Home » Archives by category » G7 Editorial

አገራዊ ጥሪ ለመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የኢትዮጵያ የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላትን ከአለቆቻቸው ለይቶ ይመለከታል። የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት ከፍተኛ ሹማምንት ከህወሓት የተቀዱ፣ ለህወሓት ሥልጣን የቆሙ፣ ዘረኞች፣ ፋሽስቶችና ሙሰኖች መሆናቸው በገሃድ የሚታወቅና በተደጋጋሚ ጥናቶችም የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። በዘመነ ወያኔ የሠራዊት አዛዥነት ሹመት መሥፈርቶች ዘር፣ የፓለቲካ አመለካከትና ለህወሓት ያላቸው ታማኝነት ነው። በዚህም ምክንያት ሁሉም ቁልፍ የአዛዥነት ቦታዎች የተያዙት [...]

ወያኔ አንዳርጋቸውን ያፈነበት እለት የሚረግምበት ቀን ሩቅ አይደለም!

የህወሃት ጉጅሌ እንደማንኛውም አምባገነን ከፊት ከነበሩ አምባገነኖች ቅንጣት ትምህርት አልተማረም። ወያኔዎች በእብሪት የያዙት ስልጣንና ከህዝብ የዘረፉትን ንብረት የሚያጡት እየመሰላቸው በባነኑ ቁጥር የነጻነት አርበኞችን በማፈን በመግደልና በማሰቃየት ፍርሃታቸው የተወገደ ይመስላቸዋል። ወያኔ የእኛ መሪና የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት አርበኛ በሆነው አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ ያካሄደው አፈና ከአፈናውም በሆላ በሚያደርሱበት አካላዊ ስቃይ ፍርሃታቸው የሚወገድ ወይም ስርአታቸው ከሞት የሚተርፍ መስሏቸው ከሆነ [...]

Read More

የወያኔን የጥፋት ድግስ እናምክን!

ኢትዮጵያን የሚገዛው ጉጅሌ ሀገራችንን እየወሰደበት ያለው አደገኛ አቅጣጫ አሳሳቢ ከመሆን አልፎ የአደጋውን መራራ ፍሬ ማየት ከጀመርን ሰነበትን። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ወሳኝ ከሆነው የወደፊቱ የጋራ ጥቅማቸውና ህልውናቸው በበለጠ ልዩነታቸውና ያለፈ ታሪካቸው እንደዋናው ነገር እየተቆጠረ ለሚሰበከው ስብከት የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ባይሆን ኖሮ እስካሁን ብዙ ጥፋት በደረሰ ነበር። ህወሃት በህዝቡ ውስጥ የኖረውን ልዩነት የጠብ፣ የግጭትና የመፈራራት መሰረት በማድረግ [...]

Read More

ቀና ብለን የምንሄድበት ጊዜ አየመጣ ነው! ጎበዝ ተነሳ!

ጉጅሌዎቹ አይገባቸውም እንጂ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮች የለውጥን ደመና ኣርግዘዋል። ወንዞችም ተራሮችም የለውጥ ማዕበል ማቆብቆቡን አያበሰሩ ናቸው። የቀደሙት ገዢዎች መረጃ የሚያገኙት እረኛ ምን ይላል ብለዉ እየጠየቁ ነበር። የአሁኖቹ አገር አጥፊ ገዢዎች ምሳሌ ያደረጉት ካድሬዎቻቸውን ብቻ ሆነ እንጂ ዛሬም የአገራችን እረኞች የለውጥን መምጣት በሚያምር ቅላጽያቸው አያንጎራጎሩ እንዲህ አያሉን ነው፣ የሀገሬ ጉብል የሰማውን እንጃ የጎንደሬው ጉብል የሰማውን እንጃ [...]

Read More

የወያኔ ግፍ ለከቱን አልፏል!

የወያኔ ጉጅሌ ራሱ ከሳሽ፣ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ለሚችለው በላይ ሆኗል። የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች [...]

Read More

ወጣቶች እየመጡ ነው!!!

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ “ወጣት፤ የነብር ጣት!” በሚል ርዕስ ጥር 26 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር 142 ባወጣው ርዕሰ አንቀጹ “ወጣት በነብር ጣት መመሰል ያንሰው እንደሆን እንጂ አይበዛበትም። የኢትዮጵያም ወጣት የነብር ጣት ሆኖ ያውቃል … አሁንም ነው” ብሎ ነበር። በዚያ ጽሁፍ እና በሌሎችም አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ እንዳብራራው ግንቦት 7 በወጣቱ ችሎታና ተነሳሽነት ላይ ከፍተኛ እምነት [...]

Read More

ግንቦት 20- የመከራ የስደትና ዘረኝነት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ

ወያኔ ለንግሥና የበቃበትን ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓመተ ምህረት መታሰቢያ በአል ለ23ኛ ጊዜ ለማክበር ሰሞኑን ደፋ ቀና ሲል ሰንብቷል። በኢትዮጵያ ግብር ከፋይ ህዝብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃንና በተለያዩ የውጪ አገራት የተመደቡ የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤቶች በዚሁ የግንቦት 20 በአል አከባበር ሥራ ተጠምደው ከርመዋል። ለኢትዮጵያ አገራችንንና ለህዝቦቿ ባርነትን ለህወሃትና ለግብረ አበሮቹ ደግሞ አልመውት የማያውቁትን ድሎትና ብልጽግናን ያጎናጸፈው ግንቦት [...]

Read More

በራችንን ከፍተን የወያኔን ሌብነት ማቆም አንችልም!

ግንቦት 7 የወያኔ ጉጅሌና ሎሌዎቹ ስልጣናቸውን በህዝብ ፈቃድ ላይ እንዳልቆመ አሳምረው ያውቃሉ። ነጻ የህዝብ ምርጫ ቢኖር ምን እንደሚሆኑ የዛሬ ዘጠኝ አመት በአይናቸው አይተዋል፣ በጀሮቸው ሰምተዋል። ከዚያ ተመክሮ ተነስተው ዳግም የህዝብ ፈቃድ ላለመጠየቅ ምለዋል። ቅዱሱን የዴሞክራሲና የፍቅር መንገድ ሳይሆን ሳይጣናዊውን የከፋፍሎና አናክሶ የመግዛትን መንገድ ዋና ምርጫቸው አደርገው ከወሰዱ ሰንብተዋል። የፍትህና የዴሞክራሲ ሂደት በኢትዮጵያ እነሱ እስካሉ ድረስ [...]

Read More

ትኩረት በህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ ላይ ይሁን!!!

ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ መንታ መንገድ ላይ ትገኛለች። በአንድ በኩል ህወሓት እና አገልጋይ ድርጅቶቹ በተለይም ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደህዴድ የተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃዉሞ ለመሸፈን የሕዝብ ለሕዝብ ጠብ ለመጫር የተቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ነው። በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዘርን መሠረት ያደረጉ ስድቦች፣ ዘለፋዎችና ጥቃቶች እንዲኖሩ በካድሬዎቻቸውና በቅጥረኞች አማካይነት እየጣሩ ነው። በዚህ እኩይ ተግባር ውስጥ ባለማወቅ በስሜት ብቻ የሚነዱ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ [...]

Read More

የወያኔን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማፋጠን ኅብረታችን ይጠንክር!!!

ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በግፍ ሕይወታቸው ባጡ ዜጎች መርዶ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እና ቁጭት ይገልፃል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል። ህወሓት እና አጋፋሪው ኦህዴድ በነዙት ሽብር ሳቢያ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ፣ የተደበደባችሁ እና ለእስር የተዳረጋችሁ ወገኖቻችንም ህመማችሁም እስራችሁም የሁላችንም ነው። መላው ኢትዮጵያዊ ወገናችሁ ከእናንተ ጋር ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ተደብድቧል፣ ተግዟል፣ ታስሯል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው [...]

Read More