ኢሳትን ከፋሺስታዊ አፈና የመታደግ ግዴታ አለብን!

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን (ኢሳት) በሚመለከት ሰሞኑ አዲስ አበባን ያዳረሰው ጭውውት የሚከተለውን ይመስላል።

“ዳዊት ጎልያድን ገደለ!”

“በምን?”

“በወንጭፍ!”

“ኢሳት ኢቲቪን ከሳተላይት አወረደ !”

“በምን?”

“ገና ባልታየው ችሎታው”

ይህ ጭውውት እንደ እረኛ ዘፈን ምስጢሮችንና ሕዝባዊ መልዕክቶችን ይዟል። read more

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ታቦ ኢምቤኪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተመርቂ ተማሪዎች በዓል ላይ በመገኘት የተደረገላቸውን የክብር የዶክትሬት ዲግሪ ማዕረግ ሲቀበሉ ያደረጉት ንግግር

ሐምሌ 17 2002 (JULY 24, 2010)

ክቡራትና ክቡራን፦

ፕሬዚደንት እንድሪያስ እሸቴን እና ዩኒቨርቲሲውን ባጠቃላይ ይህንን አንጋፋ አፍሪካዊ የትምህርት ማእከል እንደ ክቡር ተመራቂ እንድቀላቀል ስለሰጡኝ ክብር እና ልዩ ስጦታ ከልቤ ላመሰግን እወዳለሁ። ይህ ከኢትዮጵያ ጋር ልዩ ትስስር የሚሰጠኝ አዲስ ሁኔታ፣ በብዙ መንገድ ወደ እናት አገር ከመመለስ ጋር የሚተካከል ነው። read more

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በአምስተርዳም ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ባዘጋጁት በዓል ላይ ሁከት ለመፍጠር የጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

በሆላንድ ዋና ከተማ አስምተርዳም በኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተዘጋጀ በአል ላይ የወያኔ ቅጥረኞች ሁከት ለመፍጠር ያደረጉት ሙከራ በዝግጅቱ ታዳሚዎች እንደከሸፈ ለዝግጅት ክፍላችን ከስፍራው የደረሰ ዘገባ አሳይቷል።

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 24 በአምስተርዳም የተካሄደው 8ኛው አመታዊ የኢትዮጵያዊያን-አውሮፓውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና አውሮጳውያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። read more

የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስልጠና የፈጠረው ድብርት እንደተስፋፋ ነው፤ የሰሞኑ ሰለባዎች የዩኒቨርሲቲ ሰቃዮች መሆናቸው ታወቀ

የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያውያን በሙሉ አብዮታዊ ዴሞክራሲን እንዲቀበሉ ለማድረግ ባለው እቅድ መሰረት ሰሞኑን የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሰቃዮችን ያለ ፈቃዳቸው ሲሰብክ መቆየቱ ታውቋል።

አገዛዙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ላይ የተመሰረ አንድ አመለካከት እንዲኖራቸው እና ተቃውሞ እንዲያቆሙ የማድረግ እቅድ እንዳለው read more

ወያኔ የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በሶስት እጥፍ ጨምሬያለሁ ማለቱን የአገሪቱ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባለሙያዎች “የማይመስል ነገር” አሉት

የወያኔ አገዛዝ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የአገሪቱን የደን ሽፋን በሶስት እጥፍ ጨምሬያለሁ በማለት ያወጣውን ሪፖርት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባለሙያዎች “እውነትነት የጎደለው እና ጨቅላ” እንዳሉት አፍሪክጄት የተባለ የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል።

በወያኔ ቁጥጥር ስር የሚገኘው የግብርና ሚኒስቴር በዚህ ወር ባወጣው read more

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ትርፋማነት በታወጀ ማግስት በወደፊት እጣው ላይ ጥያቄ ተቀሰቀሰ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ትርፋማ ከሆኑ አየር መንገዶች አንዱ ነው በተባለ ማግስት አንዳንድ የተቋሙ ሰራተኞች በወደፊት እጣው ላይ ጥያቄ እያነሱ ነው።

ናዝሬት ዳት ካም የተባለው የመረጃ ድረ-ገጽ “ኤር ትራንስፖርት ወርልድ” የሚባለውን ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአለም 16ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 1ኛው read more

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ የወረዳ መቀመጫዎችን እየሞላ ነው ተባለ

በ2000 አመተ ምህረቱ ህገ-ወጥ የማሟያ ምርጫ ተመርጠዋል በሚል በአዲስ የተለያዩ የቀበሌና የወረዳ አስተዳደራዊ መቀመጫዎችን የተረከቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለ ምርጫ በተሰበሰቡ አዳዲስ ሹመኞች እየተተኩ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። read more

በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ግፍ ቀጥሏል፤ በደቡብ አፍሪካ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው መቁሰላቸው ተዘገበ

የተሻለ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፍለጋ ወደ ውጭ በሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው እንግልት ቀጥሎ በዚህ ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው መጎዳታቸው ተዘግቧል።

“ፍሮም ዘ ኦልድ” የተባለ የደቡብ አፍሪካ የዜና ድረ-ገጽ እንደዘገበው፣ የሶስቱ ኢትዮጵያውያን መኪናዎች በቁጣ በተሰባሰቡ የአገሬው ሰዎች ከተሰባበሩ በኋላ read more

በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ከ26 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

ቅዳሜ ሃምሌ 24 ቀን 2002 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሃያ ስድስት ሰዎች ሞተው በርካቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፣ በተለምዶ 18ኛው ማዞሪያ ተብሎ read more

ታቦ ኢምቤኪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ንግግር በዘረኛው እና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ መሪዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ታወቀ

የንግግሩን ሙሉ ቃል ከዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል

የቀደሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት እና እውቁ የጸረ-ዘረኛነት የነጻነት ታጋይ ታቦ ኢምቤኪ ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክተሬት በተቀበሉበት ክብረ በአል ላይ ያደረጉት ንግግር አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል።

ባለፈው ቅዳሜ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የተማሪዎች ማስመረቂያ በአል ላይ በመገኘት የክብር ዶክተሬት ዲግሪያቸውን የተቀበሉት ፕሬዚደንት ኢምቤኪ ያደረጉት read more

የአሜሪካ መንግስት በሙስና የተዘፈቁ አፍሪካውያን መሪዎችን ገንዘብ በቁጥጥር ስር አውላለሁ አለ

አሜሪካ ከዚህ በኋላ በሙስና በተዘፈቁ መሪዎቻቸው አማካኝነት ከአፍሪካውያን ለተሰረቀ ገንዘብ ማከማቻነት አታገለግልም ሲሉ የኦባማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኤሪክ ሆልደር መናገራቸውን የዩጋንዳው ደይሊ ሞኒተር ዘግቧል።

ባለፈው ሳምንት በዩጋንዳ በተካሄደው የአፍሪካ አንድነት ጉባኤ ላይ ለአገራቱ መሪዎች ራሳቸው ባደረጉት ንግግር፣ የአሜሪካ መንግስት ከአፍሪካ ተሰርቆ በምእራባውያን read more

የወያኔ አገዛዝ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የሚፈጽመው ኢ-ሰብአዊ እርምጃ ሳይገታ ቀጥሏል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሊፈናቀሉ ነው

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለከተማ ልማት በሚል እንደሚፈናቀሉ የተነገራቸው በርካታ ነዋሪዎች ያለመድረሻ እንደቀሩ ለግንቦት 7 ድምጽ የአዲስ አበባ ዘጋቢ ስሞታቸውን ገልጸዋል።

215 የሚሆኑት ዜጎች የሚፈናቀሉበት ምክንያት መኖሪያዎቻቸው ባሉበት ቦታ ኮንዶሚኒየሞች እንዲሰሩ ስለታቀደ ነው። ምንም እንኳ በወያኔ ቁጥጥር ስር ያሉ መገናኛ ብዙሃን ተፈናቃዮቹ ከፍተኛ ካሳ እንደተሰጣቸው ቢናገሩም፣ ከዚህ ቀደም ከልደታ አካባቢ የተፈናቀሉ read more

ዘረኛ የትምህርት ሥርዓትን ለመቀየር ዘረኛውን አገዛዝ ከሥልጣን ማባረር ግድ ነው!!!

ትምህርት የእውቀት አድማስን ካላሰፋ፤ አዳዲስ ክህሎቶችን ካላሳወቀ፤ የእለት ከእለት ኑሮን ካላሻሻለ እና አዎንታዊ የባህርይ ለውጥ ካላመጣ ፋይዳው እምን ላይ ነው?

የወያኔ የትምህርት ሥርዓት ከላይ ከዘረዘርናቸው ውስጥ ለአንዱም የተዘጋጀ አይደለም። ወያኔ ትምህርት ቤቶችንና ዩኒቨርስቲዎችን ከእውቀትን መገበያያነት ይልቅ እጅግ ኋላቀር የሆነ ዘረኛና ጎጠኛ አስተሳሰብ ማራቢያና ማሰራጫ ተቋማት አድርጎዓቸዋል። read more

ዘረኛውና አምባገናዊው የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ስርጭት እንደገና ማፈኑ ታወቀ

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሳት) በዚህ ሳምንት እንደገና መታፈኑን እና ስርጭቱ መቋረጡን ድርጅቱ በለቀቀው መግለጫ አስታወቀ።

መግለጫው አፈናውን የሚያኬሄደው ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ስለመሆኑም ድርጅቱ ማስረጃ እንዳለው ገልጿል። አገዛዙ ኢሳት ቴሌቪዥንን ለማፈን በሚያካሄደው read more

ኢትዮጵያውያን በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት እየተንገላቱ ባሉበት የወያኔ አገዛዝ ለጎረቤት አገሮች የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ ዝግጅቱን መፈጸሙን ገለጸ

አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ክፍላት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የንግድ ድርጅቶቻቸው በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት ምክንያት እየተንገላቱ ባሉበት ወቅት የወያኔ አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል ለጎረቤት አገሮች ለመሸጥ ዝግጅቶች አጠናቅቄያለሁ ማለቱ ተዘግቧል። read more

Page 5 of 22« First...«34567»1020...Last »
© 2008-2009