Home » Archives by category » Slider Post

የእሥርና እንግልት መበራከት የነጻነት ትግሉን ያጠናክራል እንጅ አያዳፍነውም!

በተለያየ ጊዜና ቦታ የሚኖሩ አንባገነን ገዥዎች በሙሉ ከሚመሳሰሉባቸው ባህሪያት አንዱ በሥልጣናቸው የሚመጣባቸውን ተቃወሚ ለማጥፋት በቁጥጥራቸው ሥር የሚገኘውን ማንኛውንም ዓይነት ሃይልና ጉልበት ከመጠቀም ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸው ነው። የሌላውን አገር ትተን በአገራችን የታየውን የቅርብ ጊዜ ትውስታ ብቻ ብንመለከት ለወያኔ መፈጠርና ለድል መብቃት ምክንያት የሆነው ደርግ ለሥልጣኑ የሚያሰጉት የመሠሉትን ሁሉ መንጥሮ ለመጣል ከጅምላ እስርና ግርፋት እስከ ጎዳና […]

የመን ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!

የመን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን አደጋ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የመብት አፈና፣ ሥራ አጥነት፣ ችጋርና ተስፋ ማጣት ለመሸሽ የራሳቸውንና የዘመዶቻቸውን ጥሪት አሟጠው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለሚሰደዱ ወገኖቻችን የመን መሸጋገሪያቸው ናት። ዛሬ የህወሓት ወዳጅ የሆኑም ያልሆኑም የየመን አምባገነን ገዢዎች እርስ በርሳቸው እየተላለቁ፤ ከምድር እሳት እየነደባት መሆኑ ሳያንስ ከሰማይም እሳት እየዘነበባት ነው። እንኳን አሁንና […]

Read More

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል። ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ […]

Read More

ጉዞአችን ወደ ነፃነት ነው!! መዳረሻችንም የነፃነት አደባባይ ብቻ ነው!!

አለማችን አንባገነን ስታስተናግድ ወያኔ የመጀመሪያው አይደለም። ዘረኛንም እንዲሁ …….. እኛም ስለነፃነት ብለን ለትግል ሰንነሳ የመጀመሪያዎቹ አይደለንም …… አለማችን እንደየዘመኑና እንደ የወቅቱ አንባገነኖች ያለ የሌለ የመሳሪያና ወታደራዊ ሀይላቸውን በመጠቀም ህዝብን በፍርሀት አሸማቀውና ረግጠው ለመግዛት ሲውተረተሩ በተደጋጋሚ ታይተዋል። በዚያው ልክ ህዝባዊ ሀይልና መመከት ተስኗቸው ሲንኮታኮቱ በተደጋጋሚ የታየ ወደፊትም አናባገነኖች እስከተከሰቱ ድረስ በህዝባዊ ሀይል ተጠራርገው መቀመቅ ሲወርዱ መታየቱ […]

Read More

ተቀላቀሉን፤ ካልሆነም በያላችሁት ተደራጁ!

ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስለሚያደርሰው ዘርፈ ብዙ በደል ብዙ የተነገረለትና የተፃፈበት ብቻ ሳይሆን እየኖርንበት ያለ ሀቅ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚደርስበትን ስቃይ መታገስ ወደማይችልበት ጫፍ መድረሱ በሰበብ አስባቡ በሚፈነዳዱ ተቃውሞዎች የሚታይ ሀቅ ሆኗል። በሌሎች አገሮች እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ምሬት ሲኖር በጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ጥሪ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ አደባባይ ይወጣል። ከሕዝብ አብራክ የወጣው ጦር ሠራዊትና ፓሊስ ከተበደለው […]

Read More

በህወሓት ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎች ሁሉ ወደ እምቢተኝነት ይደጉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በአለፉት 23 ዓመታት በህወሓት ዘረኛ አገዛዝ የደረሰበት ስቃይ እንዲቀንስ፤ ገዢዎቹ ከጫንቃው እንዲወዱ፤ ህወሓትን አውርዶ የሚፈልጋቸው መሪዎችን በነፃነት እንዲመርጥ ሲጠይቅና አቤቱታ ሲያሰማ ቆይቷል። በ1997 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝብ ምኞት የሚሳካ መስሎ የታየ የነበረ ቢሆንም በአገዛዙ አረመኔዓዊ እርምጃ ተሰናክሏል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ድምፃችን ይሰማ” የሚሉ አቤታዎች ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መምጣት ጀምሯል – “ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሞች”፣ “ድምፃችን […]

Read More

የአድዋ ድልን እያከበርን ለዛሬ ነፃነታች ቃል እንግባ!

መቶ አስራ ዘጠነኛውን የአድዋ ድል በዓል እየዘከርን እንገኛለን። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም ቀደምቶቻችን በርካታ የውስጥና የውጭ ችግሮች ነበሩባቸው። እንደዛሬው ሁሉ ያኔም በመካከላቸው የሀሳብና የጥቅም ልዩነቶች ነበሩ። ያም ሆኖ ግን ቀደምቶቻችን በአገር ነፃነት ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ መግባባት ላይ መድረስ በመቻላቸው በዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችና ድርጅት የተጠናከረውን የአውሮፓ ጦር በጥቁር የጦር አዛዦችና ተዋጊዎች መመከት ቻሉ። ከአድዋ በፊት አፍሪቃ […]

Read More

ምርጫ ለኢትዮጵያ ወታደርና ፓሊስ: – ለህወሓት ባርነት ወይስ ለኢትዮጵያ ነፃነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውትድርና ከፍተኛ ክብር አለው። ውትድርና ከሙያና ሥራ በላይ የነፃነትና የክብር መገለጫ፤ ሀገርን ከባዕድ ወረራ መከላከያ ጋሻ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህግና ሥርዓት አክባሪ በመሆኑ ለፓሊስም ከፍተኛ አክብሮት አለው። የፓሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ መሆኑ በኢትዮጵያ ባህል የተከበረ ቦታና እውቅና አለው። በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ግን ይህ እየተቀየረ ነው። የህወሓት አዛዦች […]

Read More

አዋራጅ ሰልፎችና ድግሶች እንዲያበቁ ህወሓት ይወገድ!

ድግሶችን፣ ወታደራዊ ሰልፎችንና ሀውልቶችን ማብዛት የአባገነኖች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝም በሕዝብ እየተጠላ፣ እያረጀና እየወላለቀ በሄደ መጠን በየተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ደግሶ መብላት፤ ወታደራዊ ሰልፍና የመሣሪያ ጋጋታ ማሳየት እና በየመንደሩ ሀውልት መመረቅ ሙያው አድርጎት ቆይቷል። የህወሓት ድግሶችና ፌሽታዎች የአገራችን ሀብት ከማሟጠጣቸውም በላይ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ የአርሶ አደሮችንና የአነስተኛ ነጋዴዎችን ኪስ እያራቆቱ ናቸው። በአስር ሺዎች […]

Read More

የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

ህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት […]

Read More