብራዉን እንደኦሳማ ቢንላደን ካለ አሸባሪ ጋር የአለማችንን የሽብርተኝነት መዋጋት ዘመቻ ለማሳካት አጋር ማድረጋቸው አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ ባሰሙት ጩኸት በከፍተኛ ሑኔታ የሰው ልጆችን መብት እየጣሰ እንደሆነ ከሚታወቀውና ያለምንም የሕዝብ ይሑንታና ፈቃድ በስልጣን ወምበር ላይ ከተፎጠጠው መለስ ዜናዊ ጋር ቁጪ ብሎ የአለማቺን ሌላው ቺግር ስለሖነው የአየር ንብረት መዛባት ችግር መፍትሔ ለማፈላለግ መነጋገርም በጣም የሚያሳፍር ነው ብለዋል። በመቀጠልም ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያዊያን ባሑኑ ወቅት በጨፍጫፊው መለስ ዜናዊ በተቀነባበረ ሽብር ስቃይ እያዩና ለእልቂትም እየተዳረጉ እንደሖነ እነጎርድን ብራውን ሊገነዘቡ ይገባል ካሉ በሑዋላ እንግሊዝም ሖነች ሌሎች ሓገራት የመለስ ዜናዊን የአገዛዝ እድሜ ለማራዘም የሚያደርጉትን ድጋፍ ሊያቆሙ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። read more
በትናንትናው እለት የአሜሪካው ሬዲዮ የአማርኛ ዝግጂት ክፍል ባቀረበው ፕሮግራሙ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የመኢአድ እጩ ተወዳዳሪዎች ከገዢው ፓርቲ በደረሰባቸው የተለያዩ ተጸእኖዎች ምክንያት ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን መኢአድ ያስታወቀ ሲሆን ለምርጫ ተመዘገቡ ከተባሉ ፓርቲዎች ደግም አስራ ሰባት የሚሆኑት በምርጫው እንደማይሳተፉ ተገልጿል። ከዚሁ ዘገባ ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ እየታተም የሚሰራጨው ሪፖርተር ጋዜጣ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን አጣቅሶ የየፓርቲዎቹን የፓርላማ ምክርቤትና የክልል ተወዳዳሪ እጩዎች ቁጥር በእትሙ ያወጣ ቢሆንም ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጠ የተባለው የተወዳዳሪዎች ቁጥር ተወዳዳሪ ፓርቲዎቹ አስመዝግበናል ካሉት ተወዳዳሪዎች ቁጥር ጋር የማይጣጣምና የተለያየም መሆኑ ታውቋል። read more
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ዜጎችን በተለያዩ አቅጣጫዎችና ስልቶች ለስቃይ መዳረጉን ብሎም ወደ እስር ቤት እያጎረ መሆኑ ታወቀ። አዲስ አበባ የሚገኘው የግንቦት ሰባት ዘጋቢ ለእስር የተዳረጉ ንጹሃን ዜጎች ቤተሰቦችና የቅርብ ዘመዶች በማነጋገር ባደረገው ማጣራት በቂና ተገቢ ባልሆኑ ምክንያቶች ሰበብ አስባብ በመፍጠር በተለያዩ የንግድ ስራዎች ተሰማርተው የሚገኙ ስድስት ግለሰቦችን ወደ እስር ቤት መላኩ ታውቋል።
እነኚሁ የአምባገነኑ ወያኔ የእስር ሰለባዎች አቶ ጌቱ ወልደ ሰማያት በአዲስ አበባ ከተማ 22 ማዞሪያ አካባቢ የፋሲካ ስጋ ቤት ባለቤት፤ አቶ ከበደ የተባሉ የበረከት ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት፤ read more
ሰሞኑን መለስ ዜናዊ “ተቃዋሚዎች በምርጫ ክርክር ወቅት የሚናገሩትን እንቀዳና ከምርጫ በኋላ በማስረጃነት ተጠቅመን እንከሳቸዋለን” በማለት በፓርላማ ውስጥ ያደረገውን ንግግር የምርጫ አፈፃፀም ሥነ-ምግባር ደንብን የጣሰ ስለመሆኑ ደንቡን የፈረሙ ፓርቲዎች አመራሮች መግለጫ ሰጥተውበታል።
በእኛ እምነት የመለስ ዜናዊ ከላይ የተጠቀሰው ንግግርና ሌሎቹም የሰሞኑ መግለጫዎቹ በጥቅሉ ሲታዩ የጣሱት አንድ የምርጫ አፈፃፀም ሥነ-ምግባር ደንብን ሳይሆን ባጠቃላይ ሥነ-ምግባርን ነው። እንዲህ ዓይነት ንግግሮችን ከአዕምሮ ህመምተኛ አሊያም አንዳችም የሥነ-ምግባር ለከት ከሌለው ወራዳ ብቻ ነው መጠበቅ የሚቻለው። ሰሞኑን ከመለስ አንደበት ከተሰሙ በርካታ አሳፋሪ ንግሮች አራቱን ብቻ ነቅሰን እናውጣ። read more
በአምባገነንነቱና በዘረኝነቱ የሚታወቀው መለስ ዜናው አሻንጉሊት በሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንዳስታወቀው በቀጣዩ ምርጫ ከመጫወቻ ሜዳው ወጥተው በህግ ጥሰት ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን ፓርቲዎች መንግስት ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል በመዛት አስታውቋል። እንደመለስ አገላለጽ የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ እየሰሩ የሚገኙ ሃይሎች በተለያየ ደረጃ የሚታዩ መሆናቸውን፣ ይህን አደናቃፊ ስራ የሚሰሩ ሃይሎች ደግሞ ሆን ብለው አቅደው ከተነሱት የታጠቁት ሃይሎች ጀምሮ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ስህተቱን የሚፈጽሙ ህጋዊ እውቅና ያላቸውን የፖለቲካ ሃይሎችም የሚጨምር መሆኑን በይፋ ተናግሯል። read more
በአረመኔአዊው የወያኔው አገዛዝ በቃሊቲ ወህኒ ቤት በግፍ ታስራ የምትገኘው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመን በር ወ/ት ብርቱካና ሚደቅሳ ህክምና በመከልከሏ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከወህኒ ቤቱ አካባቢ ከተገኙ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህመሟ ከወህኒ ቤቱ ክሊኒክ አቅም በላይ በመሆኑ ለአንድ ግዜ ወደ ሆስፒታል መላኳን የገለጹት የመረጃ ምንጮች፣ ህክምና ያደረገላት ሀኪም ተጨማሪ ህክምና እንደሚስፈልጋትና በሌላ ሐኪም መታየት እንደሚገባት የገለጸ ቢሆንም ወህኒ ቤቱ ይህን read more
አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ሰላማዊና ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ እያለ በሚናገርበት ባሁኑ ሰዓት አዳዲስ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እየጫነ መሆኑን የደህንነት ምንጮቻችን ገለጹ። ምንጮቻችን እንደገለጹት ወያኔ መጋቢት 4 ቀን 2002 ዓ.ም ደማቅ አረንጓዴ ቀለም ባላቸው 8 ቮልቮ ተሳቢ የጦር ካሚዮኖች 16 ኮንቴይነር የጦር መሳሪያ ወደሁመራ አቅጣጫ ማጓጓዙ ታወቋል። በነኚሁ ከ16 በላይ የሚሆኑ አዳዲስ ኮንቴይነሮች ተጪኖ ወደ ሰሜን ምእራብ የተላከው የጦር መሳሪያ ፒ.ኬ.ኤም. ከባድ መትረጌስ በደገኑ ሁለት ፒክ አፕ ቶዮታ ወታደራዊ ፈጣን መኪኖችና የጦር መሪዎችም የታጀበ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል። read more
ደይሊ ሜይል የመረጃ ድረ ገጽ ባወጣው ጽሁፍ ቦብ ጊልዶፍ ቀደም ብሎ በቢቢሲ ሪፖርተር የቀረበውን ዘገባ ማጣጣሉንና መረጃ ከተገኘ ግን ይህን መንግስት እፋረዳለሁ ማለቱን አውስቶ፣ በወቅቱ የባንድ ኤይድ ዳይሬክተር በመሆን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈረንጆች አቆጣጠር ከ1985-91 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩትን የ 85 ዓመቱን ጆህን ጄምስ በመጥቀስ በርግጥም ከርዳታው ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ 20 በመቶ የሚሆነው ለጦር መሳሪኦያ ግዢ መዋሉን ማረጋገጣቸውን ይፋ አድርጓል። read more