Home » Archives by category » አማርኛ

የፈሪ ዱላ ነፃነትን አያስቀርም !

ህወሃቶች ኢትዮጵያን “ለመምራት” ያላቸው አቅም ተሟጦ አልቋል። ፍርሃት አቅላቸውን አስቷቸዋል። ፍርሃታቸው ጭካኔን ወልዷል። ይህ ጭካኔያቸው ወሰን አጥቷል። ልጥ ባዩ ግዜ እባብ እየመሰላቸው ልጡን በቆመጥ ሲደበድቡ ውለው ያድራሉ። ፍርሃት ያ ደካማ ማሰቢያቸውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶታል። የፈሪ ዓይን ማየት እንደማይችል፤ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ከህወሃቶች ተርድተናል። እኛ ግን እንዲህ እንላለን ህወሃቶች ዓይናችው እያየ፤ ጆሮዋቸውም እየሰማ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን [...]

ብሄራዊ ብድር የዕድገታችን ምንጭ እንጂ የደኅንነታችን ስጋት ሊሆን አይገባም

እኛ ሰዎች ሁሌም ከምንፈራዉና ከምንጠላዉ አንዴ ከገባንበት ደግሞ የቱንም ያክል ብንጠላዉና ብንፈራዉ እየደጋገምን የምንዘፈቅበትና በቀላሉ የማንወጣዉ አዘቅት ቢኖር ብድር ወይም የብድር ልጅ የሆነዉ ዕዳ ነዉ። ብድር ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ የንግድ ድርጅቶች፤ ማዘጋጃ ቤቶች፤ ትላልቅ ኮርፓሬሺኖችና አገሮች በአጭርና በሪጂም ግዜ የሚያጋጥማቸዉን የገንዘብ እጥረት የሚሸፍኑበት መንገድ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ብድር ወደፊት በምናገኘዉ ገቢ ዛሬን መኖር [...]

Read More

ለሀገር ነጻነት የወጣቱ ተሳትፎ ቀጣይነት ይኑረው!

ከ1997 ምርጫ ማግስት ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጣቶችና በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ዜጎች ለሀገራቸው የዲሞክራሲ መብት መከበር እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ላቅ እያለ መምጣቱ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ይህን ተከትሎ ዛሬ ወጣቱ የወላጆቻችን ደምጽ ይከበር፣ ኢትዮጵያዊነት በዘረኝነት አይፈተንም! ነጻነት ዳቦ አይደለም! እስራትና ግድያ በኢትዮጵያ ይቁም! የወያኔ አገዛዝ በቃን! በሚሉ በበርካታ ወጣቶች ጩኸት የወያኔ ሹማምንትና አገልጋዮቹ ላይ [...]

Read More

ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ለተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ትንታግ የሆኑትን ወጣት ፖለቲከኞች በሽብር ወንጀል ተካፍለዋል፣ ድርጊቱን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ ህዝብን ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል የፈጠራ ክስ አጎሮ ስቃይ እየፈጸመባቸው ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት አራቱ ወጣት ፓለቲከኞችን እና በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ሌሎች 6 ተከሳሾች ለቀረበባቸው የፈጠራ ክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ [...]

Read More

ታሪክን ማደብዝዝም ማጥፋትም አይቻልም!

በአለማችን በተለይ አፍሪካ ዉስጥ የአገርን ብሄራዊ ኃብት የሚዘርፉ፤የህዝብን መብት የሚረግጡና አገርን እነሱ ባሰኛቸዉ አቅጣጫ ብቻ ይዘዉ የሚነጉዱ አያሌ ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት አሉ። እነዚህ ህዝብን የሚበድሉ መንግስታት ሁሉም በጥቅሉ አምባገነን ይባሉ እንጂ በመካከላቸዉ ጎላ ብሎ የሚታይ ትልቅ ልዩነት አለ። ሀኖም የቱንም ያክል ልዩነት ቢኖርም እንደ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ የሚንቁና የኛ ነዉ የሚሉትን አገር [...]

Read More

የሰንደቅ አላማችን ጠላት ወያኔና ወያኔ ብቻ ነዉ!

ሰንደቅ አላማ ለአንድ አገር ህዝብ የኩራት፤ የአልበገር ባይነት፤ የአንድነትና የታሪክ ተከታታይነት ምልክት ነዉ። ሰንደቅ አላማ በአንድ በኩል የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ ክወዲሁ እያሳየን እየዟችሁ የሚለን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በምናብ ወደኋላ እየወሰደን የድልና የመስዋዕትነት ታሪላችንን የሚያስታዉሰን የነጻነት፤ የሠላምና የብሩህ ተስፋ ማህደር ነዉ። የአገራቸን የኢትዮጵያ አረንጓዴ፤ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ አላማ ትናንትናና ከትናንት ወዲያ በተስፋፊዎች አለመደፈራችንን ብቻ ሳይሆን ዛሬም [...]

Read More

እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ደብዳቤ መጻፏን ወያኔ አረጋገጠ

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በተመለከተ ለወያኔዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መጻፋቸውንና ወያኔም አቋሙን ግልጽ ማድረጓን የወያኔዉ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሚኒስትሩ አቶ ሬድዋን ሁሴን ተናገረ። ሬድዋን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ዴቪድ ካሜሩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደብዳቤ መጻፋቸውን የተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች መዘገባቸውን ሰምቻለሁ ካለ በኋለ “ለምን ጻፉ ማለት አይቻልም፤ [...]

Read More

የፈርዖኖች ድንኳን እየፈረሰ ነው

“ዓረብ ስፕሪንግ” እየተባለ ስለሚነገረው ህዝባዊ አብዮት ብዙ ተብሏል። ያ ህዝባዊ አመፅ ለውጥ አምጥቷል።ማን ይነካኛል ብሎ ዜጎቹን መከራ ሲያበላ የነበረው የቱኒዚያው ቤኒ ዓሊ ዛሬ የተረሳ ግለሰብ ሁኗል። እኔ ከሌለው ይህች አገር ትጠፋለች ሲል የነበረው ጋዳፊ ከተደበቀበት የአይጥ ጉድጓድ ውስጥ ተጎትቶ ወጥቶ እንደ ውሻ ተቀጥቅጦ ሙቷል። ሆስኒ ሙባረክም እንዲሁ ተርስቶ ቀርቷል። የየመንም አምባገነን አገር ጥሎ ሂዷል።በሶሪያም አምባገነኖች [...]

Read More

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ላለፉት 3 ወራቶች ያሰለጠናቸውን የአምስተኛ ዙር ታጋዮች አስመረቀ

አገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛውና በከፋፋዩ የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ መዳፍ ውስጥ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደትና መከራ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመገርሰስ ወደ ክብር ለመለወጥ፤ ብሎም የናቋትን እና ያዋረዷትን ጉጅሌዎች በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ማድረግን ቀዳሚ አላማው አድርጎ ወደ ዱር የከተተውና፤ በአገራችን የነገሰውን ፍጹም አምባገነናዊ አገዛዝ በሚገባው ቋንቋ ሁሉ ለማነጋገር እጅግ በዘመነ ሁኔታ እየተደራጀ [...]

Read More

አማራ! አማራ! አማራ! ብቸኛዉ የወያኔ ዘፈን

“ሞኝና ወረቀት የያዙትን አይለቁም” የሚለዉ ቆየት ያለ ያለ የአገራችን ተረት ትርጉም ያልገባዉ ሰዉ ካለ የቅኔ አዋቂ መፈለግ ወይም መጽሐፍ ማገላበጥ የለበትም። ማድረግ ያለበት ቀላል ነገር ቢኖር ወያኔንና የወያኔን ስራ ትኩር ብሎ መመልከት ብቻ ነዉ። በመሠረቱ ወረቀት የያዘዉን አለመልቀቁ ወያኔን ጨምሮ ሁላችንም የምንፈልገዉ ነገር ነዉና ወረቀት ሊመሰገን ይገባል። ሞኝ የያዘዉን አለመልቀቁና ከግዑዙ ወረቀት ጋር መነጻጸሩ ግን [...]

Read More