ግንቦት7 የዘረኛውን አምባገነን መለስ ዜናዊ የ እንነጋገር ጥሪ የተለመደ ቅጥፈት ነው ሲል አጣጣለው

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቁንጮ የሆነው መለስ ዜናዊ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፡ ህገመንግሥቱን ተቀብለው በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እስከ ተስማሙ ድረስ ከማንኛውም ሃይል ጋር ለመደራደር እንደሚፈልግ ገልጾ በሃይል ከስልጣን ሊያባሪሩኝ ነው እያለ ዘወትር ከሚከሳቸው የግንቦት7 እና የ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋርም read more

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በጠረፋማ ክልሎች ሊዘረጋ ያቀደው አዲስ የቁጥጥር መዋቅር የትጥቅ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ መሆኑ ታወቀ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በጠረፋማ ክልሎች ሊዘረጋ ያቀደው አዲስ የቁጥጥር መዋቅር በአካባቢዎቹ የሚመላለሱ የትጥቅ ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ እንደሆነ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ዘገባ አሳይቷል።

አገዛዙ በአራት የጠረፍ ክልሎች “የገበሬ መንደር” የሚባል እና ከቀበሌ ያነሰ የቁጥጥር መዋቅር ለመመስረት መነሳቱን ሐሙስ እለት መዘገባችን ይታወሳል። ይህንንም እቅድ ለማስፈጸም፣ read more

በድህረ-ምረቃ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲሳተፉ ከተመረጡ ተማሪዎች ውስጥ ሰማንያ በመቶ የሚሆኑት የአንድ ብሔር ተወላጆች ናቸው የሚል ስሞታ ቀረበ

ባመጧቸው ጥሩ ውጤቶች የተመለመሉ የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን በአዳማ እና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተሰብስበው ስለ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲሰበኩ እንደሰነበቱ መጥቀሳችን ይታወሳል።

የግንቦት 7 ድምጽ የአዲስ አበባ ሪፖርተር አጠናቅሮ በላከው ተከታይ ዘገባ እንዳስታወቀው፥ በስልጠናው ፍፃሜ ላይ በሁለቱ የስልጠና ቦታዎች መቶ መቶ ተማሪዎች ለሁለተኛ ዲግሪያቸው read more

የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ አለ የሚለው የደብል-ዲጂት የኢኮኖሚ እድገት አጠያያቂ እንደሆነ ቀጥሏል

ወያኔ በኢትዮጵያ አስገኝቻለሁ የሚለው የደብል-ዲጂት የኢኮኖሚ እድገት ከኢትዮጵያውያን አልፎ በአንዳንድ የአለማቀፍ የመረጃ አውታሮች ዘንድ ጥያቄ ማስነሳት መጀመሩ እየተስተዋለ ነው።

ፋይናንሻል ታይምስ የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ ሰሞኑን ያወጣው ጽሁፍ፣ በኢትዮጵያ አለ የሚባለው እና አንዳንድ የአለማቀፍ ባለሙያዎች የሚቀበሉት የኢኮኖሚ እድገት ወሬ ምንጩ በውል read more

ሁለገብ ትግሉ ዲያስፓራው ደጃፍ መጥቶለታል፤ ለእራሳችንና ለአገራችን ነፃነት በአርበኝነት እንነሳ!

የወያኔ ዘረኝነት፣ ትምክህት እና የስሌት ስህተት እርስበርስ የሚመጋገቡ ናቸው። ትዕቢቱ “ስህተቱን” ግዙፍ ሲያደርገው፤ ዘረኝነቱ ደግሞ “ስህተቱን” አስነዋሪና አሳፋሪ ያደርገዋል። በዘረኝነትና ትዕቢት ከተነዱ በርካታ ስህተቶች አንዳንዱን ለአብነት ያህል እናንሳ።

  1. ወያኔ ለእኩልነት ታገልኩ ብሎ ለዘረኝነት ተቋማዊ መሠረት ሰጠ። ማንም እንደሚገነዘበው ለእኩልነት በመታገል እና ዘረኝነት በማስፈን መካከል ያለውን ልዩነት የትየለሌ ነው። ይህም በመሆኑ “እኩልነትን አሰፈንኩ” ባለበት አገር ለእኩልነት የሚታገዙ read more

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ለስለላ ያሰለጠናቸውን የትግራይ ብሔር አባላት በተለያዩ የአገሪቱ ወረዳዎች በአማካሪነት እየመደበ መሆኑ ታወቀ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ከትግራይ ብሔረሰብ ተመልምለው ከአንድ አመት በላይ የስለላ ሙያ ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ ወጣቶችን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ወረዳዎች በአማካሪነት ስም እየመደበ መሆኑን የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ከሰሜን ኢትዮጵያ ባስተላለፈው ዘገባ አስታውቋል። read more

የከፍተኛ ትምህርት እድል ከተሰጣቸው የሰሞኑ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስልጠና ሰለባዎች ውስጥ ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው ታወቀ

የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲን እንዲቀበሉ ለማድረግ ባለው እቅድ ሰሞኑን መቀሌና አዳማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በግዴታ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስልጠና እንዲወስዱ የተደረጉት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሰቃዮች ስልጠናቸውን አጠናቀዋል። ስልጠናውን ከተከታተሉት ውስጥ 200 የሚሆኑት read more

ወያኔ በኦሮሚያ እና በደቡብ የገጠር ቀበሌዎች በስራ ላይ ያዋላቸውን የቁጥጥር መዋቅሮች ወደ ሌሎች ክልሎች ሊያስፋፋ ነው ተባለ

የወያኔ አገዛዝ ባለፉት በርካታ አመታት በአንዳንድ የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች አካባቢዎች በስራ ላይ ያዋላቸውን ከቀበሌ ያነሱ የቁጥጥር መዋቅሮች ወደ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች ለማስፋፋት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታውቋል።

የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ከኢትዮጵያ አጠናቅሮ በላከው ዘገባ መሰረት፥ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ የሚመራ ቡድን በነዚህ ክልሎች “የገበሬ መንደር” read more

በግንቦት 15ቱ የምርጫ ተውኔት መቶ በመቶ ማሸነፉን ያወጀው ወያኔ፣ ስለምርጫው ትክክለኛነት ህዝቡን ለማሳመን ዘመቻ መጀመሩ ታውቋል

የወያኔ አገዛዝ በግንቦት 15ቱ የምርጫ ተውኔት መቶ በመቶ መርጦኛል ያለውን ህዝብ መልሶ ስለምርጫው ትክክለኛነት ለማሳመን ዘመቻ መጀመሩን የግንቦት 7 ድምጽ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ባስተላለፈው ዘገባ አስረድቷል።

በወያኔ ቁጥጥር ስር በሚገኙ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን ተቀጥረው የሚሰሩ ልማታዊ ጋዜጠኛ ተብዬዎች በተለያዩ ክልሎች የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ወያኔ የፓርላማውን መቀመጫ read more

በወልቃይት ጠገዴ እና በተቀረው የአገሪቱ ክፍል የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም የትብብር ትግል ጥሪ ተደረገ

በወልቃይት ጠገዴ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም የኢትዮጵያውያን የትብብር ትግል አስፈላጊ ነው ሲሉ ልሳነ-ግፉአን የተባለ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር ገልጸዋል።

አቶ አባይ መንግስቱ ለግንቦት 7 ድምጽ ሬድዮ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፥ ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ወልቃይት ጠገዴን ከተቆጣጠረ ወዲህ በአካባቢው ነባር ነዋሪ read more

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ቃል ገብቶ ያልፈጸመው የወያኔ አገዛዝ አሁንም የምግብ ዋስትናን አረጋግጣለሁ ሲል ደሰኮረ

የወያኔው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሱፊያን አህመድ፥ “ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአለም ፊት በተመጽዋችነት ስሟ አይነሳም” ማለቱ የወያኔው አገዛዝ ከዚህ ቀደም የገባቸውን ተመሳሳይ ቃላት እንዳስታወሳቸው የፖለቲካ ተንታኞች ገልጸዋል።

የቀድሞው የወያኔ ታጋይ አማረ አረጋዊ ንብረት የሆነው read more

ስብሃት ነጋ ከአንድ የቻይና ኩባንያ 150 ሚሊዮን ዶላር ጉቦ ተቀብሏል ተባለ

ከወያኔ ዋና ባለስልጣናት አንዱ የሆነው ስብሃት ነጋ ከአንድ የቻይና ኩባንያ በደላላነት ስም የመቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር ጉቦ ተቀብሏል ሲል አንድ አዲስ መጽሃፍ ወንጅሏል።

አዲስ ቮይስ የተባለው የመረጃ ድረ-ገጽ የገመገመው እና ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በተባሉ read more

በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቻይና ኤምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሐሙስ ሐምሌ 29 ቀን 2002 ዓም በቻይና ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አገሪቱ ለዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ የምታደርገውን ድጋፍ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ፥ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ እንዳያገኝ ለሚያደርገው እገዳ ቻይና የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል። አገዛዙ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮን፣ የጀርመን ድምጽ ራድዮን፣ read more

የወያኔ እና የደጋፊዎቹ ኩባንያዎች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር የሚያወጣ የመንግስት ኮንትራት ለብቻቸው ተቀራመቱ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ከ4.1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ስድስት የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶችን ለአምስት ኩባንያዎች ሰጥቶ ስምምነት መፈራረሙን ሪፖርተር የተባለውና ከገዢው ፓርቲ ጋር ትስስር ያለው ጋዜጣ ዘግቧል።

ኩባንያዎቹም፥ መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ ሱር ኮንስትራክሽን፣ እንይ ኮንስትራክሽን፣ ኢትዮ-ጀነራል ኮንስትራክሽን እና ማክሮ ኮንስትራክሽን መሆናቸው ታውቋል። read more

የንግድ ባለቤቶች ግብርን በተመለከተ ስሞታ እያሰሙ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የትናንሽ ንግድ ባለቤቶች ግብር በዝቶብናል በማለት ስሞታ እያሰሙ እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን ዘገባ አሳይቷል።

የግንቦት 7 ድምጽ ዘጋቢ ተዘዋውሮ ያናገራቸው ግለሰቦች የተጫነባቸው መጠን ከአቅማቸው በላይ እንደሆነና መክፈል ተስኗቸው እስር ቤት እንሄዳለን ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል። ግለሰቦቹ፥ ለመጣጣር እና ልጆቻቸውን ለማዳን ሲሉ መንግስት ለጥቃቅን እና መለስተኛ ንግዶች የሚሰጠውን ብድር በመውሰድ read more

Page 4 of 22« First...«23456»1020...Last »
© 2008-2009