December 23, 2011 ርእሰ አንቀጽ የኢትዮጵያን ፓለቲካና ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው የድሆችን ደም እየመጡ ያሉት የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላትና ሎሌዎች እአአ ከ1990 መጀመሪያ እስከ 2007 መጨረሻ በነበሩት 18 ዓመታት ውስጥ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ ማሸሻቸው የተባበሩት መንግሥታት የልማት መርሃግብር (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) በጥናት ማረጋገጡን ይፋ ካደረገ አንድ ዓመት አልሞላውም። ስምንት ቢሊዮን ሶስት መቶ ሚሊዮን (8.3 ቢሊዮን) የአሜሪካ ዶላር [...]
December 16, 2011 ርእሰ አንቀጽ ሰሞኑን “የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን” የሚል የማስመሰያ ስያሜ የተሰጠው ድግስ በመቀሌ ከተማ ተጥሎ ሲበላና ሲጨፈር ተከርሟል። ይህ ዓመታዊ ድግስ እንደ ነገሥታት ግብር ተገዢዎች ተገዢነታቸውን፤ ምስለኔዎች ደግሞ ታማኝነታቸውን ለገዢዎቻቸው የሚያረጋግጡበት መድረክ ነው። ይህ በዓል የትግራይ ገዢ ጉጅሌ በትግራይ ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራም፣ በኦሮሞም፣ በሲዳማም፣ በወላይታም፣ በአፋርም፣ በሶማሊም፣ በጉራጌም፣ በሃድያም፣ በአንዋኝዋክም፣ [...]